ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ጥቅምት 17፣ 2014- የዓለማችን አገሮች የአየር ለውጥ ተፅዕኖውን ለመገደብ ቃል በመግባት ላይ የሚገኙት ሁሉ ከሚጠበቅባቸው ያነሰ ነው ተባለ

የዓለማችን አገሮች የአየር ለውጥ ተፅዕኖውን ለመገደብ ቃል በመግባት ላይ የሚገኙት ሁሉ ከሚጠበቅባቸው ያነሰ ነው ተባለ፡፡

ቀደም ሲል የአየር ለውጥ ተፅዕኖ መግቻው የሙቀት መጠን ጭማሪው ከቅድመ ኢንዱስትሪ አብዮት በፊት ከነበረው ጋር ሲመሳከር ከ1.5 ዲግሪ ሴልሺየስ መብለጥ እንደሌለበት የሚጠይቅ ነበር፡፡

ይሁንና በአሁኑ የአገሮች አዝማሚያ የአለም ሙቀት መጠን ከ2.7 ዲግሪ ሴሊሺየስ በላይ ተጨማሪ ሙቀት እንዲመዘገብ ሊያደርግ እንደሚችል ቢቢሲ ፅፏል፡፡

የ2.7 ዲግሪ ሴሊሺየስ ጭማሪው እጅግ ከፍተኛ አሉታዊ ውጤት እንደሚኖረው የአለም ሜቴዎሮሎጂ ድርጅት እወቁልኝ ብሏል፡፡

ሰሞኑን በስኮትላንድ ግላስጎው አለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ይከፈታል፡፡

ከዚህ አስቀድሞ የተለያዩ አገሮች ለአየር ለውጥ ተፅዕኖ ማቃለያ የተለያዩ ቃሎች እየገቡ መሆኑን መረጃው አስታውሷል፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ