ከመርካቶ የጀመረውን የደረሰኝ ግብይት ላይ የሚያደርገውን ቁጥጥር 250 ባለሞያዎችን በማሰማራት በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች እየሰራበት መሆኑን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ተናገረ፡፡
በከተማዋ ባሉ ሁሉም ስፍራዎች ግብይቶች ያለ ደረሰኝ እንዳይፈፀሙ ለማድረግ የቁጥጥር ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የሚናገረው ቢሮው ከዚህ ጋር በተያያዘ በመርካቶ አካባቢ ከተፈጠረው ውዥምብር ወዲህ በመርካቶ የንግድ እንቅስቃሴው ምን መልክ አለው?
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ፤ #መርካቶ አካባቢ ያለው የንግድ እንቅስቃሴ በአብዛኛው ጥሩ ነው ነገር ግን አልፎ አልፎ ሱቆችን መዝጋት፣የቁጥጥር ባለሙያዎች በማይኖሩባቸው ሰዓታት ማታ እና በጣም በጠዋት ግብይት የመፈፀም ዝንባሌ እንዳለ ነግረውናል፡፡

ከዚህ በኋላ በከተማዋ ያለ ደረሰኝ ግብይት እንዳይፈፀም ለማድረግ በመስተዳድሩ የተቋቋመው የኑሮ ውድነትና የህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ግብረሃይል ባሰማራቸው በእነዚህ ባለሙያዎቹ የቁጥጥር ስራ ይሰራል፤ ያለ #ደረሰኝ ሲሸጥ ተገኘ 100 ሺህ ብር ይቀጣል፤ ይህንን ተግባር ከቀጠለበት ቅጣቱም እየጨመረ ይሄዳል፡፡
ከተደጋገመ ነጋዴው ሌላ ማጣራት ይደረግበታልም ብለውናል የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ አቶ ሰውነት ፡፡
የአቶ ሰውነት ገለፃ ነጋዴዎች ከዚህ ቀደም ያለደረሰኝ ገዝተውት #በመጋዘን ያስቀመጡት ንብረት ካለ ዓይነቱን፣ መጠኑን፣ የተገዛበትን ዋጋ ግብር ለሚከፍልበት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በማሳወቅ እቃውን ሲሸጡ ግን በደረሰኝ እንዲሸጡ ከዚያም ግብር በሚከፍሉበት ወቅት ያለደረሰኝ የገዙት እቃ በሚከፍሉት ግብር ላይ ታሳቢ እንዲደረግላቸው የከተማዋ ገቢዎች ቢሮ የአሰራር ሥርዓት ዘርግቷል፡፡
ምንታምር ፀጋው
Comentarios