top of page

ህዳር 11፣2017 - አህመድ አብተው(ዶ/ር) የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ

አህመድ አብተው(ዶ/ር) የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ፡፡


አህመድ አብተው(ዶ/ር) የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በመሆን መሾማቸውን ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ሰምተናል።


ዶክተር አህመድ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት ከትናንት ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ነው ተብሏል፡፡

ይህንን ለሸገር ራዲዮ የነገሩት በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የህዝብ ግኑኝነት እና ኮሙኒኬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ማርታ አድማሱ ናቸው።


ቀድሞ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣንን በዋና ዳይሬክተርነት ሲመሩ የነበሩት አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል፡፡


ማንያዘዋል ጌታሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


bottom of page