ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ህዳር 24፣ 2014-ትልቁ የፋይናንስ ተቋም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ “አይዞን ኢትዮጵያ” በተባለ መላ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ3 ሚሊየን ዶላር በላይ ሰበሰብኩ አለ

Image
cbe

ትልቁ የፋይናንስ ተቋም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ “አይዞን ኢትዮጵያ” በተባለ መላ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ3 ሚሊየን ዶላር በላይ ሰበሰብኩ አለ፡፡

የተገኘው የውጭ ምንዛሬው ባስፈላጊው ጊዜ የተገኘ ነው ተብሏል፡፡

የውጭ ምንዛሬው በጥቂት ሳምንታት ውስጥም የተገኘ ነው ተብሏል፡፡

ለኢትዮጵያ ያሰቡ የኢትዮጵያ ወዳጆች አገራቸውን አይዞሽ በማለት የላኩት የአገር ልጆች 13 ሺህ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡

ከአሜሪካ 87 በመቶ ከቀረው አለም ደግሞ 23 በመቶ የመጣ መሆኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ ነግረውናል፡፡

እሳቸው ኢትዮጵያ ለዘለአለም በድህነት እንዳትኖር ውጪ አገር ያሉ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገር ቤት የውጭ ምንዛሬ ሲልኩ በህጋዊ መንገድ ይሁን ሲሉ ተናግረዋል፡፡ 

ከውጭ አገር ወደ አገር ቤት የሚገባው የውጭ ምንዛሬ 30 በመቶ የሚሆነው ብቻ በሕጋዊ መንገድ የሚገባ እንደሆነ ሰምተናል፡፡ 

የቀረው 70 በመቶ ከህግ ውጪ የሚገባና አገርን የሚጎዳ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋም ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ ስርዓት በመዘርጋቱ በውጪ የምትሆኑ የአገር ወዳጆች መላውን እየተጠቀማችሁ አገራችሁን ዳብሱ ተብላችኋል፡፡

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ከሌሎች ጋር በመተባበር ያለማው እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አለም አቀፍ የክፍያ መስመሩን ያመቻቸው የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ስላስገኘው ውጤት የተለያዩ ተቋማት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ዛሬ ጋዜጣዊ መግጫ ተሰጥቷል፡፡  

የብሔራዊ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በጦርነት ምክንያት 1.5 ሚሊየን ሰዎች መፈናቀላቸውን አስታውሰዋል፡፡ 

ድጋፉ በወቅቱ የተፈለገና በጊዜው የደረሰ መሆኑን ነግረውናል፡፡

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ በበኩሉ ቴክኖሎጂውን በማልማት ትልቅ ፕሮጀክቶችን ወደፊት እናስታዋውቃለን ሲሉ ሰምተናል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ ኢትዮጵያ ከአለም እንድትቆረጥ በሚደከምበት ጊዜ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከገንዘብ በበለጠ ካሉበት መዝመታቸው ቀላል አይደለም ብለዋል፡፡ 

አሁንም ለአገራቸው ልሳን መሆናቸውን ቀጥለው ኢትዮጵያ የማንንም እጅና እርዳታ ሳታይ አንድም ሆነ ሁለት ዶላር ቢልኩ አገራቸውን ይጠቅማሉ ብለዋል፡፡ 

በተደረገውም ነገር ሁሉ አመስግነዋል፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ