ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ህዳር 18፣ 2014- ዘመን ባንክ የባለፈው በጀት ዓመት ካቀድኩት በላይ ትርፍ በትርፍ የሆንኩበት ነው አለ

Image
ዘመን ባንክ

ዘመን ባንክ የባለፈው በጀት ዓመት ካቀድኩት በላይ ትርፍ በትርፍ የሆንኩበት ነው አለ። 

ባንኩ በ2013 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 1.2 ቢሊዮን ብር ትርፍ አግኝቻለሁ ብሏል። 

ትርፉ በእቅድ ተይዞ ከነበረው ጋር ሲተያይ የ16.2 በመቶ፤ ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ደግሞ የ30 በመቶ ብልጫ አለው ተብሏል።

በዛሬው ዕለት ዓመታዊ የባለ አክስዮኖች ዓመታዊ ጉባዔ እያካሄደ የሚገኘው ዘመን ባንክ፣ የተከፈለ ካፒታሉ 2 ቢሊዮን 749 ሚሊዮን ብር መድረሱን ተናግሯል።

አጠቃላይ ሀብቱ 25.2 ቢሊዮን ብር፤ የሰጠው ብድር 14 ቢሊዮን ብር መድረሱን ተናግሯል።

የባንኩ የተበላሹ ብድሮች ክምችት 2.25 በመቶ ላይ ይገኛል ተብሏል።

ዘመን ባንክ በ2013 በጀት ዓመት ከሰጠው ዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎት 418 ሚሊዮን ዶላር አግኝቻለሁ  ያለ ሲኾን፣ ብሔራዊ ባንክ፣ ባንኮች ከሚያገኙት የውጪ ምንዛሪ 30 በመቶ ለባንኩ እንዲያስገቡ ባወጣው መመሪያ መሠረት 127 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማድረጉን ተናግሯል።

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ