top of page

ህዳር 15፣2016 - ‘’ጎህ ቤቶች ባንክ’’ በ2015 የበጀት ዓመት ያልተጣራ 6.38 ሚሊዮን ብር ማትረፉን ተናገረ

በኢትዮጵያየመጀመሪያው የቤት ፋይናንስ አቅራቢ ሆኖ የተቋቋመው ‘’ጎህ ቤቶች ባንክ’’ በ2015 የበጀት ዓመት ያልተጣራ 6.38 ሚሊዮን ብር ማትረፉን ተናገረ።


ትርፉበ2014 የበጀት ዓመት ከተገኘው ትርፍ ጋር ሲነፃፀር የ19 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል ብሏል፡፡


ለአዳዲስቅርንጫፎች ማስፋፊያ፣ የቢሮ ኪራይ፣ አላቂ ቁሳቁሶች ማሟላት፣ የሠራተኞች ቁጥር መጨመርን ተከትሎ የመጣው የደመወዝና ጥቅማጥቅም መጠን ማደግ፣ በዋጋ መናር ምክንያት የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር፣ ከካፒታል ዕቃዎች እና ቴክኖሎጂ ጋር በተያያዘ የእርጅና ቅናሽ መጠን ከፍ ማለት ለታየው ቅናሽ ምክንያት ከሆኑት መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው ሲልባንኩ አስረድቷል።


ጎህቤቶች ባንክ የባለአክሲዮኖች 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በዛሬው እለት አካሂዷል።

የባንኩየዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጌታሁን ናና የ2015 የበጀት ዓመት በሀገር ውስጥም በውጪም በፋይናንስ ዘርፉ ላይ ተፅናኖ ያደረጉ ሁኔታዎችን ጠቅሰው ይህምየታቀደውን ያህል ባይሆንም ተስፋ ሰጪ እና አበረታች ውጤቶችን ባንኩ አስመዝግቧል ብለዋል።


በበጀትዓመቱ የተሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ255.3 በመቶ አድጓል ተብሏል፡፡ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ 911.8 ሚሊዮን ብር ደርሷል ተብሏል ።


ባንኩበበጀት ዓመቱ ለሞርጌጅ እና ሌሎች የንግድ ሥራዎች የተሰጠው ብድር እና ቅድሚያ ክፍያ ከምችት 1.3 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተነግሯል።


ከተሰጠውብድር ውስጥ 49.2 በመቶው የረጅም ጊዜ የሞርጌጅ ብድር፣ ቀሪው ደግሞ የንግድ ብድር መሆኑን የዳይሬክተሮች ቦርድ ተሰብሳቢው ጠቅሰዋል፡፡


ጎህቤቶች ባንክ በሂሳብ ዓመቱ በአጠቃላይ 3 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘቱን አስረድቷል።


ባንኩ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 2.63 ቢሊዮን ብር ፣ አጠቃላይ ካፒታሉ ደግሞ 1.55 ቢሊዮን ብር መድረሱም ተጠቅሷል።


ጎህቤቶች ባንክ ከሪል ስቴት አልሚዎች ጋር በትብብር ለመስራት ጥረት እያደረገ መሆኑን የቦርድ ሰብሳቢው አስረድተዋል።


ከዚህምጋር በተያያዘ ባንኩ በከፊል ባለቤት ከሆነበት ጎሕ የቤቶች ልማትና ገበያ አ.ማ. ከሚባል የሪል ስቴት ኩባንያ ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ሳሪስ አካባቢ የመኖሪያ እፓርትመንቶችን በሪል ስቴት ኩባንያው በኩል ለማስገንባትና ለተጠቀሚዎች ለማስተላለፍ ዝግጅቱን አጠናቋል ብለዋል፡፡


ባንኩከዚሀ ኩባንያ በተጨማሪ የመኖሪያ ቤቶች አቅርቦትን ለማሻሻል ከሚጥሩ ሌሎች መሰል ድርጅቶችም ጋር በቅርበት እሰራለሁ ብሏል፡


የሞርጌጅባንክ ሥራን በተገቢው ሁኔታ ለመስራት የሚያስችል ግልጽ የሆነ የሕግ ማዕቀፍ አለመኖር፣ ቤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ የግንባታ እቃዎች ዋጋ በየጊዜው መናር፣ ለአጭርም ሆነ ረዥም ጊዜ የሚቆይ ገንዘብ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ማሰባሰብ አስቸጋሪ መሆን ካሉብኝ ፈተናዎች መካከል ይገኙበታል ሲል ባንኩ ተናግሯል።የሸገርንወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz


bottom of page