top of page

ህዳር 20፣2017 - በአዲስ አበባ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍ በእጥፍ ጨመረ

በአዲስ አበባ በቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍ በእጥፍ(100% ) ጭማሪ መደረጉን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ተናግሯል፡፡


በዚህም አሁን 10 ብር እየተከፈለበት የነበው ታሪፍ 20 ብር ሆኗል፡፡


የተደረገው የታሪፍ ጭማሪ ከታህሳስ 01፣2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ነው ተብሏል፡፡


የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በሁለት አቅጣጫ (ከሰሜን ወደ ደቡብ/ከጊዮርጊስ - ቃሊቲ/ እና ከምስራቅ ወደ ምዕራብ/ከአያት - ጦር ሀይሎች/ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠ እንደሆ አስረድቷል፡፡


በየቀኑ በአስር ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ እያጓጓዘ ይገኛል ሲል ቢሮው ተናግሯል፡፡

留言


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page