ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ነሐሴ 18፣2012/ የ2013 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ነገ እንደሚጀመር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ተናገረ

የ2013 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ነገ እንደሚጀመር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ተናገረ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2013 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ከነገ ነሐሴ 19፣2012 ዓ.ም ጀምሮ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተገቢዉን ጥንቃቄ በማድረግ ይጀመራል ብሏል፡፡

በመንግሰት ትምህርት ቤቶች ለሚደረገዉ ምዝገባ ትምህርት ቤቶች አስፈላጊዉን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ቢሮው ያሳሰበ ሲሆን የግል የትምህርት ተቋማትም ከነገ ጀምሮ   ምዝገባ ማካሄድ እንደሚችሉ ቢሮው ተናግሯል።

ትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ በአጠቃላይ አገሪቱ ከነገ በስቲያ ጀምሮ የተማሪዎች ምዝገባ መካሄድ አለበት ብሏል።

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ያወጣውንም የምዝገባ ማስታወቂያ አልተቃወመም።

ትምህርት የሚጀመርበት እንዲሁም የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ፈተና መስጫ ጊዜን በቅርብ እንደሚያሳውቅም ሚኒስቴሩ ተናግሯል።

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ