ከ30 ዓመታት በላይ አካባቢ ሲበክልና ለሰው ጤና ጎጂ የሆነ በካይ ፍሳሽ ቆሻሻ በዘፈቀደ ሲለቅ ነበር የተባለው የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ብክለቱን ማቆም ካልቻለ ከቦታው እንዲነሳ በፍርድ ቤት ተወሰነበት፡፡
ለሕዝብ ጥቅም ሲባል በፍርድ ቤት ተቋሙን ላይ ክስ በመመስረትና ለ5 ዓመታት በመሞገት የተጠቀሰው ውሳኔ እንዲሰጥ ምክንያት የሆነው ‘’ቁም ለአካባቢ’’ የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው፡፡
በጎ ፈቃደኛ የህግ ባለሞያዎች የአካባቢ ብክለትን በተመለከተ መሰል ስራዎችን የሚከውነው ቁም ለአካባቢ፤ ከዚህ ቀደምም በ7 ተቋማት ላይ ተመሳሳይ ውሳኔ በፍርድ ቤት መገኘቱን ነግሮናል፡፡
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ብክለቱተን ማቆም ካልቻለ አሁን ካለበት ቦታ ተነስቶ ሌላ ቦታ ላይ ደረጃውን የጠበቀና ዘመናዊ የእንስሳት እርድ የሚከውነበት ቦታ እንዲያዘጋጅ በፍርድ ቤት ተወስኖበታል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ትዕግስት ዘሪሁን
Comments