ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ግንቦት 4፣ 2013- ኢትዮጵያዊው ጤፍ በደቡብ አፍሪካ 5 ከተሞች በስፋት እየተመረተ ለውጪ ገበያ እየቀረበ ነው ተባለ

ኢትዮጵያዊው ጤፍ በደቡብ አፍሪካ 5 ከተሞች በስፋት እየተመረተ ለውጪ ገበያ እየቀረበ ነው ተባለ፡፡
 
ትውልድ ኢትዮጵያዊውን ጤፍ በስፋት እያመረተ ለውጪ አገር ገበያ የሚያቀርበው አይከንስ ፉድስ ኢንተርናሽናል የተባለ የደቡብ አፍሪካ ኩባንያ መሆኑን ሰምተናል፡፡ 

ኩባንያው እጅግ ዘመናዊ በሆነው መንገድ ጤፍን በደቡብ አፍሪካ ፍሪታውንና በሌሎች አራት አካባቢዎች እያመረተ 90 በመቶ ምርቱን ለውጪ አገር ገበያ እያቀረበ መሆኑን የተናገሩት በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ መንግስት ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ናቸው፡፡ 

ሰርገኛ፣ ማኛ፣ ቀይና ጥቁር ጤፍ በያይነቱ በዘመናዊ መንገድ እያመረተና የምርቱን 10 በመቶ ገለባ ለከብቶች መኖ አስቀርቶ 90 በመቶውን ለውጪ አገር ገበያ የሚልከው ኩባንያው ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ እንዲሰራ ንግግር እየተደረገ መሆኑን አምባሳደር ሽፈራው ለሸገር ነግረዋል፡፡

በትውልድ አገሩ በብዙ ድካም የሚመረተው ጤፍ የድካሙን ያህል ውጤት ያለመጣና ለዘመናት ከሄደበት የበሬ ጫንቃ እርሻ እንዲላቀቅ ኩባንያው ኢትዮጵያዊውን ጤፍ ውጤታማ እንዲያደርግ ንግግር መድረጉን ሰምተናል፡፡ 

ከጆሃንስበርግ ከተማ በ60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በጀስቲስ መሐመድ ጎዳና ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሸገር ከአምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም ጋር ባደረገው ውይይት ኤምባሲው ጤፍን በዘመናዊ መንገድ ከሚያመርተው ኩባንያ በተጨማሪ ሌሎች ግዙፍ የደቡብ አፍሪካ የንግድ ተቋማትን ለማምጣት እየተሰራ መሆኑን ሰምተናል፡፡

ደቡብ አፍሪካ ከኢትዮጵያ ጋር እስትራቴጂካዊ ወዳጅነት አላት ያሉት አምባሳደሩ በቅርቡ የደቡብ አፍሪካን 25 በመቶ የወተት ምርት የሚያቀርበው ኩባንያ ስራውን ወደ ኢትዮጵያ እንዲያመጣና እንዲያስፋፋ በአምባሳደር ሽፈራው በኩል ግብዣ ተደርጎለት አገር ቤት መጥቶ ነገሮችን መመልከቱን ለሸገር ነግረዋል፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ