top of page

ህዳር 11፣2017 - ‘’በግጭቶችና ጦርነቶች የአምቡላንሶች ወዲህ ወዲያ በመገደቡ እናቶች በወሊድ ህይወታቸው እያለፈ ነው’’ የሚድዋይፈሮች ማህበር

  • sheger1021fm
  • Nov 20, 2024
  • 1 min read

‘’በግጭቶችና ጦርነቶች ምክንያት የአምቡላንሶች ወዲህ ወዲያ በመገደቡ እናቶች በወሊድ ምክንያት ህይወታቸው እያለፈ ነው’’ ሲል የኢትዮጵያ ሚድዋይፈሮች ማህበር ተናገረ፡፡


ችግሩ የበረታውም በአማራ ክልል ነው ተብሏል፡፡


በአማራ ክልል ባለው ግጭት በዚህ አንድ ወር ውስጥ ብቻ በወሊድ ምክንያት በጥቂቱ የአምስት እናቶች ህይወት ማለፉን ማህበሩ ለሸገር ሬዲዮ ተናግሯል።


የኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማህበር ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ማዘንጊያ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ቅድሚያ ተጎጂ የሚሆኑት እናቶችና ህፃናት መሆናቸውን አንስተው ‘’በማህበሩ ስር ያሉ ባለሙያዎች ባደረሱን መረጃ በአማራ ክልል በግጭቱ ምክንያት እናቶች ወደ ጤና ተቋማት ሳይሄዱ ቤታቸው ውስጥ እየሞቱ ነው’’ ብለዋል።


‘’በሰፊው ዳሰሳ ስላልተደረገ ነው እንጂ በአንድ ወር ውስጥ የሞቱት እናቶች ቁጥር ከዚህም ሊያልፍ ይችላል’’ ሲሉ ነግረውናል።


በወለጋ ዞኖች አካባቢም የአምቡላንሶች እንቅስቃሴ ገደብ እንዳለም ጠቁመዋል።


በግጭት ቀጠና ውስጥ ያሉ ሁሉም ሀይሎች የጤና ባለሙያዎችን እና የአምቡላንሶችን እንቅስቃሴ ነፃ በማድረግ የእናቶችን ህይወት መታደግ እንደሚገባም ተናግረዋል።


በግጭት ምክንያት የመንገዶች መዘጋጋት ከሚፈጥረው የእናቶች ሞት ባለፈም በዘርፉ ሌላኛው ችግር ደግሞ የባለሙያዎች እጥረት መሆኑን የሚያነሱት አቶ ፍቃዱ በተለይ በኦሮሚያ ክልል ቦረና፣ ወለጋ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ሰሜን ሸዋ እና ምዕራብ ሸዋ የሚድዋይደሮች እጥረት ያለባቸው ቦታዎች መሆናቸውንም ነግረውናል።


ፍቅሩ አምባቸው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page