ማስታወቂያ

የሸገር ወሬዎቻችን

Sort by
ነባሪ
Post Date
2021-06-19
ኢትዮጵያ ውስጥ ከዓመታት በፊት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የነበረው የሃገሪቱ አውድ አላላውስ አለን ፤  መስራት አልቻልንም የሚሉ ቅሬታዎችን ያቀርቡ ነበሩ፡፡  የዴሞክራሲ ግንባታና የሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ እንዳይሰሩ እገዳ በመጣሉም መቸገራቸውን ሲናገሩ አቤቱታም ሲያሰሙ  ቆይተዋል፡፡ ድርጅቶቹ ሲያነሱት የነበረው ችግር እልባት ያገኘ በመሆኑ  በተፈጠረው ሁኔታ ምን እየሰሩ ነው፡፡
2021-06-19
የፊታችን ሰኞ ሰኔ 14 በሚካሄደው ምርጫ አዲስ አበቤዎች ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ተወካዮቻቸው 23 እጩዎችን ይመርጣሉ፡፡ አዲስ አበባ በህዝብ እንደራሴዎች ለሚኖራት 23 መቀመጫዎች 15 የፖለቲካ ፓርቲዎች ያቀረቧቸው እጩዎችና 2 የግል ተወዳዳሪዎች በእጩነት የቀረቡበት ነው፡፡  ትዕግስት ዘሪሁን ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የሚወዳደሩ የአዲስ አበባ ተወዳዳሪ ወኪሎችና ፓርቲዎችን በተመለከተ ያዘጋጀችው አለ፡፡
2021-06-19
ሕዝብ ያሻውን እንዲመርጥ ዴሞክራሲያዊ  መብቱን  እንዲጠቀም  የመራጮች ትምህርት መስጠት አንዱና ወሳኝ የምርጫ  ጊዜ ተግባር ነው፡፡ ሰኞ ለሚካሄደው ምርጫ ዘግይቶም ቢሆን የተለያዩ ሲቪክ ማህበራት ይህንኑ የመራጮች  ትምህርት በተለያዩ አካባቢዎች እየሰጡ እንደሆነ ሰምተናል፡፡  ከምርጫ ቦርድ ፈቃድ ወስደው ትምህርቱን እየሰጡ ከነበሩት ከ100 በላይ የሲቪክ ማህበራት መካከል ሸገር የተወሰኑትን ማህበራት የትምህርቱ አሰጣጥ እንዴት ነበር ምንስ ታዝበው ይሆን? ሲል  ጠይቋል፡፡ 
2021-06-18
ግዙፍ የነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች የሚያመርተውና የሚከፋፈለው ቶታል ኩባንያ የስያሜ ለውጥ አደረገ፡፡ ቶታል ከእንግዲህ በኋላ መጠሪያው ቶታል ኢነርጂስ እንዲሆን ኩባንያው የወሰነው በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደ የባለ አክሲዮኖች ስብሰባ ወቅት መሆኑንን ሰምተናል፡፡ ኩባንያው የስያሜ ለውጥ ማድረጉ ወደ ሁለገብ የሀይል ኩባንያ ለመለወጥ ለሚያደርገው ሂደት አጋዥ መሆኑን ሸገር ከኩባንያው የደረሰው መረጃ ያሳያል፡፡ የቶታል ኢነርጂስ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፓትሪክ ፑያኔ የአየር ንብረት ፈተና ላጋጠማት ምድራችን ዘላቂ የሆነ የልማት አስተዋጽኦ ወደ ፊት እየሄድን ነው ሲሉ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡ በተመሳሳይ ቶታል ስያሜውን ወደ ቶታል ኢነርጂስ ከመለወጡ በተጨማሪ አዲስ የንግድ ምልክትንም ይፋ አድርጓል፡፡ የቶታል ኢነርጂስ አዲስ ስያሜ እና የንግድ ምልክት አስተማማኝ እና ንፁህ የሆነ ኃይል ለማመንጨት እና ምርቶቹን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ እንደሚያግዘው ተናግሯል፡፡ ከእንግዲህ በኋላ ወደ ቶታል ኢነርጂስ የተቀየረው የፈረንሳዩ ቶታል በኢትዮጵያ ተጨማሪ ያንብቡ
2021-06-18
በመጪው ሰኞ የሚካሄደው 6ኛው ሃገራዊ ምርጫ በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ማድረጉን የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን ተናገረ፡፡ 
2021-06-18
በሰሜን ሸዋ ዞን 32 ወረዳዎች ለሚካሄደው ምርጫ ፖሊስ ዝግጅቴን አጠናቅቄአለሁ አለ፡፡ 
2021-06-18
የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን አዲስ አበባ ገባ፡፡ ሰኞ ለሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን በቀድሞ የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ እየተመራ አዲስ አበባ መድረሱን ህብረቱ ተናግሯል፡፡ ለምርጫ ታዛቢ ቡድኑ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬአለም ሽባባው አቀባበል አድርገውለታል፡፡
2021-06-18
እስከ ሰኞ በሚኖረው የጥሞና ጊዜ መገናኛ ብዙሃን የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጉዳይ የተመለከቱ መረጃዎችን ትተው ለመራጮች ግንዛቤ የሚሰጡ መረጃዎች ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳሰበ፡፡  የምርጫ አሰጣጡን እና የድምፅ ቆጠራውን ሂደት በተመለከተም ቦርዱ መገለጫ ሰጥቷል፡፡   
2021-06-18
የኢትዮጵያ ደረቅ ወደብ የተሟሸባት ሞጆ ከተማ፤ ወደፊት ሙሉ በሙሉ የሎጅስቲክስ መዲና መሆኗ እንደማይቀር ተሰማ፡፡ ሞጆ የገቢና ወጪ ጭነቶች ማስተላለፊያነቷ እየደራ በመምጣቱ የሞጆ ደረቅ ወደብ ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት ማዘመንና ማሳደግ አስገድዶታል፡፡  ለዚህም ሲባል የወደቡ ይዞታ እየሰፋ አዳዲስ ግንባታዎች ከስር ከስር እየተጨመሩ ነው፡፡ ከዓለም ባንክ በተገኝ 150 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ሞጆ ላይ የገቢና ወጪ እቃዎች የሚስተናገዱባቸው የኮንቴነር ማኖሪያ፣ የዕቃ ማቆያ መጋዘኖች፣ መተላለፊያ መንገዶች፣ ከባቡር ማውረጃና መጫኛ ማሽኖች እንዲገዙበትና እንዲሰሩበት እየተደረገ ነው፡፡ የሞጆ ደረቅ ወደብ ቀልጥፎ አገልግሎት መስጠት መቻሉ በሀገርም ሆነ በእያንዳንዱ ግለሰብ ኢኮኖሚ ያለው መዋጮ ቀላል የሚባል አይደለም ይላሉ ሙያተኞች፡፡  የኢትዮ ጅቡቲ ዋና የንግድ መተላለፊያ የሆነው ሞጆ ደረቅ ወደብ እስካሁን ከተሰሩለት የአገልግሎት ማዘመኛዎች የበለጠ ፋይዳ የሚኖረው የማሻሻያ ስራ ፕሮጀክት ትናንት ተበስሯል፡፡  ተጨማሪ የይዞታ ስፋት ተጨማሪ ያንብቡ
2021-06-18
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ለባለሀብቶች ምቹ የሆኑ ብዙ መሰረተ ልማቶች የተሟሉ ቢሆኑም፤ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ተሳትፎ በጣም አናሳ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ተናገረ፡፡