top of page

ህዳር 16፣2017 - ነዳጅ የሚያከፋፍሉ ኩባንያዎች 5,000 ሊትር ክምችት የሚይዝ ዲፖ እና ቢያንስ አምስት ማደያ እንዲኖራቸው በህግ ሊገደዱ ነው

ነዳጅ የሚያከፋፍሉ ኩባንያዎች 5,000 ሊትር ክምችት የሚይዝ ዴፖ እና ቢያንስ አምስት ማደያ እንዲኖራቸው በህግ ሊገደዱ ነው፡፡


ለፓርላማ ቀርቦ ከመፅደቁ በፊት ውይይት እየተደረገበት ያለው የነዳጅና ነዳጅ ውጤቾች ግብይት ሥርዓትን ለመደንገግ የወጣው ረቂቅ አዋጅ እንደሚለው ነባር #የነዳጅ_አከፋፋይ ኩባንያዎች 5,000 ሊትር ክምችት የሚይዝ ዴፖና ለጊዜው ሶስት ማደያ እንዲኖራቸው ያስገድዳል፡፡


በ2 ዓመት ውስጥ ግን ተጨማሪ 2 ማደያ ገንብተው 5 እንዲያደረሱት በህጉ ተደንግጓል፡፡


ኩባንያው አዲስ ከሆነ ሲጀምር 2,500 ሊትር የሚይዝ #ዴፖና ሁለት ማደያ ይዞ ስራውን መጀመር ይችላል የተባለ ሲሆን የተጠቀሰውን ደረጃ በ2 ዓመት ውስጥ እንዲያሟላ ህጉ ያስገድዳል፡፡


የነዳጅን ግብይትን በዘመናዊ መንገድ ለመምራት፣ የሚታየውን ምርቱን የመደበቅና ከባዕድ ነገር ጋር የመቀላቀል ችግርም ለመፍታት ያግዛል የተባለው ይኸው ህግ በነዳጅ ግብይት ላይ ለመሳተፍ የብቃት ማረጋገጫ እንዲኖር የሚያስገድድ ነው ተብሏል፡፡

በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ ውይይት ሲደረግ ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተገኙ ተወካይ አዋጅ በነዳጅ ማደያዎች የተለያየ ግዴታ መጣሉን ተናግረዋል፡፡


ከክልል ንግድ ቢሮዎች የተገኙ ተወካዮች በበኩላቸው የነዳጅ አቀራረቡ ፍትሃዊ አይደለም ብለዋል፡፡


ጥቂት አከፋፋዮች እስከ 80 በመቶውን አቅርቦት በብቸኝት በመያዛቸው ግብይቱ ፍትሃዊነት ይጎድለዋል፤ ህጉም ይህን የሚያርም እንዲሆን ሲሉ ጠይቀዋል፡፡


የነዳጅ ግብይትን የሚመለከተው ረቂቅ አዋጅ የነዳጅ ሽያጭ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ መላ መፈፀም እንዳለበት ያስገድዳል፡፡


ይሁንና የግብይትን ሥርዓቱን የሚቆጣጠሩ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴርን ጨምሮ በእያንዳንዱ ሂደት በቴክኖሎጂ የታገዘ ቁጥጥር እንዲደረግበት በህጉ አስገዳጅ እንዲሆን ተጠይቋል፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን

Comments


bottom of page