top of page

ህዳር 10፣2017 - ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 55 የፖለቲካ ፓርቲዎች አብረውት እየሰሩ መሆኑን ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Nov 19, 2024
  • 1 min read

ብሔራዊ መግባባትን ለማምጣት በሚከወነው ሀገራዊ ምክክር 55 የፖለቲካ ፓርቲዎች አብረውት እየሰሩ መሆኑን ተናገረ፡፡


ይሁንና ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር አብሮ ለመስራት በፈረሙ ማግስት ለእስር የሚዳረጉ እንዳሉ አቤቱታ ያቀርቡልናል ሲሉ ዋና ኮሚሽነሩ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ተናግረዋል፡፡


ዋና ኮሚሽነሩ የኮሚሽኑን የስራ አፈፃፀም በተመለከተ ዛሬ በፓርላማ ተገኝተው ሪፖርታቸውን አቅርበዋል፡፡


የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያቀርቡልንን የተጠቀሰውን እና መሰል አቤቱታ ተቀብለን ችግሩን በተመለከተም ለሚመለከተው አካል ጥያቄውን አቅርበን የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋና አስቻይ ሁኔታ እንዲፈጠር እየሰራን ነው ብለዋል፡፡


ኮሚሽኑ በምክክር ብሔራዊ መግባባትን እንዲያመጣ የተሰጠው የስልጣን ጊዜ 3 ዓመት ሲሆን ሊጠናቀቅ የ3 ወራት እድሜ ቀርተውታል፡፡


ፕሮፌሰር መስፍንም አሁን ኮሚሽኑ ስራውን አጥጠናቆ የመውጫ ሪፖርቱን ለፓርላማው ማቅረብ የነበረበት ጊዜ እንደነበር ጠቅሰው በተለያዩ ክልሎች ያለው የፀጥታ ችግር ለስራው መጓተት ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል፡፡


ፓርላማው የኮሚሽኑን የስልጣን ጊዜ ካላራዘመለት ከ3 ወር በኋላ የተሰጠው የስልጣን ጊዜ ይጠናቀቃል፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን

Recent Posts

See All
የኢትዮጵያ ሂሳብ አዋቂዎች እና ኦዲተሮች ማህበር ከፍተኛ ቅሬታ የቀረበባቸውን የቦርድ አባላት በአዲስ ተካ፡፡

ጥር 12/2018 የኢትዮጵያ ሂሳብ አዋቂዎች እና ኦዲተሮች ማህበር "ስራቸውን በአግባቡ አልሰሩም፣ ህግን አላከበሩም ፣ ኦዲት ሪፖርት ለዓመታት አላቀረቡም ፣ጠቅላላ ጉባዔም ወቅቱን ጠብቀው ማካሄድ አልቻሉም"በሚል ከፍተኛ ቅሬታ የቀረበባቸውን የቦርድ አባላት በአዲስ ተካ፡፡ የቀድሞ ቦርድ አባላት ስራቸወን በአግባቡ ባለመ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page