top of page

ህዳር 13፣2017 - ኢትዮፒካር፤ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ 3 ‘’የኔታ ብራንድ’’ ተሽከርካሪዎች ለኢትዮጵያ ገበያ ማቅረብ መጀመሩን ተናገረ

  • Nov 22, 2024
  • 1 min read

በኢትዮፒካር በኩል ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡትን የኔታ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሸከርካሪዎችን የሚያመርተው "ሆን ዞ" የሚባለው የቻይና ኩባያ ነው፡፡


የሆን ዞ የኢትዮጵያና ምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ ወኪል የሆነው ኢትዮፒካር ወደ ሀገር ቤት እያስመጣቸው ያሉት ሶስቱ የኔ ምርቶች ኔታ ዩ (NETA U)፣ ኔታ አያ (NETA Aya) እንዲሁም ኔታ ኤክስ(NETA X) የሚባሉ ናቸው፡፡

ተሽከርካሪዎቹ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር አስተባባሪነት በተዘጋጀው እና ዛሬ በተከፈተውና እስከ ህዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በሚቆየው የ"ኢትዮ ግሪን ሞቢሊቲ 2024" ኤግዚቢሽን እና አለም አቀፍ ሲምፖዚየም ላይ ቀርበዋል፡፡

በዚህ "ኢትዮ ግሪን ሞቢሊቲ 2024" ኤግዚቢሽን ላይ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት እና የውጭ ሃገራት ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን ኢትዮፒካር ያቀረባቸውን የኔታ ብራንድ ምርቶችን በመጎብኘት አድናቆት ሰጥተዋል፣ አበረታትተዋል፡፡


ኢትዮፒካር እነዚህን የኔታ ብራንድ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች አንደሚያከፋፍልም አስረድቷል፡፡


ኢትዮፒካር ከዚህ በፊትም የተለያዩ ዓይነት ተሽከርካሪዎችን ከውጪ ሃገር ሲያስመጣ መቆየቱ ይታወሳል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Recent Posts

See All
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የህፃናት እንክብካቤ ማዕከላት ወይም ማቆያዎች ላይ ለውጦች እየመጡ ነው ተባለ፡፡

ሐምሌ 15 2018 በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የህፃናት እንክብካቤ ማዕከላት ወይም ማቆያዎች ላይ ለውጦች እየመጡ ነው ተባለ፡፡ ከጥቂት አመታት በፊት የህፃናት ማቆያዎቹ ጥቂት ነበሩ ያለው የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት አሁን ላይ ከፍተኛ መሻሻሎች ታይተውበታል ብሏል፡፡ ጥናቱም በግል እና በመንግስት ማ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page