top of page

ህዳር 18፣2016 - የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና፤ የሞያ ማማከር እና መምሪያ ድጋፍ አገልግሎት ይፋ ተደረገ

የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና፤ የሞያ ማማከር እና መምሪያ ድጋፍ አገልግሎት ይፋ ተደረገ።


ይፋ የተደረገው መምሪያ እና ማማክር ድጋፍ አገልግሎት ወጣቶች ወደ ቴክኒክና ሞያ ሲገቡ መማር ያለባቸውን ሞያ በቀልሉ እንዲመርጡ ይረዳቸዋል ተብሏል።


በተለይ ተማሪዎች የሚማሩትን ሞያ ከመጀመራቸው በፊት እንዲያውቁት ያደርጋል የተባለው መምሪያው ተመርቀው ከወጡም በኋላ በቀላሉ ወደ ስራ እንዲገቡ ይረዳል ሲባል ሰምተናል፡፡


ወደስራ እየገባ ነው የተባለው በኢትዮጵያ የቴክኒክና ሞያ ስልጠና የሞያ ማማከርና መምሪያ ድጋፍ አገልግሎት ተማሪዎች ከመደበኛው የመማር ማስተማር በተጨማሪ እራሳቸውን እንዲያበቁ ይረዳል ተብሏል።


የቴክኒክና ሞያ ስልጠና ተቋማት ወጣቶች ክህሎት እንዲኖራቸውና የእራሳቸወን ስራ እንዲፈጥሩ እንደሚረዳ ተነግሯል።


በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኑክና ሞያ ትምህርት ዘርፍ አማካሪ ዶክተር ተሾመ ለማ እንዳሉት አሁን የተዘጋጀው መምሪያ እና የማማከር ድጋፍ አገልግሎት ተማሪዎች በቀላሉ በሚፈልጉት ዘርፍ የሞያ ዘርፍ ውጤታማ እንዲሆኑ ያደርጋል ብለዋል።

መምሪያው የቴክኒክና ሞያ ተቋማት የትምህርት ጥራት አቅም የሚጨምር እና ብቁ እና ክህሎት የተላበሰ የሰው ሀይል ለመፍጠር ይረዳቸዋል ሲሉ ተናግረዋል።


ከዚህም ባለፈ ሰልጣኝ ወጣቶች ስልጠናቸውን ሲያጠናቅቁ ስራዎችን በቀላሉ እንዲያገኙ ይረዳቸዋል ሲባል ሰምተናል።


የቴክኒክና ሞያ ስልጠና ተቋማት የሞያ ማማከር ድጋፍ አገልግሎት እና መምሪያ ሲዘጋጅ መንግስታዊ እና ሌሎች አጋር አካላት ተሳትፈዋል ተብሏል።


መምሪያው ተግባራዊ ሲሆን በዘርፉ ክህሎት እና እውቀት ያለው ሰልጣኝ ከመፍጠር አኳያ ትልቅ ለውጥ ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል መባሉን ሰምተናል።በረከት አካሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz


bottom of page