በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በሚከሰቱ ግጭቶች ምክንያት ሰዎች የከፋ ሕይወት እንዲኖሩ አድርጓል ሲል የሰላም ሚኒስቴር ተናገረ፡፡
በሀገሪቱ እዚህም እዚያም በሚከሰቱ ግጭቶች ምክንያት ንጹሃን ሕይወታቸውን እያጡ፣ የአካል ጉዳተኛ እየሆኑ ንብረታቸው እየወደመና ከቤት ንብረታቸው እየተፈናቀሉ የእንግልት ኑሮ እንዲኖሩ ምክንያት ሆኗቸው ብሏል፡፡
ይህ የተባለው ዛሬ እየተካሄደ በሚገኘው የሰላም ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ነው፡፡
የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ስዩም መስፍን ሰዎችን ከተጋረጠባቸው አደጋ ለመታደግ ለነገ የማይባል ጉዳይ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል ብለዋል፡፡
በግጭቶች ሳቢያ ንብረታቸው የወደመባቸውን ከቤት ንብረታቸውን የተፈናቀሉትን እና የስነ ልቦና ስብራት የደረሰባቸው ንፁሃንን ከችግራቸው ሊያወጣ የሚችል መፍትሄ መዘርጋት ያስፈጋል ሲሉ ሰምተናል፡፡
በሚፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት የህዝብ ለህዝብ መልካም ግንኙነት እና አብሮ የመኖር እሴት በእጅጉ ተሸርሽሯል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የንግድ፣ የማህበራዊና የኢኮኖሚ ትስስሮችን ወደ ነበሩበት መመለስ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡
የሰላም ሚኒስቴር ለተፈጠሩ ጉዳቶች ምላሽ ከመስጠት ጎን ለጎን አለመግባባቶች በሚታዩባቸው አንዳንድ አካባቢዎች የግጭት መከላከል ስራ እየሰራው እንደሆነ ይታወቅኝ ብሏል፡፡
ግጭቶችን አስቀድሞ ለመከላከል ትልድ ቅርሻ ያለው የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት መጠቀም ያስፈልጋል ያሉት ሃላፊው ከዝቅተኛ የመንግስት መዋቅር እስከ ፌዴራል ድረስ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ስርዓት ለመገንባት የሰላም ሚኒስቴር እየሰራ እንደሆነ ተናግሯል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments