ማስታወቂያ

programs top mid size ad

የሸገር ልዩ ወሬ/ የዓይነ ሥውር እናት እና ልጆች ነገር

በአዲስ አበባ፣ ቦሌ ሚካዔል አካባቢ፣ ግብርና ሰፈር ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ውዳሴ የዓይን ብርሃናቸውን ያጡት ቀስ በቀስ ነበር፡፡ ባለቤታቸው የዓይን ብርሃናቸው እንዲመለስ በርካታ የሕክምና ተቋማት ወስደዋቸው ነበር አልተሳካም እንጂ፡፡

ከዚህ በኋላ በቀጠሉት ዓመታት ሁለት ልጆችን አከታትለው ሲወልዱ የባሰው መጣ - ሁለቱም ልጆች የዓይን ብርሃናቸውን አጥተው ነው የተወለዱት፡፡

ቤተሰቡን ይደግፉ የነበሩት አባወራ ለንግድ ሥራ በሄዱበት በቢጫ ወባ ሕመም ሲሞቱ ወይዘሮዋ ሰማይ ተደፋባቸው፡፡ ልጆቹን ይዘው ጎዳና ወጡ፡፡ ኋላ ላይ በበጎ ሰዎች ርብርብ እንደምንም የቀበሌ ቤት አግኝተው በሰዎች እርዳታ ኑሮን ይገፉ ጀመር፡፡

አሁን የመጀመሪያ ልጃቸው 26 ዓመቱ ነው፤ ሁለተኛው እና የኦቲዝም ተጠቂው ደግሞ 22 ዓመቱ ነው፡፡

ይህ የኮሮና ወረርሽኝ ሲመጣ ደግሞ ለዓይነ ሥውር እናት እና ልጆቹ ጊዜውን የከፋ አድርጎባቸዋል ይለናል የሸገር ልዩ ወሬ አዘጋጁ ወንድሙ ኃይሉ…ሙሉ ታሪካቸውን ያዳምጡ…

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ