top of page

ህዳር 19፣2017 - ድምፃዊት አስቴር አወቀ እና ሜትሮፖሊታን ሪል ስቴት አብረው ለመስራት ተስማሙ።

  • sheger1021fm
  • Nov 28, 2024
  • 1 min read

ድምፃዊት አስቴር አወቀ እና ሜትሮፖሊታን ሪል ስቴት አብረው ለመስራት ተስማሙ።


ስምምነቱ በዛሬ እለት የሜትሮፖሊታን ሪል ስቴት ሀላፊዎች እና የአስቴር አወቀ ማናጀር አዳነች ወርቁ ይፋ አድርገውታል።


በስምምነቱ መሰረት ድምፃዊት አስቴር አወቀ እና ሜትሮፓሊታን ሪል ስቴት የበጎ አድራጎት ስራዎችን አብረው ይሰራሉ ተብሏል።


ከዚህ በተጨማሪም ኩባንያው የድምፃዊቷን አልበም ስራ ወጪ ይሸፍናል፣ የኮንሰርት፣ የማስታወቂያ ስራዎችንም አብረው ይሰራሉ ሲባል ሰምተናል።

በተለይ በበጎ አድራጎት ስራዎች ኩባንያውና ድምፃዊቷ የሚሰሩት ስራ የሚዲያ ሽፉን እንዲያገኝ ይሰራሉ ተብሏል።


የአብሮ የመስራት ስምምነቱ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ በግልፅ አልተጠቀሰም።


ከተወዳጇ የሙዚቃ ባለሞያ ጋር የተደረገው ይህ የጋራ የስራ ስምምነት ሜትሮፖሊታን ማህበረሰብ አቀፍ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ባለ መልኩ ለመሳተፍ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ተብሏል።

የሶል ሙዚቃ ንግስት የሚል ቅፅል ስም ማትረፍ የቻለችው ድምፃዊት አስቴር አወቀ አዲስ አልበም እንዲሁም የቀድሞ ስራዎችን በድጋሜ እየሰራች መሆኑን ማናጀሯ አዳነች ወርቁ ስትናገር ሰምተናል።


ሜትሮፓሊታን ሪል ስቴት ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ በቱርክ እና በአሜሪካ እንዲሁም ላለፉት 9 ዓመታት በኢትዮጵያ በርካታ የሪል ስቴት ፕሮጀከቶችን እያከናወነ ይገኛል ሲባል ሰምተናል።


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page