top of page

ህዳር 10፣2017 - በሶማሌላንድ በቅርቡ በተካሄደው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ መሪው ሞሐመድ አብዱላሂ አሸነፉ

በሶማሌላንድ በቅርቡ በተካሄደው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ መሪው ሞሐመድ አብዱላሂ አሸነፉ፡፡


ሞሐመድ አብዱላሂ በምርጫው ማሸነፋቸውን የሀገሪቱ የምርጫ አከናዋኝ መስሪያ ቤት እወቁልኝ ማለቱን አሶሼትድ ፕሬስ ፅፏል፡፡


የተቃዋሚ መሪው በምርጫው ያሸነፉት ከተሰጠው ድምፅ ከ50 በመቶ በላይ የሆነውን በማግኘት ነው ተብሏል፡፡


በስልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዘዳንት ሙሴ ቢሒ ከተሰጠው ድምፅ ያገኙት 30 በመቶ ያህሉን እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡


ሙሴ ቢሒ ላለፉት 7 ዓመታት ስልጣን ላይ ቆይተዋል ተብሏል፡፡


ሶማሌላንድ ራሷን ከተቀረችዋ ሶማሊያ ከነጠለች 33 ዓመታትን እንዳስቆጠረች መረጃው አስታውሷል፡፡


የኔነህ ከበደ

Comments


bottom of page