ማስታወቂያ

የሸገር ወሬዎቻችን

Sort by
ነባሪ
Post Date
2021-07-22
በአልጄሪያ በኮሮና ቫይረስ ስርጭት መዛመት የተነሳ የእስትንፋስ መደገፊያ (የኦክስጂን) እጥረቱ እየተባባሰ ነው ተባለ፡፡ ለችግሩ መፍትሄ የሚፈለግ አጣዳፊ ብሔራዊ ኮሚቴ እንደተሰየመ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ የኦክስጂን ፍላጎቱ ከእለት እለት እየጨመረ ሲሆን አገሪቱ ይሄን ፍላጎት የሚመጥን ኦክስጂን እንደማታመርት በመረጃው ተጠቅሷል፡፡ እስከ ትናንት ምሽት በነበረው የ24 ሰዓታት ጊዜ 1,300 ያህል ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ታውቋል፡፡ በጊዜው በበሽታው የ23 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ በአልጄሪያ እስካሁን የኮሮና ቫይረስ መከላከያ የተከተቡት 3 በመቶ ያህሉ ብቻ ናቸው ተብሏል፡፡ አገሪቱ ሩሲያ ስሪቱን ስፑትኒክ 5 እና የቻይናው ሲኖ ፋርም ክትባቶች እዚያው የማምረት እቅድ እንዳላት መረጃው አስታውሷል፡፡
2021-07-22
በናይጄሪያ የደቡባዊ ምዕራቧ ዩርባ ግዛት የመገጠል አቀንቃኝ ነው የተባለ ግለሰብ በጎረቤት ቤኒን መያዙ ተሰማ፡፡ የዩርባ ግዛትን ከናይጀሪያ ለመነጠል ሲያሴር ቆይቷል ተብሎ ቤኒን ውስጥ የተያዘው ስንዴይ ኢግቦሆ የተባለ ግለሰብ እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ ሰውየው መያዙን የህግ አማካሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ የናይጄሪያ መንግሥት ግን በዚህ ረገድ የሰጠው ማረጋገጫ የለም፡፡ እንደሚባለው ሰውየው የተያዘው ከቤኒን ወደ ጀርመን ለመብረር በተሰናዳበት ወቅት ነው፡፡ የናይጄሪያ ፖሊስ ከጥቂት ሳምንት በፊት በግለሰቡ የዩርባ ግዛት መኖሪያ ቤቱ ባደረኩት አሰሳ በርካታ የጦር መሳሪያዎች ተከማችተው አግኝቻለሁ ማለቱን መረጃው አስታውሷል፡፡
2021-07-21
በአፍጋኒስታን ርዕሰ ከተማ ካቡል ወደሚገኘው ቤተ መንግሥት 4 ሮኬቶች እንደተተኮሱበት ተሰማ፡፡ ሮኬቶቹ ወደ ካቡል ቤተ መንግሥት የተተኮሱት ፕሬዝዳንት አሽራፍ ጋኒ የትናንቱን የአረፋ በዓል አስመልክተው ለህዝብ መልዕክት ከማስተላለፋቸው አስቀድሞ እንደሆነ አሶሼትድ ፕሬስ ፅፏል፡፡ ሮኬቶቹ ያደረሱት አንዳችም ጉዳት የለም ተብሏል፡፡ የአፍጋኒስታኑ የአይ ኤስ ፅንፈኛ ቡድን ሮኬቶቹን የተኮስኩት እኔ ነኝ ማለቱ ተሰምቷል፡፡ በአፍጋኒስታን ሰፍረው የቆዩ የአሜሪካ እና የሰሜና አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅተ (ኔቶ) አጋሮቿ ወታደሮች በአብዛኛው ለቀው መውጣታቸው የአገሪቱን የፀጥታ ስጋት እያባባሰው ነው፡፡ ታሊባኖችም ተጨማሪ ግዛቶችን በመያዙ ገፍተውበታል ተብሏል፡፡
2021-07-21
በወታደራዊ የመንግሥት ግልበጣ ስልጣን የጨበጡት የማሊው ፕሬዝዳንት አሲሚ ጎይታ ትናንት በኢድ አል አድሃ ፀሎት ወቅት የስለት ጥቃት ተቃጣባቸው፡፡ ጎይታ ትናንት ለፀሎት ባማኮ በሚገኘው ታላቁ መስጊድ በተገኙበት ወቅት 2 ግለሰቦች ጥቃት ሊሰነዝሩባቸው ሞክረው እንደነበር ቢቢሲ አስታውሷል፡፡ ከሁለቱ ጥቃት ሰንዛሪዎች አንዱ ስለት ይዞ ነበር ተብሏል፡፡ ይሁንና  ያሰቡትን ጥቃት ሳይፈፅሙ ቀርተው ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል፡፡ አሲሚ ጎይታ የተቃጣባቸውን ጥቃት፤ የሚያጋጥም ነው ሲሉ ማቃለላቸው ተሰምቷል፡፡ ምንም ችግር አልተፈጠረም ደህና ነኝ ሲሉም ተናግረዋል፡፡
2021-07-21
የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መርጃ ድርጅት (ዮኒሴፍ) በሊቢያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መባባሱ በእጅጉ አስግቶኛል አለ፡፡ በሊቢያ የተለያዩ ግዛቶች የወረርሽኙ መዛመት በተለያየ መጠን እየከፋ መምጣቱን ቢቢሲ ፅፏል፡፡ በምዕራብ የአገሪቱ  ክፍል በ3 እጥፍ ያህል በደቡብ ደግሞ 5 እጥፍ ገደማ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኙ መጨመሩ ታውቋል፡፡ በሊቢያ 220,000 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ይፋዊ የጤና መረጃው ያሳያል፡፡ እሁድ እለት በአንድ ቀን ከ6000 በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ታውቋል፡፡ ይህም ወረርሽኙ ከተቀሰቀሰ በሊቢያ በአንድ ቀን በኮሮና ቫይረስ በመያዝ የምንግዜውም ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡
2021-07-21
በማዕከላዊ ቻይና ሄናን ግዛት የተከሰተ የጎርፍ አደጋ በጥቂቱ 12 ሰዎችን መግደሉ ተሰማ፡፡ በተለይም የዜንግዙ ከተማ አደጋው የከፋባት እንደሆነች ቢቢሲ ፅፏል፡፡ በጎርፍ ምክንያት 12 ሰዎች የሞቱት በዚያ መሆኑ ታውቋል፡፡ ከሄናን ግዛት የጎርፍ አደጋው ከፍተኛ ስጋት ካለባቸው ስፍራዎች ከ10,000 በላይ ሰዎችን ከአደጋው ወደሚጠበቁባቸው ስፍራዎች ማውጣት ተችላል ተብሏል፡፡ በሺንግዙ ጎዳናዎች እና የምድር ውስጥ ለውስጥ የባቡር አገልግሎት መስጫዎች በጎርፍ እና በውሃ ሙላት መጥለቅለቃቸው ተሰምቷል፡፡ በዚያ የተሳፈሩባቸው ባቡሮች ጎርፍ የተጥለቀለቁባቸው መንደኞች በየመቀመጫዎቻቸው ላይ ለመቆም ተገድደዋል ተብሏል፡፡ የአደጋ ተከላካይ ሰራተኞችም እነዚህን ሰዎች የተለያዩ መላዎችን በመጠቀም እያወጧቸው መሆኑ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡ የሄናን ግዛት ጎርፍ ሰሞኑን የሚጥለውን ዶፍ ዝናብ የተከተለ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ በግዛቲቱ ባለፉት 3 ቀናት የጣለው ዶፍ ዝናብ ያልተለመደ ነው ተብሏል፡፡ በመጪዎቹ 24 ሰዓታትም ዶፍ ዝናቡ እንደሚቀጥል የአየር ተጨማሪ ያንብቡ
2021-07-19
ድንቃድንቅ
2021-07-19
በዚምባብዌ መንግሥታዊው የእህል ግዢ ቦርድ ሰራተኞቹ በሙሉ በአፋጣኝ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ እንዲከተቡ አዘዛቸው፡፡ ከወር ባልበለጠ ጊዜ የኮሮና ቫይረስ መከላከያውን ተከትበው እንዲያሳውቁት ማዘዙ ብሉምበርግ ፅፏል፡፡ መንግስታዊው የእህል ግዢ ቦርድ ትዕዛዙን ያስተላለፈው 150 ያህል ሰራተኞቹ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ቦርዱ በአገሪቱ ብቸኛው የበቆሎ ምርት ገዢ እንደሆነ መረጃው አስታውሷል፡፡ የማይከተቡ ሰራተኞች ከተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ በኋላ ስራ አለን ብለው እንዳይመጡበት በብርቱ ማስጠንቀቁ ተሰምቷል፡፡ በዚምባብዌ እስካሁን ከ82,600 በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ እንደተያዙ የጤና መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
2021-07-19
አሜሪካ በኦስትሪያ ቬየና የሚገኙ ዲፕሎማቶቿ እና የኤምባሲ ሰራኞች በጅምላ መታመማቸው ምንድነው ነገሩ እያሰኛት መሆኑ ተሰማ፡፡ ክስተቱንም በብርቱ እየመረመረችው መሆኑን ቢቢሲ ፅፏል፡፡ ከ20 በላይ ዲፕሎማቶች እና የኤምባሲው ሰራተኞች አካላዊ መዛል እና ብርቱ የድካም ስሜት፣ ሚዛንን አለመጠበቅ እና የማድመጥ ችሎታ መቀነስ እንዳጋጠማቸው ተጠቅሷል፡፡ ከ4 ዓመታት በፊትም በኩባ ሐቫና የሚገኙ የአሜሪካ እና የካናዳ ዲፕሎማቶች ተመሳሳይ ችግር ሲገጥማቸው መቆየቱን መረጃው አስታውሷል፡፡ ይሄ ዓይነቱ የጤና እክል ከጨረራ ጥቃት ጋር ተያይዞ ሲነሳ ቆይቷል፡፡ የኩባ መንግሥት ግን ከደሙ ንጹህ ነኝ ነበር ምላሹ፡፡ የኦስትሪያዋ ቬየና ከአለማችን የዲፕሎማሲ መናኸሪያዎች አንዷ ተደርጋ ትቆጠራለች፡፡
2021-07-17
በናይጄሪያ 1 ከፍተኛ የጦር መኮንን ተተኩሶባቸው ተገደሉ፡፡ ሜጄር ጄኔራል ሐሰን አህመድ ተተኩሶባቸው የተገደሉት ሎኮጃ ከተባለችዋ ከተማ ወደ መዲናዋ አቡጃ በማምራት ላይ በነበሩበት ወቅት እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ የጦር መኮንኑ የተገደሉት በታጣቂዎች በተከፈተባቸው ተኩስ ነው ቢባልም የታጣቂዎቹ ማንነት አልተጠቀሰም፡፡ የናይጄሪያ ጦር ሀይል በሜጄር ጄኔራሉ ላይ የተፈፀመውን ግድያ በእጅጉ አሳዛኝ ነው ብሎታል፡፡ በናይጀሪያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አጠቃላይ የፀጥታ እና የደህንነት ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱ ይነገራል፡፡ በሜጄር ጄኔራል ሐሰን አህመድ በምን ምክንያት ግድያ እንደተፈፀመባቸው ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም ተብሏል፡፡