ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ጥቅምት 17፣ 2014- የአሜሪካ መንግሥታዊ የጤና ኮሚቴ የፋይዘር ባዮቴክ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባትን እድሜያቸው ከ5 እስከ 11 ዓመት ለሆኑ ሕፃናት እንዲሰጥ ወሰነ

የአሜሪካ መንግሥታዊ የጤና ኮሚቴ የፋይዘር ባዮቴክ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባትን እድሜያቸው ከ5 እስከ 11 ዓመት ለሆኑ ሕፃናት እንዲሰጥ ወሰነ፡፡

የአገሪቱ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር መሥሪያ ቤት ከፍተኛ ባለሙያዎች ሕፃናቱ የፋይዘር ክትባትን እንዲከተቡ መደገፋቸውን ቢቢሲ ፅፏል፡፡

በመስከረም ወር ኩባንያው ክትባቱን በዚህ የእድሜ እርከን ለሚገኙ ሕፃናት ሰጥቼ ውጤታማ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ብሎ እንደነበር መረጃው አስታውሷል፡፡

በአሁኑ ወቅት አሜሪካ ዕድሜያቸው 12 እና ከዛም በላይ ለሆነ አዳጊዎች ክትባቱን እየሰጠች ነው ተብሏል፡፡

አሁን እድሜያቸው ከ5 እስከ 11 ላሉ ሕፃናት ክትባቱ እንዲሰጥ በፍተኛ የጤና ኮሚቴው ቢወሰንም የበሽታዎች መከላከያ እና መቆጣጠሪያ መሥሪያ ቤቱን ይሁንታ እንደሚሻ ታውቋል፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ