ማስታወቂያ

የሸገር ወሬዎቻችን

Sort by
ነባሪ
Post Date
2021-06-18
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን አገሬ ከአሜሪካ ጋር ለሚደረግ ንግግርም ሆነ ግጭት ዝግጁ ነኝ አሉ፡፡ የኬም ጆንግ ኡን አስተያየት ጆ ባይደን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከሆኑ በኋላ የመጀመሪያው እንደሆነ ቢቢሲ አስታውሷል፡፡ ሰሜን ኮሪያ በተለይም ከአሜሪካ ጋር በኒኩሊየር እና በሌሎችም ታላላቅ የጦር መሳሪያዎች ውዝግቧ ነባር ነው፡፡ በጠላትነትም የሚተያዩ አገሮች ናቸው፡፡ ኪም ጆንግ ኡን አገሬ ከአሜሪካ በኩል ለሚጠብቃት ሁሉ ዝግጁ ነች ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ በአገሪቱ የአድራጊ ፈጣሪው የሰራተኞች የፖለቲካ ማህበር ማዕከላዊ ኮሚቴ ሳምንቱን ስብሰባ ላይ እንደሆነ መረጃው አስታውሷል፡፡
2021-06-18
ኬንያ የሞቃዲሾ ኤምባሲዋን ለመክፈት እየተሰናዳች መሆኑን በሶማሊያ የአገሪቱ አምባሳደር ተናገሩ፡፡ በሞቃዲሾ የኬንያ ኤምባሲ ዳግም የሚከፈተው ሶማሊያ ባቀረበችው ግብዣ መሰረት እንደሆነ ዘ ኢስት አፍሪካን ፅፏል፡፡ የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ሶማሊያም የናይሮቢ ኤምባሲዋን ዳግም እንድትከፍት መጠየቁ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡ የኤምባሲዎቹ ዳግም መከፈት ሁለቱ አገሮች ወደ ሙሉ ዲፕማሲያዊ ግንኙነታቸው እንደሚመለሱ ግምት አሳድሯል፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሁለቱ አገሮች ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወሰድ መለስ የበዛው ሆኖ ቆይቷል፡፡ ሁለቱ አገሮች ከዲፕሎማሲያዊ በተጨማሪ ፖለቲካዊ ጉሽሚያ ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ ኬንያ እና ሶማሊያ በውቅያኖስ ዳርቻ የውሃ አካል የይገባኛል ውዝግባቸው ነባር ነው፡፡
2021-06-18
የዛምቢያ መንግሥት ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት የአገሪቱ የነፃነት ማግስት የመጀመሪያ ፕሬዝዳንት ኬኔት ካውንዳ የ3 ሳምንታት ብሔራዊ ሐዘን አወጀ፡፡ ካውንዳ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት በ97 ዓመታቸው እንደሆነ ቢቢሲ አውርቷል፡፡ የአገራቸው የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት በመሆን ለ27 ዓመታት አገልግለዋል፡፡ በአገልግሎታቸው መልካም ስም ካፈሩ የአፍሪካ መሪዎች አንዱ ሆነው ይጠቅሳሉ፡፡ አገራቸው ዛምቢያ ሰሜን ሮዴዢያ ትባል በነበረት ወቅት ከብሪታንያ ቅኝ አጋዛዝ ነፃ እንድትወጣ ታላቅ ድርሻ ማበርከታቸው ይነገርላቸዋል፡፡  ኬኔት ካውንዳ የሳምባ ምች የጤና እክል አጋጥሟቸው ሆስፒታል የገቡት ሰኞ እለት ነበር፡፡ ካውንዳ ከ30 ዓመታት በፊት አገራቸው ወደ መድብለ ፓርቲ ሥርዓት በተሸጋገረችበት ወቅት ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው በማስረከብ በመልካም እንደሚነሱም መረጃው አስታውሷል፡፡ በካውንዳ ሕልፈት የዛምቢያ መንግሥት ለ3 ሳምንታት የሚዘልቅ ብሔራዊ ሐዘን ማወጁ ተሰምቷል፡፡ በብሔራዊ ሐዘኑ ወቅት ማንኛውም የፈንጠዝያ ዝግጅት መከልከሉ ታውቋል፡፡
2021-06-14
ፓኪስታን ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ ሲባል ከ26 አገሮች መንገደኞች እና ተጓዦች ድርሽ እንዳይሉብኝ አለች፡፡ የፓኪስታን መንግሥት ብሔራዊ አካል ወደ አገሪቱ እንዳይመጡ ካላቸው መካከል መነሻቸው ከሕንድ፣ ከባንግላዴሽ፣ ከኢራን፣ ከኢራቅ፣ ከኢንዶኔዝያ፣ ከብራዚል፣ ከሜክሲኮ እና ከደቡብ አፍሪካ የሆነ መንገደኞች የተወሰኑት እንደሆኑ ገልፍ ኒውስ ፅፏል፡፡ የአገሪቱ ብሔራዊ የጤና ኮሚቴ ወደ አገሪቱ መግባት የሚችሉ የውጭ አገራት ተጓዦችን በእርከን ከፋፍሎ ማስቀመጡ ታውቋል፡፡ ወደ አገሪቱ ሲገቡ አስገዳጅ ምርመራ እና ለይቶ ማቆያ የማይመለከታቸውም ተለይተዋል ተብሏል፡፡ ወደ አገሪቱ ሲደርሱ ከ72 ሰዓታት ያላለፈው የኮሮና ቫይረስ የምርመራ ማረጋገጫ ማቅረብ ያለባቸውም እንደተዘረዘሩ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡
2021-06-14
የእስራኤል ፓርላማ አዲሱን ጥምር መንግሥት ተቀበለው፡፡ ክኔሴት የተሰኘው የአገሪቱ ፓርላማ አዲሱን ጥምር መንግሥት የተቀበለው 60 ለ59 በሆነ ጠባብ የድምፅ ልዩነት እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ የፓርላማው ውሳኔ የቤኒያሚን ኔታንያሁ የ12 ዓመታት ዘመነ ጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲያበቃ አድርጓል፡፡ ከእንግዲህም ኔታንያሁ መታወሻቸው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል፡፡ ቀኝ ክንፈኛው ብሔረተኛ ናፍታሊ ቤኔት ለ2 ዓመታት ከ3 ወራት ያህል ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሆኑ ታውቋል፡፡ ከዚያም ለዚያ ያህል ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ለተጣማሪያቸው ያኢር ላፒድ ያስረክቧቸዋል፡፡ የ8 የፖለቲካ ማህራት ስብስብ የሆነው አዲሱ የእስራኤል ጥምር መንግሥት የለውጥ መንግስት መሰኘቱ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡ ቤኒያሚን ኔታንያሁ ፓርላማው አዲሱን ጥምር መንግሥት እንዳይቀበለው ሲያስጠነቅቁ ቢሰነብቱም እንዳልተሳካላቸው ታውቋል፡፡ ኔታንያሁ ወደ ተቃዋሚነት የተለወጠው የሊኩድ የፖለቲካ ማህበር መሪ ሆነው ይቀጥላሉ ተብሏል፡፡ ከፖለቲካ ውጭ እንደማይሆኑም ተጨማሪ ያንብቡ
2021-06-14
የሶማሊያ መንግሥት ጦር በዘመቻዬ በለስ እየቀናኝ ነው አለ፡፡ ጦሩ ትናንት ባወጣው መግለጫ ባለፉት 48 ሰዓታት በ3 የተለያዩ ግዛቶች ባካሄድኩት ዘመቻ ከ50 የማያንሱ ፅንፈኞችን ገድያለሁ ማለቱን አናዶሉ ፅፏል፡፡ በዚሁ ዘመቻ በርካታ የፅንፈኛው የአልሸባብ ቡድን የጦር ሰፈሮች እንደወደሙ የሶማሊያ መንግሥት ወታደራዊ አዛዦች ተናግረዋል፡፡ የሶማሊያ መንግሥት ጦር መሰንበቻውን ተከታታይ የድል መግለጫዎችን እያወጣ መሆኑን መረጃው አስታውሷል፡፡ በቅርብ ጊዜው ተከታታይ ዘመቻ ከ130 በላይ የአልሸባብ ፀንፈኛ ታጣቂዎችን ገድያሁ ብሏል፡፡ የሶማሊያ መንግሥት ጦር በፀረ አልሸባብ ውጊያ በአፍሪካ ህብረት ሰራዊት (አሚሶም) እንደሚረዳ ይታወቃል፡፡
2021-06-12
እስያዊቱ አገር ፊሊፒንስ ከልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) ወረርሽኝ ተገላገለች፡፡ የአለም የጤና ድርጅት እና የተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ድርጅት (ዮኒሴፍ) በጋራ ፊሊፒንስ ኮፖሊዮ በሽታ ነፃ መሆኗን አውጀውላታል፡፡ ከ2 ዓመታት ገደማ በፊት ወረርሽኙ አገርሽቶ እንደነበር አሶሼትድ ፕሬስ አስታውሷል፡፡ አስቀድሞ በፊሊፒንስ ፖሊዮ ተወግዷል የተባለው ከ20 ዓመታት በፊት ነበር፡፡ ፊሊፒንስ ዳግም ከፖሊዮ ነፃ የሆነችው ባካሄደችው ጠንካራ የክትባት ዘመቻ ነው ተብሏል፡፡ በዘመቻው 30 ሚሊዮን ያህል ሕፃናት መከተባቸው ታውቋል፡፡
2021-06-12
የቡድን 7 አባል አገሮች መሪዎች ከእንግዲህ የኮሮና ቫይረስ ዓይነት ወረርሽኝ ተመሳሳይ ጥፋት እንዳያደርስ ከወዲሁ ለመከላከል አቅማቸውን ለማሳደግ ማሰባቸው ተሰማ፡፡ አላማው ማንኛውም ዓይነት ወረርሽኝ ቢቀሰቀስ ከ100 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ የመከላከያ ክትባት መፍጠርን እንደሚጨምር ቢቢሲ ፅፏል፡፡ የቡድን 7 አባል አገሮች መሪዎች ከትናንት አንስቶ በእንግሊዝ ኮርንዌል ጉባኤ ላይ ናቸው፡፡ የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በጉባኤው መክፈቻ ወቅት በአለም አቀፍ ደረጃ የሚስተዋለው የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት ኢ-ፍትሃዊ ስርጭት መፍትሄ የሚሻ ጉዳይ ነው ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ ሐብታሞቹ አገሮች ከሚያስፈልጋቸው በላይ ክትባቶችን ሲቀራመቱ ድሆቹ አገሮች የሚያገኙት በቁጥቁጥ እና በተቆራረጠ ሁኔታ ነው፡፡ ይሄ እውነታ እንዲቀየር አለም አቀፍ ጥሪው ሲያስተጋባ ቆይቷል፡፡ የቡድን 7 አባል አገሮች ለድሆቹ አገሮች የኮሮና መከላከያ ክትባት ለማቅረብ ቃል ይገባሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡ አሜሪካ፣ ብሪታንያ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ተጨማሪ ያንብቡ
2021-06-12
በናይጄሪያ የተማሪዎች እና የአስተማሪዎች እገታ መቆሚያ አላገኘም ተባለ፡፡ በሰሜን ምዕራብ ናይጀሪያ ካዱና ግዛት ከሚገኝ አንድ ፖሊ ቴክኒክ ትምህርት ቤት 8 ተማሪዎች እና 2 መምህራን ታግተው ተወስደዋል መባሉን ቢቢሲ ፅፏል፡፡ በእገታው ወቅት ታጣቂዎች አንድ ሰው መግደላቸውም ተሰምቷል፡፡ በተያዘው በጎረቤት ዛምፋራ ግዛት ከ60 የማያንሱ ሴቶች የታገቱት ሰሞኑን ነው፡፡ እንደሚባለው የታጠቁ ወንበዴዎች እገታውን የሚፈፅሙት የቤዛ ክፍያ ለመጠየቅ አልመው ነው፡፡ ከቅርብ አመታት ወዲህ በአገሪቱ የተማሪዎች እና የመምህራን እገታው እየተባባሰ መምጣቱ ይነገራል፡፡
2021-06-10
በሰሜናዊ ምዕራብ ናይጀሪያ ዛምፋራ ግዛት ታጣቂዎች ከ60 የማያንሱ ሴቶችን አግተው ወስደዋል ተባለ፡፡ ታጣቂዎቹ በበርካታ መንደሮች ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ቢቢሲ ፅፏል፡፡ በርካታ መኖሪያ ቤቶችን እንዳቃጠሉ እና ብዛታቸው በውል ያልተጠቀሰ ሰዎችን መግደላቸው ተሰምቷል፡፡ ፖሊስ በዛምፋራ ግዛት ገጠራማ መንደሮች ታጣቂዎች ጥቃት ማድረሳቸውን ማረጋገጡን በመረጃው ተጠቅሷል፡፡ ይሁንና ታግተው ተወስደዋል በተባሉት ሰዎች ብዛት አልተስማማም ተብሏል፡፡ በናይጀሪያ ይሄን መሰሉ ጥቃት እና እገታ እየተደጋገመ መምጣቱን መረጃው አስታውሷል፡፡ የታጠቁ ወንበዴዎች እገታቸውን የደጋገሙት የማስለቀቂያ የቤዛ ክፍያ ለማግኘት አልመው መሆኑ ይነገራል፡፡ በቅርቡም ከማዕከላዊ ናይጀሪያ ቴጊና ታግተው የተወሰዱ ከ130 በላይ ሕፃናት ተማሪዎች እንዳልተለቀቁ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡