ማስታወቂያ

የሸገር ወሬዎቻችን

Sort by
ነባሪ
Post Date
2021-11-27
አዋሽ ባንክ ከተመሠረትኩ ጀምሮ እንደ ዘንድሮ አላተረፍኩም አለ፡፡  ባንኩ የዘንድሮው ትርፌ በኢትዮጵያ የግል ባንኮች ታሪክ የመጀመሪያው እንደሆነ መናገር እችላለሁ ብሏል፡፡ አዋሽ ባንክ በዘንድሮ የሥራ ዘመን የባንኩ ያልተጣራ ትርፍ ለብድር ከሚይያዘው መጠባበቂያና ከታክስ በፊት 5.58 ቢሊዮን ብር ነው ብሏል፡፡ ለብድር የሚይያዘው መጠባበቂያ ተቀንሶ ከታክስ በፊት ያገኘው ያልተጣራ ትርፍ 4.8 ቢሊዮን ብር መኾኑን ባንኩ ተናግሯል፡፡ ትርፉ ከአምናው የሥራ ዘመን ጋር ሲነጻጸር የ1.2 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው መሆኑን ሰምተናል፡፡ ባንኩ ያገኘሁት ትርፍ በግል ባንኮች ታሪክ የመጀመሪያው እንደሆነ መረጃዎች ነግረውኛል ብሏል፡፡ የአዋሽ ባንክ በዘንድሮ የሥራ ዘመን 87.5 ቢሊዮን ብር ብድር ለቅቄያለሁ ብሏል፡፡ በዘንድሮ ዓመት ብቻ የባንኩ የተከፈለ ካፒታል የ2.31 ቢሊዮን ብር ወይም የ40 በመቶ ዕድገት በማሳየት 8.2 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡ የባንኩ የተከፈለ ካፒታል በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ 12 ቢሊዮን ብር ሊደርስ እንደሚችል ተጨማሪ ያንብቡ
2021-11-27
ዘመን ባንክ የባለፈው በጀት ዓመት ካቀድኩት በላይ ትርፍ በትርፍ የሆንኩበት ነው አለ።  ባንኩ በ2013 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 1.2 ቢሊዮን ብር ትርፍ አግኝቻለሁ ብሏል።  ትርፉ በእቅድ ተይዞ ከነበረው ጋር ሲተያይ የ16.2 በመቶ፤ ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ደግሞ የ30 በመቶ ብልጫ አለው ተብሏል። በዛሬው ዕለት ዓመታዊ የባለ አክስዮኖች ዓመታዊ ጉባዔ እያካሄደ የሚገኘው ዘመን ባንክ፣ የተከፈለ ካፒታሉ 2 ቢሊዮን 749 ሚሊዮን ብር መድረሱን ተናግሯል። አጠቃላይ ሀብቱ 25.2 ቢሊዮን ብር፤ የሰጠው ብድር 14 ቢሊዮን ብር መድረሱን ተናግሯል። የባንኩ የተበላሹ ብድሮች ክምችት 2.25 በመቶ ላይ ይገኛል ተብሏል። ዘመን ባንክ በ2013 በጀት ዓመት ከሰጠው ዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎት 418 ሚሊዮን ዶላር አግኝቻለሁ  ያለ ሲኾን፣ ብሔራዊ ባንክ፣ ባንኮች ከሚያገኙት የውጪ ምንዛሪ 30 በመቶ ለባንኩ እንዲያስገቡ ባወጣው መመሪያ መሠረት 127 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማድረጉን ተናግሯል።
2021-11-27
መማር ሲኖርባቸው አንዳንዶቹ በሥራ ሌሎችም ቦዝነው በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ከምናያቸው ህፃናት መካከል ከተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች የሚመጡ ጭምር ይገኙበታል፡፡ በተለይ ከደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢ ፈልሰው የሚመጡ ህፃናት ያለ ዕድሜያቸው በተለያዩ ሥራዎች ላይ ተሰማርተው ጎዳና ላይ ይውላሉ፡፡ አንደኛ ክፍል ከሚገቡ 1000 ሕፃናት መካከል 8ተኛ ክፍል የሚደርሱት ከ5ቱ አንዱ ብቻ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይህን ችግር ለመፍታት ምን መደረግ አለበት?
2021-11-27
ህገ መንግሥቱ ለዜጎች ከሰጣቸው መብቶች መካከል መረጃ የማግኘት መብት አንዱ ነው፡፡ ኢትዮጵያ አሁን በጦርነት ላይና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ እንደመሆኗ እንዲህ ባለው ወቅት የመረጃ ነፃነት መብት እስከምን ድረስ ይፈቀድ ይሆን ?
2021-11-27
ባለፈው ዓመት ጀምሮ እየተካሄደ ያለውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት አስታከው እንደ አሜሪካ ያሉ እና አንዳንድ የምዕራባውያን ሃገራት መልኩን እየቀያየሩ ጫና ማሳደራቸውን እንደቀጠሉ ነው፡፡ መንግሥት ጫናው ለመቋቋም እያደረገ ካለው ጥረት ባሻገር ሸገር ያነጋገራቸው ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ተፅዕኖውን ለማርገብ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡  
2021-11-27
ትናንት በአዲስ አበባ የፈረንሳይ ለጋሲዎን አካባቢ ነዋሪዎች በበጎ ፈቃድ ለመከላከያ ሰራዊት ስንቅ ሲያዘጋጁ ውለዋል፡፡ በሶ፣ እንጀራ፣ ሽሮና በርበሬ እንዲሁም ሌሎች እንደ መኮሮኒ፣ ፓስታ እና ዘይት ያሉ ምርቶችን ወደ ግንባር ለመከላክ ሲያዘጋጁ ተመልክተናል፡፡ ጎን ለጎን ለሰራዊቱ ደም ሲለግሱም ውለዋል፡፡ የነዋሪዎቹን ለመከላከያ ሰራዊቱ ደጀን ለመሆን የተከወነውን ስራ ሸገር ተመልክቷል፡፡
2021-11-26
የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይን ማስለቀቅ ለተጨማሪ 3 ወራት ክልክል እንደኾነ ይቆያል ተባለ።  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከዛሬ ሕዳር 17፣ 2014 ጀምሮ ለቀጣዮቹ 3 ወራት የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይን ማስለቀቅ ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑን ተናግሯል። የከተማ አስተዳደሩ የኮሚኒኬሽን ቢሮ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጠው መግለጫ፣ "የአገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ፣ እንዲሁም የመዲናችንን ነዋሪ የኑሮ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይን ከተከራየበት ቤት ማስለቀቅ እንደማይቻል ውሳኔ አስተላልፎ እንደነበር አስታውሷል፡፡  በዛሬው ዕለትም፣ "ያለንበት ወቅት አገርን ከተጋረጠባት የኅልዉና አደጋ የማዳን መሆኑን በመጥቀስ፣ ውሳኔው ለቀጣይ ሦስት ወራት ባለበት እንዲጸና ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል" ብሏል፡፡  
2021-11-26
የመከላከያ ሠራዊት ቡርቃንና በባቲ ከተማ ዙሪያ ያሉ ተራሮችን መቆጠጠሩን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ተናገረ። የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ምሽቱን ይፋ ባደረገው መግለጫ፣ "በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁርጠኝነት የተነቃቃው ጀግናው ሠራዊታችን በባቲ ካሳጊታ ግንባር ሲደረግ በነበረው ውጊያ ካሳጊታን አስቀድሞ ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ ያወጣ ሲሆን፣ ወደፊት በመገስገስ ቡርቃን እና በባቲ ከተማ ዙሪያ ያሉ ተራሮችን ተቆጣጥሮ ወደ ባቲ ኮምቦልቻ እየገሠገሠ ነው" ብሏል። በተጨማሪም ሰራዊቱ "በአፋር ክልል፣ በጭፍራ ግንባር ጪፍቱን፣ የጭፍራ ከተማን እና አካባቢውን ከወራሪው ነጻ አውጥቶ ወደፊት በመገስገስ ላይ ነው" ብሏል።  የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት በዚሁ መግለጫው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መላውን የፀጥታ ኃይል ራሳቸው በመምራት የኅልውና ዘመቻውን ከዳር ለማድረስ ቃል በገቡት መሠረት በግንባር ተገኝተው ቃላቸውን ተግባራዊ እያደረጉ ይገኛሉ ብሏል።  
2021-11-26
የአርሲ ዞን ፖሊስ ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎችን እየያዝኩኝ ነው አለ፡፡
2021-11-26
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአሸባሪነት የተፈረጀውን ሕወሃትን የሚደግፉ አባላቱን አስጠነቀቀ፡፡