ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ታሪክን የኌሊት-ነሐሴ 12፣2012/ከ180 ዓመት በፊት በዛሬዋ ቀን የተወለዱት እቴጌ ጣይቱ ብጡል

በሀገር አስተዳደር፣ ከውጭ ወራሪዎችን በመዋጋት፣ከፍ ያለ ያመራር ተሳትፎ እንዳላቸው ታሪክ የመዘገበላቸው እቴጌ ጣይቱ የተወለዱት ከ180 ዓመታት በፊት በዛሬው ቀን ነበር፡፡

እቴጌ ጣይ ብጡል በ1832 ዓ.ም. ወሎ በየጁ አካባቢ ተወለዱ፡፡ በጊዜው የነበረውንና ለሴቶች ደረጃ የሚፈቀደውን፣ የመፃፍና የማንበብ ትምህርት ተምረዋል፡፡

ወይዘሮ  ጣይቱ፣ አራተኛቸው የሆኑትን ባላቸውን ዳግማዊ አፄ ምንይልክን ካገቡ በኋላ በሃገራዊ ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ የሚታወቁ ሆነዋል፡፡

እንደርሳቸው ሁሉ ነሐሴ 12 የተወለዱትና በአራት ዓመታት የሚልቋቸው አፄ ምንሊክን ካገቡ በኋላ የእቴጌነት ማዕረግ አግኝተዋል፡፡ 

እቴጌ ጣይቱ፣ የራሳቸው የታጠቀ ሰራዊት እየመሩ ሌላ ጊዜም  ወታደሮቻቸውን በአጋዥነት እየላኩ በዘመቻዎች ላይ የሚሳተፉ ነበሩ፡፡ 

አዲስ አበባን ለከተማነት የቆረቆሩዋት ስያሜዋንም ያወጡላት እቴጌ ጣይቱ ነች፡፡

በሞቃታማው ፍል  ውሃ ለመታጠብ ከሚመጡት ቦታ ካለው ጉብታ፣ ላይ አነስተኛ እልፍኝ አሰርተው ተቀመጡ፡፡

አፄ ምኒልክ በጊዜው በዘመቻ ላይ ስለነበሩ፣ እቴጌ ጣይቱ ሰፈራቸውን ከእንጦ ቤተመንግስት ለቀው  አዲስ ባሰሩዋት እልፍኝ አደረጉ፡፡

ቤቶች ለመስራት ደኑ ሲመነጠር አይተዋት የማያወቁ አበባ በማየታቸው ፣አዲሷን ከተማ፣ አዲስ አበባ ብለው ሰይመዋል፡፡

እቴጌ ጣይቱ ብጡል በውጭ ፀሃፊዎች ጭምር በአድናቆት የተፃፈላቸው፣ የኢጣሊያን ወራሪ ሀይል ለመቋቋም ከዝግጅቱ እስከ ጦርነቱ ባሳዩት ተጋድሎ ነው፡፡

አፄ ምኒልክ፣ የውጫሊን ውል ማፍረሳቸውን ሲያስታውቁ፣ ከኢጣሊያው ተወካይ ጋር በተደረገው ንግግር ተሳታፊ ሆነው ቁርጠኛ አቋማቸውን አሳውቀዋል፡፡

ተወካዩ፣ ወርቀቱን ቀዶ ሲወጣ፣ ከት ከት ብለው ስቀው፣ “ጦርነቱን ነገ አድርገው ፤ ለዚህ የሚደነግጥልህ የለም”  ማለታቸው ይጠቀስላቸዋል፡፡

በአድዋ ጦርነት ዘመቻ፣ እስከ 3,000 የሚደርሱትን የራሳቸውን ወታደሮች ይዘው ዘምተዋል፡፡

የኢጣሊኖች የመቀሌ ምሽግ የተሰበረው በእቴጌ ጣይቱ የጦርነት እቅድ ነበር፡፡ ተጠናክሮ የተሰራውን የመቀሌ ምሽግ፣ ፊት ለፊት ለመደምሰስ ባለመቻሉ እቴጌ ጣይቱን በቅድሚያ ቦታውን አስጠኑ፡፡ ኢጣሊያኖች የሚጠቀሙበትን ውሃ መያዝ ይቻል እንደሆነ አሰለሉ፡፡ 

በግንባር ለሚዋጉት ሊቀመኳስ አባተ አማከሩ፡፡

ወደ እርምጃ ለመግባት የሚቻል መሆኑን ሲያምኑ እቅዳቸውን ተግባራዊ ለማድረግ አፄ ምኒልክን አስፈቀዱ፡፡

እንዳቀዱት፣ 900 የሚሆኑ የራሳቸውን ወታደሮች ልከው ኢጣሊያኖች የሚጠቀሙበትን የምንጭ ውሃ አስደፈኑ፡፡

ለ15 ቀናትም፣ በተደረገ ጥበቃ፣ ኢጣሊያኖች በውሃ ጥም ተጨንቀው ምሽጉን ለቀቁ በጊዜያቸው ተደማጭ ነበሩ፡፡

እቴጌ ጣይቱ በብዙዎች ዘንድ የማይታወቀውን ቼዝ መጫወት፣ በገና መደርደር ይችላሉ፡፡ ብስክሌት መንዳትም ተላምደው እንደነበረ ተፅፏል፡፡ 

አፄ ምኒልክ በሕመም ምክንያት ቤት ሲውሉ፣ የመንግስትን ስልጣን ወስደው በማንኛውም ጉዳይ መወሰንና ሹም ሽር ማድረግ ጀምረው ነበር፡፡


ግን ብዙም ሳይቆዩ የጊዜው ሹማምንት የመንግስቱ ስልጣን አፄ ምኒልክ እንዳዘዙት በልጅ ኢያሱና በእንደራሴው እንዲከናወን እርሳቸው ከስልጣን እርቀው ባላቸውን እንዲያስታምሙ ወሰኑባቸው፡፡

ከዳግማዊ ምኒልክ ሞት በኋላ፣ ከቤተ መንግስት ወጥተው እንጦጦ እንደኖሩ ሆኖ በዚያው እያሉ በተፈጥሮ ሕመም በ78 አመታቸው አርፈዋል፡፡

ቀብራቸው በጊዜው እንጦጦ ማርያም ቢፈፀምም፣ በኋላ ንግስት ዘውዲቱ ከባለቤታቸው አፅም ጋር ፣ በበዓታ ለማርያም ገዳም አፅማቸው እንዲያርፍ አድርገዋል፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ