ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ነሐሴ 10, 2005:ታሪክን የኋሊት

ነሐሴ 10, 2005

አውሮፕላን የተፈለሰፈው በ20ኛ ክፍል ዘመን መጀመሪያ ነው፡፡ አውሮፕላን ከመፈልሰፉ ብዙም ሳይዘገይ ቴክኖሎጂውን ለውድድር ዓላማ የማዋል ሙከራዎች ነበሩ፡፡ የውድድር ዓላማ ኖሯቸው ከተዘጋጁት የአውሮፕላን በረራ ውድድሮች የዶል ውድድር የሚባለው አንዱ ነው፡፡ከተወዳዳሪዎቹ አብዛኞቹ ክፉ እጣ የገጠማቸው የዛሬ 86 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡ ውድድሩ ከሰሜናዊ ካሊፎርኒያ እስከ ሃዋይ የሚዘልቀውን 3 ሺ 870 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ነበር፡፡ የአትላንቲክ ውቅያኖስን ስለሚያቋርጥም የትራስ አትላንቲክ ውድድር በመባልም ይታወቃል፡፡ከኦክላንድ ካሊፎርኒያ እስከ ሃዋይ ሆኖሉሉ ለተደረገው ለዚህ አትላንቲክ አቋራጭ የበረራ ውድድር እስከ 18 አውሮፕላኖች በተፎካከሪነት ተመዘገቡ፡፡ ከመካከላቸውም አስራ አንዱ  መወዳደር የሚያስችላቸውን ማረጋገጫ አገኙ፡፡
ከዚህ ውድድር ከጥቂት ወሮች አስቀድሞ ቻርልስ ሊንድበርግ በተሳካ ሁኔታ ይሄን ርቀት መሸፈኑ ለውድድሩ መነቃቂያ ነበር፡፡
ጀምስ ዶል የተባለው የሐዋይ ከበርቴ ለውድድሩ የማበረታቻ ሽልማት የሚውል  35 ሺህ ዶላር  መደበ፡፡ 1ኛ ለሚወጣ 25 ሺህ ዶላር፤ 2ኛ ሆኖ ለሚያጠናቅቅ 10 ሺህ ዶላር ሽልማቱ አብራሪዎቹን ሳባቸው፡፡
ለፉክክሩ ከተመዘገቡት 11 አውሮፕላኖች ሦስቱ በቅድመ ውድድር የሙከራ በረራ ተከሰከሱ፡፡ ሶስቱ አብራሪዎቻቸው በዚሁ አደጋ ሕይወታቸውን አጡ፡፡ ስምንቱ ለዋናው ውድድር ተሠለፉ፡፡ ወደ ዋናው ፉክክር ከገቡት አውሮፕላኖች ሁለቱ ገና እንደተነሱ ተከሰከሱ፡፡ አውሮፕላን የተፈለሰፈው በ20ኛ ክፍል ዘመን መጀመሪያ ነው፡፡
አውሮፕላን ከመፈልሰፉ ብዙም ሳይዘገይ ቴክኖሎጂውን ለውድድር ዓላማ የማዋል ሙከራዎች ነበሩ፡፡
የውድድር ዓላማ ኖሯቸው ከተዘጋጁት የአውሮፕላን በረራ ውድድሮች የዶል ውድድር የሚባለው አንዱ ነው፡፡
ከተወዳዳሪዎቹ አብዛኞቹ ክፉ እጣ የገጠማቸው የዛሬ 86 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡
ውድድሩ ከሰሜናዊ ካሊፎርኒያ እስከ ሃዋይ የሚዘልቀውን 3 ሺ 870 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ነበር፡፡
የአትላንቲክ ውቅያኖስን ስለሚያቋርጥም የትራስ አትላንቲክ ውድድር በመባልም ይታወቃል፡፡
ከኦክላንድ ካሊፎርኒያ እስከ ሃዋይ ሆኖሉሉ ለተደረገው ለዚህ አትላንቲክ አቋራጭ የበረራ ውድድር እስከ 18 አውሮፕላኖች በተፎካከሪነት ተመዘገቡ፡፡
ከመካከላቸውም አስራ አንዱ  መወዳደር የሚያስችላቸውን ማረጋገጫ አገኙ፡፡
ከዚህ ውድድር ከጥቂት ወሮች አስቀድሞ ቻርልስ ሊንድበርግ በተሳካ ሁኔታ ይሄን ርቀት መሸፈኑ ለውድድሩ መነቃቂያ ነበር፡፡
ጀምስ ዶል የተባለው የሐዋይ ከበርቴ ለውድድሩ የማበረታቻ ሽልማት የሚውል  35 ሺህ ዶላር  መደበ፡፡ 1ኛ ለሚወጣ 25 ሺህ ዶላር፤ 2ኛ ሆኖ ለሚያጠናቅቅ 10 ሺህ ዶላር ሽልማቱ አብራሪዎቹን ሳባቸው፡፡
ለፉክክሩ ከተመዘገቡት 11 አውሮፕላኖች ሦስቱ በቅድመ ውድድር የሙከራ በረራ ተከሰከሱ፡፡
ሶስቱ አብራሪዎቻቸው በዚሁ አደጋ ሕይወታቸውን አጡ፡፡
ስምንቱ ለዋናው ውድድር ተሠለፉ፡፡
ወደ ዋናው ፉክክር ከገቡት አውሮፕላኖች ሁለቱ ገና እንደተነሱ ተከሰከሱ፡፡
ሁለቱ ከተነሱ በኋላ እምጥ ይግቡ ስምጥ የደረሱበት ጠፋ፡፡
ሁለት አውሮፕላኖች በረራ ከጀመሩ በኋላ በቴክኒክ እክል ተመልሠው አረፉ፡፡
ተመልሰው ያረፉት አውሮፕላኖች ከጥገና በኋላ የጠፉትን ለማፈላለግ ለነፍስ አድን በረራ ተሠማሩ፡፡
የነሱም እጣ ፋንታ ከጠፉት አውሮፕላኖች አልተለየም፡፡ ዳግም አልታዩም፡፡
ስድስት አውሮፕላኖች በመጥፋትና በመከስከስ ወደሙ፡፡
ከሁሉም በላይ አሳዛኙ ለዚህ ውድድሩ በአብራሪነትና ረዳትነት የተሰለፉ በጠቅላላው 10 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ፡፡
በመጨረሻ ከካሊፎርኒያ ኦክላንድ ሐዋይ ሆኖሉሉ በመድረስ ውድድራቸውን በተለያየ የጊዜ ርቀት የጨረሱት ሁለት አውሮፕላኖች ብቻ ነበሩ፡፡
ቁልፍ ቃላት
ምላሽ