የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በጠራው ይፋዊ የኦዲት ሪፖርት ውይይት ላይ የመገኘት ግዴታ ቢኖርባቸውም ሳይገኙ ቀሩ፡፡
#የኢሚግሬሽንና_ዜግነት_አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በውይይቱ ላይ አለመገኘታቸው ቋሚ ኮሚቴውን አስቆጥቷል፡፡
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ቋሚ ኮሚቴው የ2015 እና 2016 በጀት ዓመት የፓስፖርት አገልግሎት አሰጣጥና ውጤታማነትን በተመለከተ የክዋኔ የኦዲት ሪፖርት እና የ2015 በጀት ዓመት የሒሳብ ኦዲት ሪፖርት ላይ ለመወያየት በጠራው ስብሰባ ላይ የመገኘት ግዴታ ቢኖርባቸውም ሳይገኙ ቀርተዋል፡፡

የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሺመቤት ደምሴ ‘’ምክር ቤቱ ተመርምረው የቀረቡለትን የዋና #ኦዲት_ሪፖርት በይፋ ውይይት በሚያደርግበት ወቅት የመስሪያ ቤቱ የበላይ ሀላፊ የመኖር ግዴታ አለበት’’ ብለዋል፡፡
‘’የመጣችሁትን የስራ ሀላፊዎች ሀላፊነታችሁን አክብራቹሀል’’ ያሉት ሰብሳቢዋ ‘’ነገር ግን የመስሪያ ቤቱ ዋና ሀላፊ በኦዲት ሪፖርት ምርመራ ላይ የመገኘት ግዴታ አለባቸው’’ ሲሉም ተናግረዋል፡፡
‘’ዋና ሀላፊዋ ሀገር ውስጥ የሉም’’ ያሉት ሰብሳቢዋ ‘’ነገር ግን #ደብዳቤያችን ከደረሳቸው በኋላ ነው ከሀገር የወጡት ይህ ድርጊትም ተገቢ እንዳልሆነ ማሳወቅ እፈልጋለሁ’’ ብለዋል፡፡
ይህም ድርጊት የሚያሳየው ለመስሪያ ቤቱ የሰጣችሁትን ትኩረት ነው ብለዋል፡፡
‘’ይህን ፈፅሜአለሁ ይህን አልፈፀምኩም ብሎ ፊት ለፊት ማስረዳት ከ1 የስራ ሀላፊ የሚጠበቅ ነው ብለው ከዚህ በኋላ ይህ ድርጊት እንዳይፈፀም እንድታሳውቁልን እፈልጋለሁ’’ ሲሉ አሳስበዋል፡፡
የመስሪያ ቤቱ የስራ ሀላፊዎችም ይህ ድርጊት ከዚህ በኋላ እንደማይደገም ቃል በመግባት ይቅርታም ጠይቀዋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments