ማስታወቂያ

የሸገር ወሬዎቻችን

Sort by
ነባሪ
Post Date
2021-07-23
በትግራይ ክልል በሚገኙት በማይ-ዓይኒ እና ሀዲ ሐሩሽ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች  ውስጥ ያሉ ኤርትራዊያን ስደተኞች ሁኔታ አስከፊ ወደ ሆነ ደረጃ በመሸጋገሩ እጅግ አሳሳቢ ሆኗል ተባለ፡፡ ህወሓት የስደተኛ መጠለያ ጣቢያ መሰረተ ልማቶችን ለወታደራዊ አገልግሎት እያዋለ ነው ተብሏል፡፡ ይህን ያለው የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ነው፡፡ ኤጀንሲው ለሸገር በላከው መግለጫ ህወሓት የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ወዳሉባቸው አካባቢዎች መግባቱን ተከትሎ እስካሁን ድረስ ቢያንስ 6 ስደተኞች እንደተገደሉ የሚያሳዩ መረጃዎች ተገኝተዋል ብሏል፡፡ የህወሓት ታጣቂ ቡድን አለም አቀፉን የሰብአዊ መብት ህግ በመጣስ በስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ከባድ መሳሪያዎች መትከሉን የተናገረው የኤጀንሲው መግለጫ ቀጣይነት ያለው የታጣቂ እንቅስቃሴ እና አልፎ አልፎም የተኩስ ድምፅ በመሰማት ላይ ይገኛል ብሏል፡፡  ከዚህ በተጨማሪም ለሰብአዊ አገልግሎት እንዲውል የተዘጋጁና የተቋቋሙ ጤና ጣቢያዎችን ጨምሮ አምቡላንሶችና መሰረተ ልማቶችን የሕወሓት ቡድን ተጨማሪ ያንብቡ
2021-07-23
የሐረር ከተማ ነዋሪዎች በወር ምን ያህል ውሃ እንደጠጡ እና እንደተጠቀሙ ለማወቅ ከእንግዲህ በር አይንኳኳባቸውም ተባለ። የሐረር የውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን በየወሩ የከተማው ነዋሪ የተጠቀመውን ውሃ ለመቁጠር በየቤቱ ደጅ አልጠናም ደንበኞች ለተጠቀሙበት የውሃ ፍጆታ በየወሩ በእጅ ስልካቸው እነግራቸዋለው ማለቱን ሰምተናል፡፡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እና የክልሉ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን የክፍያ አሰራሩን ለማሻሻል ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን ተናግረዋል። ኤጀንሲው የሐረር ነዋሪዎች ለተጠቀሙት ውሃ ወርሃዊ ክፍያ ለመፈፀም የተሻለ አሰራር እንደተከናወነ ተናግሯል። ጥሬ ገንዘብ እንዳይዘዋወር የክፍያ አገልግሎቱን ከአንበሳ ባንክ ጋር አንበሳ ሄሎካሽ በተባለ የሞባይል ወኪል ማከናወን ይቻላል ተብሏል። ደንበኞች ከዚህ በፊት እንደሚያደርጉት ለክፍያ መሰለፍ አይኖርባቸውም። የአገልግሎት ክፍያ ስርዓቱ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) በአንበሰ ኢንተርናሽናል ባንክ እና የሄሎ ካሽ አገልግሎት አቅራቢነት ተቀናጅቷል ተብሏል፡፡
2021-07-23
በአዲስ አበባ ከተማ በትራፊክ አደጋ ሳቢያ ይደርስ የነበረውን ሞት 13 በመቶ በቀነስ መቻሉን የከተማዋ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ተናገረ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ በትራፊክ ግጭት ምክኒያት ከሚደርሰው የሞት፣ የአካል ጉዳት እና የንብረት ውድመት ባሻገር ለከፋ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እያስከተለ ይገኛል። ኤጀንሲው የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የሚያስችል የመንገድ ደህንነት ስትራቴጂን በመንደፍ  ወደ ትግበራ መግባቱን ተናግሯል፡፡  ይሀው የመንገድ ደህንነት ስትራቴጂ ተግባራዊ በመደረጉ በየዓመቱ በትራፊክ ግጭት ሳቢያ  የሚደርሰውን ሞት እና የአካል ጉዳት ለመቀነስ አግዟል ተብሏል፡፡  በተጠናቀቀው የ2013 በጀት ዓመት ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው በ13 በመቶ በመቀነስ  የ59 ሰዎችን ህይወት ከሞት መታደግ ተችሏል ብሏል ኤጀንሲው። በዘንድሮም በከተማዋ  በትራፊክ ግጭት አደጋ የደረሰው ሞት 389 ሲሆን በ2012 በጀት  ዓመት የተመዘገበው  የሞት መጠን 448 ነበር ተብሏል፡፡  በተመሳሳይ ሁኔታ በትራፊክ ግጭት ከባድ የአካል ተጨማሪ ያንብቡ
2021-07-23
ኢትዮጵያ በ2013 በጀት ዓመት ከ3.6 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ከወጪ ንግድ ማግኘቷ ተነገረ፡፡ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ያለፈውን በጀት ዓመት የወጪ ንግድ አፈጻጸም አስመልክተው ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸው እንዳሉት የተገኘው ገቢ ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት የ592 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ብልጫ አለው፡፡ የግብርናው ዘርፍ 2.47 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በማስመዝገብ ከአጠቃላይ የወጪ ንግድ ገቢው 68 በመቶ ድርሻ መያዙን ጠቅሰዋል፡፡ ከግብርና ምርቶችም ቡና 25 በመቶውን በመሸፈን የአንበሳውን ድርሻ ይዟል ተብሏል፡፡  አበባ 13 በመቶ፣ የቅባት እህሎች 9 በመቶ፣ ጫት 11 በመቶ እና የጥራጥሬ ሰብሎች 6 በመቶ ድርሻ መያዛቸውም ታውቋል፡፡ አምራች ዘርፉ ደግሞ 390 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በበጀት አመቱ ለሀገራችን አስገኝቷል ብለዋል ፤ ከማዕድን ዘርፍ የተገኘው 668 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ከታቀደውም የበለጠ እንደሆነ ሚኒስትር ዴኤታው በመግለጫቸው ተናግረዋል ተጨማሪ ያንብቡ
2021-07-23
41,488 ዜጎች ከሳውዲ አረቢያ መመለሳቸው ተሰማ፡፡  አስፈላጊው ድጋፍም እየተደረገላቸው ነው፡፡  
2021-07-23
በመላው አለም 1 ሚሊየን ጥቁሮችን ቢሊየነር ለማድረግ ያሰበው ‘ፐርፐዝ ብላክ’ በነገው እለት በኢትዮጵያ ይፋ ይሆናል ተባለ፡፡ 
2021-07-23
እስራኤል ታዛቢ ሀገር በመሆን የአፍሪካ ህብረትን በድጋሜ መቀላቀሏ ተሰማ፡፡ የእስራኤል ታዛቢነት በመደበኛ ደረጃ ከአፍሪካ ህብረት ጋር መመስረቱ፤ ሁለቱ አካላት በጋራ ኮቪድ-19 ን ለመዋጋት ፣ ፅንፈኛ ሽብርተኝነት በመላው አህጉሪቱ እንዳይስፋፋ ለመከላከል እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ መተባበር የሚችሉባቸዉን ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል ተብሏል። በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ እ.ኤ.አ ከ2001 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአፍሪካ ህብረት በታዛቢነት የሹመት ደብዳቤያቸውን ያቀረቡ የመጀመሪያዉ አምባሳደር ሆነዋል፡፡ 55 አባል ሃገራት ያሉት የአፍሪካ ህብረት፤ በአፍሪካ አህጉር ዉስጥ ትልቁ ተቋም ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ያኢር ላፒድ “ይህ ለእስራኤል እና ለአፍሪካ ግንኙነቶች ትልቅ  የደስታ ቀን ነው... በአፍሪካ አህጉር እና ከድርጅቱ አባል አገራት ጋር የምናደርገውን  እንቅስቃሴ ለማጠናከር ይረዳናል” ሲል መናገራቸውን በኢትዮጲያ ኤምባሲ ተናግሯል፡፡ እስራኤል ከ 46 የአፍሪካ አገራት ጋር ግንኙነት ያላት ሲሆን በንግድ፣ ተጨማሪ ያንብቡ
2021-07-23
በአማራ ክልል የኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተፀመ ዝርፊያ እና ጥቃት ከ47 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል ተባለ፡፡ 
2021-07-23
አማኑኤል ሆስፒታል ዛሬ የጤና ባለሙያዎቹንና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞቹን አመሰገነ፡፡ 
2021-07-23
ቻይናዊው ባለሀብት ጃክ ማ አፍሪካዊያን ስራ ፈጣሪዎችን ለማገዝ ‘’የአፍሪካ ቢዝነስ ጀግኖች’’ በሚል የሰየሙት ውድድር በየዓመቱ ይካሄዳል፡፡  ከዘንድሮው ተወዳዳሪዎች የመጨረሻዎቹ 50ዎቹ ውስጥ 2 ኢትዮጵያዊያን መካተት ችለዋል፡፡  ንጋቱ ሙሉ ሀምሳዎቹ ውስጥ ከተካተቱት አንደኛው የሆነውን የዛይ ራይድ መስራችና ባለቤት አቶ ሀብታሙ ታደሰ አነጋግሮ የሚከተለውን አዘጋጅቷል፡፡