ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ግንቦት 4፣ 2013- በሱዳኗ ርዕሰ ከተማ ካርቱም ለተቃውሞ አደባባይ ከወጡት መካከል ሁለቱ በፀጥታ ሀይሎች ተተኩሶባቸው መገደላቸው ተሰማ

በሱዳኗ ርዕሰ ከተማ ካርቱም ለተቃውሞ አደባባይ ከወጡት መካከል ሁለቱ በፀጥታ ሀይሎች ተተኩሶባቸው መገደላቸው ተሰማ፡፡

ሰልፈኞቹ አደባባይ የወጡት ከ2 አመታት በፊት በዛው ለተቃውሞ ሰፍረው በነበረ ሰልፈኞች ላይ በፀጥታ ሀይሎች በተወሰደ እርምጃ ያለቁትን ሰዎች ለመዘከር እንደሆነ አሶሼትድ ፕሬስ ፅፏል፡፡

የአሁኖቹ ሰልፈኞች አደባባይ የወጡት ያን ጊዜ ላለቁት ሰልፈኞች ፍትህ ለመጠየቅ ጭምር ነው ተብሏል፡፡

ሰልፈኞቹ ከ2 ዓመታት በፊት በሰልፈኞች ላይ እልቂት የፈፀሙት ተጠያቂ ይሁኑልን ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

ይሁንና ምላሹ ጥይት እና አስለቃሽ ጋዝ እንደሆነባቸው በመረጃው ተጠቅሷል፡፡
በአሁኑ የፀጥታ ሀይሎች እርምጃ ከተገደሉት ሌላ 15 ያህሉ ደግሞ አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡ 

ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ በሰልፈኞች ላይ ጥይት መተኮስ ተቀባይነት የሌለውና በሕግ የሚያስጠይቅ ወንጀል ነው ማለታቸው ደግሞ ቢቢሲ ፅፏፏል፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ