ማስታወቂያ

programs top mid size ad

በጀት መዝጊያ መጣ ስልጠና ደግሱ

"በጀት መዝጊያ መጣ ስልጠና ደግሱ"

ጠያቂው የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ነው፡፡ ሪፖርት እሚያቀርበው ደግሞ አንዱ የመንግስት መ/ቤት ነው፡፡

ተጠያቂው መ/ቤት የሚጠያቃቸው ጥያቄዎችን የያዘ ወረቀት እጄ ላይ አለ፡፡

ጥያቄዎቹን እያየሁ ወረቀቱን ገለጥ ገለጥ ሳደርግ የመጨረሻው ጥያቄ እንዲህ ይላል (ቃል በቃል ነው)

እንደሚታወቀው መ/ቤቱ በ11 ወር የተጠቀመው ከተፈቀደለት በጀት 70 በመቶውን ብቻ ነው፡፡ በቀረው ግዜ በጀቱን እንዴት ሊጠቀምበት እንዳሰበ በእቅድ የተያዘ ነገር ካለ ቢገለፅ ለምሳሌ. . . ስልጠናዎችን ማዘጋጀት የቢሮ እቃዎችን መግዛት ሌላም ሌላም . . .
በጀት መመለስ ሃጥያት ሆነ እንዴ?
እንዴት ሳትጠቀም ቀረህ? አንድ ጥያቄ ነው::
ስራው ካልተሰራ መውቀስ. . . ስራው ወጪ ቆጣቢ ሆኖ ተሰርቶም ከሆነ ገንዘብ ያስተረፈውን መ/ቤት ማወደስ ሲገባ በስልጠና ልታንጣጣው አለሰብክም እንዴ? ማለት እንዴት ያለ ነገር ነው?
2007 አልቀበልም ይላል እነዴ?እሚባለውን ለመስማት ጓጓሁ፡፡ መላሾቹ በሌሎቹ ጥያቄዎች ተጠምደው ምላሹ ሳይሰማ ስብሰባው አበቃ!
እንዲህ ያለው ችግር የብዙዎቹ የመንግስት መ/ቤቶች ስራ ነው፡፡ ለብዙዎቹ በጀት መመለስ የስንፍና ምልክት ተደርጎ ነው የሚታየው፡፡ ለዚህም ይመስላል ለ11 ወር የተለመደው የመ/ቤቱ ገንዘብ አወጣጥ በመጨረሻው ወር ጣሪያ ይነካል፡፡
በጀት መዝጊያ ሲደርስ እሚያስፈልገውም እማያስፈልገውም ያለውም እቃ ሁሉ መሸመት ይጀምራል፡፡
ወንበር ስራውን ይሰራ ይመስል ያለው እንከን ሳይወጣለት አዲስ ወንበር ይቀየራል፡፡
በውድ መጋረጃ መስኮቶች ይጌጣሉ፡፡
ስልጠናዎች በገፍ ይዘጋጃሉ፡፡
"ከከተማ ወጣ ይባል" ይባላል፡፡
አበል እንደጉድ ይከፈላል፡፡ የምሳ ግብዣው በውድ ሆቴል ይደረጋል፡፡
ሰባራ ሳንቲም እንዳትቀር ነው እቅዱ፡፡
አንዳንዴ ይህም ይሁን ስልጠናው ታስቦበት ሰራተኛው የጎደለው ተጠንቶ የተወሰነለት ባይሆንም ሰው ላይ የፈሰሰ ሃብት ነውና ብክን አለ አንልም፡፡ ወንበሩንም ይገዛ ተመዝግቦ የሚከማች የህዝብ ሃብት ይሆናል በጀት እንዳይተርፍ ብለው የረሱትን መንገድ የሚገነቡ እና አስፓልት የሚያድሱትን ምን ይሉታል ?
ወትሮ መንገድ በክረምት ስራው ይሰተጓጎላል ያባላል፡፡ ዝናቡ ለስራ አይመችም፡፡ ድንጋይ ምንጣፍም በጭቃ ላይ አይዘረጋምና እና ነው ነገሩ፡፡
ግን ግን በጋውን የተዘነጉ ኮብልስቶን መንገዶች በክረምት ሊያውም በቀናት እንዲጠናቀቁ ታዘው ስንቶቹ መስከረም ሳይጠባ . . .በጎርፍ ታጥበው ፈረሱ? ሁላችንም በሰፈራችን በየአከባቢያችን የምናየው ነው፡፡
ቅድም ያልኳችሁ መ/ቤት አመታዊ በጀቱ 98 ሚሊየን ብር ገደማ ነው፡፡ ተጠቀመ የተባለው ደግሞ ወደ 67 ሚሊየን ብሩን ነው፡፡
በቀረው አንድ ወር እንዴት ልትደፋፉት አስባችኋል የሚባለው እንግዲህ 30 ሚሊየን ብር ነው፡፡
እንዴት ነው ነገሩ?
ተሰርቶም በቀረው አንድ ወር ተደፋፍቶም ወደ መንግስት ካዝና ተመልሶም የ2006 በጀት አልቋል፡፡
የ2007ቱ ደግሞ ከዛሬ ይጀምራል፡፡ አመት ጨርሶ በጀት እንዳይቃጠል የህዝብ ሃብት ከማቃጠል የቤት ስራው በግዜ ቢጀመር!
 
ቁልፍ ቃላት
Tue, 07/08/2014 - 08:21