የአገር ውስጥ ወሬ

ጥቅምት 10፣ 2014- ስመ ጥሩው ድምፃዊ ቴዎድሮስ ታደሰ በአገር ቤት ያሉ የኪነ ጥበብ ባለሙያና ሌሎችም የሚገባውን እያደረጉ እንደሆነ ሰምተናል

በሀገረ አሜሪካ ጥቃት ለደረሰበት ስመ ጥሩው ድምፃዊ ቴዎድሮስ ታደሰ በአገር ቤት ያሉ የኪነ ጥበብ ባለሙያና ሌሎችም የሚገባውን እያደረጉ እንደሆነ ሰምተናል፡፡

ሸገር የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የስነ ጥበብ ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሰርፀ ፍሬስብሃትን አግኝቷቸዋል፡፡

 

ምላሽ

ጥቅምት 10፣ 2014- ሰኔ 14 እና መስከረም 20 የተካሄዱትን ምርጫዎች የታዘበው ኢሰመጉ ቀዳሚ ሪፖርቱን ዛሬ ይፋ አድርጓል

መስከረም 20፣ 2014 ምርጫ በተካሄደባቸው አካባቢዎች የተሻሉ አፈፃፀሞች ቢታዩም፤ ሂደቱ ላይ ችግሮች እንደነበሩም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ተናገረ፡፡ 

ሰኔ 14 እና መስከረም 20 የተካሄዱትን ምርጫዎች የታዘበው ኢሰመጉ ቀዳሚ ሪፖርቱን ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡ 

ምላሽ

ጥቅምት 9፣ 2014- ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች ከሰሜን እና ደቡብ ወሎ በተፈናቀሉ ዜጎች እጅግ በጣም እንደተጨናነቁ ተሰማ

በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀው የህወሓት ታጣቂ ኃይል በከፈተው ጦርነት ሳቢያ ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች ከሰሜን እና ደቡብ ወሎ በተፈናቀሉ ዜጎች እጅግ በጣም እንደተጨናነቁ ተሰማ፡፡

መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ምላሽ

ጥቅምት 9፣ 2014- በትግራይ እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ መወሰኑ የትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ

በትግራይ እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ መወሰኑ የትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ፡፡

በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል አሸባሪነት የተፈረጀው ህወሃት በተፈጠረው ችግር ምክንያት በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎችና በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ትምህርት ሚኒስቴር ወስኛለሁ ብሏል፡፡

በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና ወልዲያ የዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲ በጊዜያዊነት ለመመደብ የመመዝገቢያ ገፅ ተከፍቶ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ እና ምደባ እንደሚካሄድም ተነግሯል፡፡

ምላሽ

ጥቅምት 5፣ 2014- በኢትዮጵያ አጎአ ቢቋረጥ ምጣኔ ሀብቱን ምን ያክል ይጎዳ ይሆን?

ከሰሀራ በስተደቡብ ያሉ የአፍሪካ ሃገራት ከቀረጥና ኮታ ነፃ ሆነው ምርታቸውን ወደ አሜሪካ እንዲያስገቡ በጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር 2000 ከአሜሪካ ለአፍሪካ ሀገራት የተሰጠ ችሮታ ነው፡፡

ይህ በምህፃሩ አጎአ እየተባለ የሚጠራው የንግድ እድል በየጊዜው እየተራዘመ ለ21 ዓመታት ዘልቋል፡፡

በዚህ ነፃ ንግድ እድል የሚፈለገው ያክል ባይሆን እየተጠቀሙ ካሉ ሃገራት ኢትዮጵያ አንደኛዋ ነች፡፡

ባለፈው ዓመት ብቻ ኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ከላከችው 300 ሚሊየን ዶላር ገቢ ካገኘችበት ምርት ግማሹ በአጎአ እድል የተላከ ነው፡፡

ሰሞኑን አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምታደርሰውን ጫና ማጠናከሪያ አድርጋ ኢትዮጵያን ከዚህ እድል ለማስወጣት ማሰቧ እየተነገረ ነው፡፡

ይህ እውን ከሆነ ጉዳቱ የት ድረስ ይሆን?

አጎአ ቢቋረጥ ምጣኔ ሀብቱን ምን ያክል ይጎዳ ይሆን?

ምላሽ

ጥቅምት 5፣ 2014- በኢትዮጵያ ከደቡብ ክልል ውጪ ያሉት ሁሉም ክልሎች የራሳቸው የህዝብ መዝሙር አላቸው

በኢትዮጵያ ከደቡብ ክልል ውጪ ያሉት ሁሉም ክልሎች የራሳቸው የህዝብ መዝሙር አላቸው፡፡ 

በየትምህርት ቤቱም ታዳጊዎች የሚዘምሩት ይህንኑ የየክልሉን የህዝብ መዝሙር ነው፡፡ 

በተለይ አንዳንድ ክልሎች ሲያዘምሩት የኖሩትና አሁንም ያለው የህዝብ መዝሙር ቁርሾ፣ ቂምና በቀልን የሚያነሳሳ፣ ፀበኝነትን የሚያበረታታ ይዘት እንዳላቸው ሸገር ያነጋገራቸውና በግጥሞቹ ይዘት ላይ ትንታኔ የሰጡ ባለሙያዎች ትዝብታቸውን ተናግረዋል፡፡ 

ታዳጊ ሕፃናት ያሉበትን ክልል ብቻ እንደ አገር ቆጥረው ኢትዮጵያን እንዲዘነጉ የሚያደርግ ይዘት እንዳለውም ይነገራል፡፡ 

ወንድማማችነትና መከባበርንም የሚያመጣ ይዘት የለውም፡፡ 

ምላሽ

ጥቅምት 5፣ 2014- የሼሪያው ህግ ስለሚፈቅድልኝ 2 ባለቤቶች አሉኝ፤ 3ኛ የማግባት ሀሳብም አለኝ

የሼሪያው ህግ ስለሚፈቅድልኝ 2 ባለቤቶች አሉኝ፤ 3ኛ የማግባት ሀሳብም አለኝ፡፡ ወደ አዲስ አበባ የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ሄጄ ሁለቱንም ባለቤቶቼን እንዲመዘግቡልኝ ብጠይቅም ከ1 በላይ መመዝገብ አንችልም አሉኝ፡፡

የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ በበኩሉ የቤተሰብ ህጉ ከ1 በላይ የትዳር አጋር ስለማይፈቅድ መመዝገብ አልችልም ብሏል፡፡ ሸገር ያነጋገራቸው የህግ ባለሞያ በበኩላቸው ኤጀንሲው መመዝገብ አለበት ብለዋል፡፡

ምላሽ

ጥቅምት 5፣ 2014- ብዙም ያልተለመደ የነበረው አካባቢን እየጎበኙ የሚደረግ የእግር ጉዞ (ሀይኪንግ) እየተለመደ መምጣቱን እያስተዋልን ነው

ብዙም ያልተለመደ የነበረው አካባቢን እየጎበኙ የሚደረግ የእግር ጉዞ (ሀይኪንግ) እየተለመደ መምጣቱን እያስተዋልን ነው፡፡

ይኽው እንዲለመድ እየተጉ ያሉ ወጣቶችንና ጉዳዩ የሚመለከተው መስሪያ ቤት ኃላፊን ስለጉዳዩ ቴዎድሮስ ወርቁ አነጋግሯቸዋል፡፡

ምላሽ

ጥቅምት 4፣ 2014- የአሰላው የአህያ ቄራ በድብቅ ሥራ ጀምሯል

በኬንያ በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ የተከፈተው የአህያ ቄራ ከሚያርዳቸው 90 በመቶዎቹ በኮንትሮባንድ ተነድተው የሚሄዱ የኢትዮጵያ አህዮችን ነው፡፡

የአሰላው የአህያ ቄራ በድብቅ ሥራ ጀምሯል፡፡

ቄራው Manufacturing P.L.C የሚል ስያሜ ለጥፎ ማታ ማታ አህያ እያረደ ማቀዝቀዣ ባለው ኮንቴነር በጅቡቲ በኩል ሥጋ እና ቆዳውን ወደ ቻይና ይልካል ተብሏል፡፡

እንዲህ ከቀጠለ የኢትዮጵያ አህዮች በአጭር ጊዜ ቁጥራቸው መመናመኑና በገጠሩ ማኅበረሰብ ዘንድም ትልቅ ማኅበራዊ ቀውስ እንዳይኖር ተሰግቷል፡፡

በመሆኑም መንግሥት በኮንትሮባንድ የሚወጡ አህዮችን እንዲቆጣጠር የአሰላውን ቄራም ሥራ እንዲያስቆም ተጠይቋል፡፡

ምላሽ
ወሬ መለያዎች
Reset filters
2021-10-20
ኮቪድ 19 ሃገራዊ ስፋቱ እጅግ ጨምሯል ተባለ፡፡ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ብም በወርሽኙ ከ2 መቶ በላይ ሰዎች ሕይወት…
2021-10-20
ውሃን ከከርሰ ምድር አውጥተው እያሸጉ የሚሸጡ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ተበራክተዋል፡፡ ዘርፉ የአዋጭነት ሁኔታው በጥንቃቄ…
2021-10-20
ወደ ጅቡቲ የገቢና የውጪ እቃዎችን የሚያጓጓዙ ከባድ ተሽከርካሪዎች የይለፍ ፈቃድ የሚሰጣቸው አጥተዋል ተብሏል ለምን?
2021-10-20
በሕንድ ኡትራካሐንድ ግዛት የደረሰ ቅፅበታዊ የጎርፍ አደጋ በጥቂቱ 46 ሰዎችን መግደሉ ተሰማ፡፡ በግዛቲቱ የደረሰው ጎርፍ…
2021-10-20
የኢራኑ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ አሜሪካ ከኢራን ጋር በቀና ልቦና መነጋገር ካሻት የጣለችብንን ማዕቀብ ልታነሳው ይገባል አሉ…
2021-10-20
ሰሜን ኮሪያ ትናንት ወደ ባሕር የተኮሰችው ባልስቲክ ሚሳየል ከባሕር ሰርጓጅ መርከብ የተተኮሰ መሆኑን አረጋገጠች፡፡ ቀደም…