ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት በሁሉም ረገድ የወላጅ ወይም የአሳዳጊ ክትትል እና ቁጥጥር እንደሚያስፈልጋቸው ይታመናል፡፡
ጥናቶች እንደሚያሳዩት በከተሞች ከ12 እስከ 17 ዓመት እድሜ ያላቸው ህፃናት 40 በመቶው የኢንተርኔት ተጠቃሚ ናቸው፡፡
ከመካከላቸው 13 በመቶዎቹ ደግሞ ያለወላጅ ክትትልና ቁጥጥር #ኢንተርኔት ይጠቀማሉ ተብሏል፡፡
ይህም በአለም አቀፍ ደረጃ እየሰፋ ለመጣው የኢንተርኔትን መሰረት ባደረገ የህፃናት ወሲባዊ ብዝበዛ እንዲያጋልጣቸው ስጋቱ ከፍ ያለ ነው ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ ለበይነ መረብ ፆታዊ እና ወሲባዊ ጥቃት የሚጋለጡ ህፃናት ቁጥርም እየጨመረ ነው ተብሏል፡፡
በተለይ እየተለወጠ ከመጣው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ጋር በተያያዘ ኢንተርኔትን በመጠቀም የሚደርስ የህፃናት #ወሲባዊ_ብዝበዛ የኢትዮጵያ ትልቁ ስጋት እየሆነ መጥቷል ተብሏል።
ወንጀሉ በሌሎች ያደጉ ሀገራት ላይ በስፋት እንደሚታይ እና ኢንተርኔትን በመጠቀም በተለያዩ #ማህበራዊ_መገናኛ ዘዴዎች ወሲባዊ ነክ ምስሎችን እንዲሁም ጽሁፎችን ለህፃናቱ በማጋራት እና ስሜታቸውን በማነሳሳት የሚፈፀም መሆኑ ይነገራል።
ኢትዮጵያ ይህን ዘመን አመጣሽ ወንጀል እና የህፃናትን የፍትህ ጉዳዮችን በተመለከተ በተለይ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው የህግ ባለሞያዎች ዳኞችን ጨምሮ መስራት እንደሚገባት ተነግሯል።
በቅርቡ ይኸው ስጋት ሆኗል የተባለውን ኢንተርኔትን በመጠቀም የሚፈጸም የህጻናት ወሲባዊ ብዝበዛ ቀድሞ ከወጣው የኢትዮጵያ የወንጀል ህግ ጋር እንዴት ተጣጥሞ ይሰራበታል?
ባለሙያዎችስ ጉዳዩን የሚያዩት ዳኞች ምን ያህል ግንዛቤ አላቸው የሚለው በባለሞያዎች ጥናት ተደርጎበታል።
ምህረት ስዩም
Comments