top of page
የነሐሴ 9 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#ኮንጎ የኮንጎ ኪንሻሣው የኢቦላ ወረርሽኝ አድማሱን እያሰፋ ነው ተባለ፡፡ ወረርሽኙ ወደ ተጨማሪ ግዛትም መዛመቱን የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከያ እና መቆጣጠሪያ /አፍሪካ CDC/ መረጃ ማሳየቱን አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡ በኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝ ያዳረሳቸው ግዛቶች ብዛት 6 ደርሷል፡፡ ኢቱሪ ወረርሽኙ ከፍተኛ ጫና ያሳደረባት ግዛት ነች፡፡ ወረርሽኙ መቀስቀሱ ከተነገረ 3 ወር ሆኖታል፡፡ እስከ ትናንትም የገደላቸው ሰዎች ብዛት 2 ሺህ 100 ደርሷል፡፡ የኮንጎው ኢቦላ በከፍተኛ የመዛመት ፍጥነት ላይ ነው፡፡ በታሪክም ታላቁ የኢቦላ ወረርሽኝ ሊሆን የሚችልበት እድል የሰፋ ነው ተብሏል፡፡ #ሩሲያ የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭለድሚር ፑቲን በቀጠናዊ የፀጥታ እና ደህንነት ጉዳይ ከሰሜን ኮሪያ ጋር በትብብር እንሰራለን አሉ፡፡ ፑቲን ከሰሜን ኮሪያ ጋር ቀጠናዊ የፀጥታ እና የ
2 days ago2 min read
የነሐሴ 6 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#ደቡብ_አፍሪካ በደቡብ አፍሪካ በአንድ የማዕድን ዝቃጭ ማስወገጃ ስፍራ መደርመስ 14 ሰዎች የሞቱበት አደጋ እየተመረመረ ነው ተባለ፡፡ ሌሎች 8 ሰዎች ደግሞ አካላዊ ጉዳት እንደገጠማቸው ቢቢሲ ፅፏል፡፡፡ በዝቃጩ ውስጥ የተቀበሩ ሌሎች ሰዎች ሳይኖሩ አይቀሩም ተብሏል፡፡ በአደጋው የሞቱት እና አካላዊ ጉዳት የገጠማቸው ሕገ-ወጥ የማዕድን ሰራተኞች መሆናቸው ታውቋል፡፡ አደጋው የደረሰበት ከተዘጋ የቆየ የማዕድን ስፍራ እንደሆነ መረጃው አስታውሷል፡፡ ስፍራው ቀደም ሲል ፕላቲኒየም እና ሌሎችም ማዕድናት ሲመረቱበት የቆየ ነው ተብሏል፡፡ #ሊባኖስ የሊባኖስ ፓርላማ የሞት ቅጣትን የሚያስቀር ህግ አፀደቀ፡፡ የፓርላማው አባላት የሞት ቅጣትን የሚያስቀረውን ህግ ያፀደቁት በአብላጫ ድምፅ እንደሆነ አልጀዚራ ፅፏል፡፡ የሊባኖሱ የፍትህ ሚኒስትር የህጉን መፅደቅ ታሪካዊ ሲሉ
5 days ago2 min read
የነሐሴ 5 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን በጦርነቱ ለተገደሉብን ወታደሮቻችን ካሣ ልትከፍል ይገባል አሉ፡፡ ቀደም ሲል በጦርነቱ አሜሪካ ላደረሰችባት ጉዳት ሁሉ ካሣ እንዲከፈላት የጠየቀችው ኢራን እንደነበረች አልጀዚራ አስታውሷል፡፡ ትራምፕ የተገደሉባቸው የጦር ባልደረቦች ብዛት ባይጠቅሱም እኛም ለተገደሉብን ሰዎች ካሣ እንጠይቃለን ሲሉ በትሩዝ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ እወቁልን ብለዋል፡፡ ትራምፕ አልፈው ተርፈውም የኢራን መንግስት ባለፉት 50 አመታት ለገደላቸው የተቃዋሚዎች ቤተሰቦች ጭምር ካሣ ሊከፍል ይገባዋል ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ተደራዳሪዎቻቸው የካሣ ጥያቄያቸው በወደፊቱ ንግግር በአጀንዳነት እንዲያሲዙላቸው ማዘዛቸው ተሰምቷል፡፡ #ኢራን አብዮታዊ ዘብ የተሰኘው የኢራን የጦር ክፍል ከተተኮሱ በኋላ
6 days ago2 min read
የነሐሴ 1 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#ሳውዲ_አረቢያ የሳውዲ አረቢያው የመከላከያ ሚኒስቴር በቀይ ባህር ለንግድ እና ለጭነት መርከቦች ሰላማዊ ምልልስ ከለላ የሚሰጥ አለም አቀፍ ጥምረት መመስረቱ በቀጠናው የደህንነት ስጋቱን የሚያሳይ ነው አለ፡፡ ሳውዲ አረቢያ እና ሌሎች 13 አገሮች ባለፈው ሳምንት አለም አቀፉን ጥምረት መመስረታቸውን አረብ ኒውስ ፅፏል፡፡ ጥምረቱ የተመሰረው የየመን ሁቲዎች የሳውዲ አረቢያን ወደቦች በሙሉ እንከረቻችምባታለን ብለው ከዛቱ እና በተወሰኑ መርከቦቿ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ሁቲዎቹ በሳውዲ መርከቦች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ገፍተውበታል ተብሏል፡፡ ሳውዲ ከራሷ ባለፈ በአሁኑ ወቅት በኤደን ባህረ ሰላጤ ፣ በባብኤል መንደብ ወሽመጥ እና በመላው ቀይ ባህር ለአለም አቀፍ የንግድ መርከቦች ደህንነት አስጊ እየሆነ መምጣቱን እያጎላቸው ነው፡፡ ርዕሰ ከተማዋ ሰ
Aug 72 min read
የሐምሌ 29 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#አፍጋኒስታን በአፍጋኒስታን የተለያዩ ግዛቶች የደረሰ የጎርፍ አደጋ 29 ሰዎችን ገደለ ተባለ፡፡ አደጋው በ130 ያህል ሌሎች ሰዎች ላይ ደግሞ አካላዊ ጉዳት ማድረሱን አናዶሉ ፅፏል፡፡ 4 ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አልታወቀም ተብሏል፡፡ ጎርፉ በብዙ ቤቶች እና መሰረተ ልማቶች ላይ ውድመት ማስከተሉ ታውቋል፡፡ በአፍጋኒስታን የተለያዩ ግዛቶች የጎርፍ አደጋው የደረሰው በዶፍ ዝናብ ምክንያት እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ በአደጋው ምክንያት ብዙ ሰዎች እርዳታ እንደሚያሻቸው ተነግሯል፡፡ የአለም የጤና ድርጅት 3 ተዘዋዋሪ የጤና ባለሙያዎች ቡድኖችን በማሰማራት ድጋፍ እያደረኩ ነው ማለቱ ተሰምቷል፡፡ #የመን በየመን የውሃ ክልል በመንሳፈፍ ላይ የነበረች መርከብ ፈንጂ በተጫነ ጀልባ ተገጭታ ሰጠመች ተባለ፡፡ መርከቧ ብትሰጥም ሁሉንም 14 ባህረኞቿን ማትረፍ እንደተቻለ አለም አ
Aug 52 min read
የሐምሌ 28 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#የመን አለም አቀፉ ዕውቅና አለው የሚባለው የየመን መንግስት ወታደሮቼ በጣም ብዙ የሁቲ ታጣቂዎችን ገደሉ አለ፡፡ በደፈናው በጣም ብዙ የሁቲ ታጣቂዎችን ሙት እና ቁስለኛ አድርገናል ቢልም ብዛታቸውን በአሃዝ ይሄን ያህል ነው እንዳላለ ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡ የሁቲ ታጣቂዎቹ የተገደሉ በደቡባዊ ምዕራቧ ታይዝ ግዛት በተካሄዱ ውጊያዎች ነው ተብሏል፡፡ በጣም ብዙ ታጣቂዎቻቸው ተገድለዋል ስለመባሉ ሁቲዎቹ ምንም ዓይነት አስተያየት እንዳልሰጡ ተጠቅሷል፡፡ አለም አቀፍ እውቅና አለው የሚባለው የየመን መንግስት መቀመጫው በደቡባዊቱ የወደብ ከተማ ኤደን ነው፡፡ የኢራን ሽርካዎች ናቸው የሚባሉት ሁቲዎቹ ርዕሰ ከተማዋ ሰንዓን ጨምሮ አብዛኛውን የየመን ሰሜናዊ ክፍል ሲያስተዳድሩ ከ10 አመታት በላይ ሆኗቸዋል፡፡ #እስራኤል ሁለት እስራኤላዊያን ሚኒስትሮች ጠቅላይ ሚኒ
Aug 42 min read
የሐምሌ 27 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#ኢራን በኢራን ለጠላት ሲሰልሉ ተደርሶባቸዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በሞት ተቀጡ፡፡ ሁለቱ ሰዎች በሞት የተቀጡት በፍርድ ቤት የእስራኤል ሰላዮች በመሆን ጥፋተኝነታቸው ስለተረጋገጠባቸው ነው መባሉን አልጀዚራ ፅፏል፡፡ በሞት የተቀጡት ግለሰቦች የወታደራዊ እና የደህንነት ተቋማትን መገኛ አመልካች መረጃዎችን ለእስራኤሉ የውጭ የስለላ ተቋም ሞሳድ ባልደረቦች ሲያቀብሉ ነበር ተብሏል፡፡ የፅሁፍ እና የምስል መረጃዎችን ለሞሳድ እንደላኩ ተረጋግጦባቸዋል ተብሏል፡፡ እስራኤል ኢራን ውስጥ የስለላ እጇ በጣሙን የረዘመ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ኢራን ውስጥ ከዚህ ቀደምም ለእስራኤል ሰለላ ሲያቀላጥፉ ነበር የተባሉ በርካታ ሰዎች በሞት መቀጣታቸው መረጃው አስታውሷል፡፡ #ሱዳን በሱዳን ዳርፉር በባህላዊ የፍርድ ስፍራ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት 35 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የሰ
Aug 32 min read
የሐምሌ 24 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#ኮንጎ በኮንጎ ኪንሻሣ በኢቦላ የሚያዙ ሕሙማንና ወረርሽኙ የሚገድላቸው ሰዎች ብዛት በጣሙን እየጨመረ ነው ተባለ፡፡ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠው ሰዎች ብዛት ከ3 ሺህ 400 መብለጡን አናዶሉ ፅፏል፡፡ ወረርሽኙ የገደላቸው ሰዎች ብዛት ከ1 ሺህ 500 በላይ መድረሱ ተነግሯል፡፡ በአገሪቱ በኢቦላ በሽታ የሚያዙ ሰዎች ብዛት በየ20 ቀኑ በእጥፍ እያደገ መምጣቱን የጤና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መረጃ ያሳያል፡፡ ወረርሽኙ የመግደል አቅም ከ44 በመቶ በላይ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ ወረርሽኙ ወደ አዳዲስ ስፍራዎችም በመዛመት ላይ ነው ተብሏል፡፡ በኮንጎ ኪንሻሣ ኢቦላ በወረርሽኝ ደረጃ መቀስቀሱ ከተነገረ ወደ 3ኛ ወሩ ተቃርቧል፡፡ #አሜሪካ ከ130 በላይ የዮርዳኖስ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የአሜሪካ ጦር ከአገሪቱ እንዲወጣላቸው ጥያቄ አቀረቡ፡፡ ተፅዕኖ ፈጣሪዎቹ ቀደም ሲል ከ
Jul 312 min read
የሐምሌ 23 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#ግብፅ በግብፅ የሜዴትራኒያን የባህር ዳርቻ የነበረ የአሜሪካ የጋዝ ማጠራቀሚያ መርከብ በድሮን ተመታ ተባለ፡፡ ሁለት የደህንነት ምንጮች መርከቡ በድሮን እንደተመታ አረጋግጠውልኛል ሲል ሬውተርስ ፅፏል፡፡ መርከቡ በድሮን እንደተመታ በእሳት መያያዙ ታውቋል፡፡ ቃጠሎው ወደ ሌላ መርከብም ተጋብቶ ነበር ተብሏል፡፡ ኋላ ግን ቃጠሎው በቁጥጥር ስር መዋሉ ተጠቅሷል፡፡ በእሳት ተያይዘው የነበሩት መርከቦች ባህረኞች አንዳችም ጉዳት ሳይገጥማቸው እንዲወጡ ተደርጓል ተብሏል፡፡ ለጥቃቱ ሀላፊው እኔ ነኝ ያለ ወገን እንደሌለ መረጃው አስታውሷል፡፡ #ኢራቅ በኢራቅ ካታኢብ ሔዝቦላህ የተሰኘው ታጣቂ ቡድን መንግስት የአገሪቱን ሉአላዊነት ሊያስከብር ይገባል አለ፡፡ ቡድኑ ለመንግስት ያቀረበው ጥያቄ በማስጠንቀቂያ ጭምር የታጀበ እንደሆነ አልጀዚራ ፅፏል፡፡ የቡድኑ ማስጠንቀቂያ የተ
Jul 302 min read
የሐምሌ 22 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#አሜሪካ አሜሪካ እና ሳውዲ አረቢያ ኢራቅ ውስጥ በአፍቃሪ ኢራን ታጣቂዎች ይዞታ ላይ ድብደባ ፈፀሙ፡፡ ሰሞኑን ሳውዲ አረቢያ በኢራቅ የሚገኙ አፍቃሪ ኢራን ታጣቂዎች በድሮን ጥቃት አድርሰውብኛል ስትል እንደነበር አልጀዚራ አስታውሷል፡፡ ሳውዲ ጥቃቱን ከማውገዝ በተጨማሪ መበቀሌ አይቀርም በሚል ዝታ ነበር፡፡ በኢራቆቹ አፍቃሪ ኢራን ታጣቂዎች ላይ አሜሪካ እና ሳውዲ በፈፀሙት ጥምር ድብደባ ከ20 የማያንሱት መገደላቸው ተሰምቷል፡፡ በሌላ መረጃ አብዮታዊ ዘብ የተሰኘው የኢራን የጦር ክፍል በዮርዳኖስ በሚገኝ የአሜሪካ የጦር ተቋም ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሰንዝሬያለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡ የዮርዳኖስ ጦር አምስት ሚሳየሎችን መትቼ አሰናክያለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡ ስለ ዮርዳኖሱ ጥቃት ከአሜሪካ በኩል የተሰጠ አስተያየት የለም፡፡ የወደፊቱን የሆርሙዝ የባህር መተላለፊያ ወሽመ
Jul 292 min read
የሐምሌ 21 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#ጃፓን የጃፓን ደቡባዊ ምዕራብ ክፍል በርዕደ መሬት ተመታ፡፡ ርዕደ መሬቱ የደረሰው ኩማማቶ የተባለው የአገሪቱ ክፍል እንደሆነ ኒኪ እስያ ፅፏል፡፡ የመሬት ነውጡ የተቀሰቀሰው ከምድር በ10 ኪሎ ሜትር ጥልቀት መሆኑ ታውቋል፡፡ ነውጡ በርዕደ መሬት መለኪያ /ሬክተር ስኬል/ 7 ነጥብ 1 ሆኖ መመዝገቡ ታውቋል፡፡ ቀደም ሲል የባህር ማዕበል /ሱናሚ/ ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል ተሰጥቶ የነበረው ማስጠንቀቂያ ወዲያው መታጠፉ ተጠቅሷል፡፡ ያም ሆኖ ሰዎች ራሳቸውን ከባህር ዳርቻዎች እንዲያርቁ ተመክረዋል፡፡ በኩማማቶው ርዕደ መሬት በሰው እና በንብረት ላይ ስለደረሰ ጉዳት የተጠቀሰ ነገር የለም፡፡ በዚሁ ስፍራ ከ10 አመታት በፊት ደርሶ የነበረ ርዕደ መሬት 300 ያህል ሰዎችን እንደገደለ መረጃው አስታውሷል፡፡ #ጋና ጋና ተጨማሪ 1 ሺህ ዜጎቿን ከደቡብ አፍሪካ አስወጣች፡
Jul 282 min read
የሐምሌ 20 የውጭ ሀገር ወሬዎች
#ቀይ_ባህር በቀይ ባህር የባብኤል መንደብ ወሽመጥ የሚተላለፉ መርከቦች ብዛት በእጅጉ እየቀነሰ ነው ተባለ፡፡ በወሽመጡ የሚተላለፉ መርከቦች ብዛት የቀነሰው የየመን ሁቲዎች ባለፈው ሳምንት የሳውዲ አረቢያን ወደቦች እንከቻችምባታለን ብለው ከዛቱ በኋላ እንደሆነ ሬውተርስ ፅፏል፡፡ ለምሳሌም ትናንት በባብኤል መንደብ የባህር ወሽመጥ በኩል ያለፉት የጭነት መርከቦች 11 ብቻ እንደሆኑ የባህር ጉዞ መረጃ አጠናቃሪው የኬፕለር መረጃ ያሳያል፡፡ ይሄም በወሩ በባብኤል መንደብ ወሽመጥ ከተላለፉት መርከቦች ብዛት እጅግ ዝቅተኛው መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ የየመን ሁቲዎች እና ሳውዲ አረቢያ ዳግም ወደ ጦር ፍጥጫቸው ከተመለሱ ሰንብተዋል፡፡ ርዕሰ ከተማዋ ሰንዓን ጨምሮ የየመንን አብዛኛውን ሰሜናዊ ክፍል የሚያስተዳድሩት ሁቲዎቹ የኢራን ሁነኛ የፖለቲካ ሸሪኮች እና የጦር አጋሮች እን
Jul 272 min read
የሐምሌ 18 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#ስፔን በስፔኗ ርዕሰ ከተማ ማድሪድ አቅረቢያ ነዋሪዎች በመዛመት ላይ በሚገኘው ከባድ የሰደድ እሳት ምክንያት ለቅቀው እንደወጡ ታዘዙ፡፡ የማድሪድ ምዕራባዊ ክፍል አቅራቢያ የሰደድ እሳቱ በጣሙን ያየለበት እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ እስከ ትናንት ምሽትም ከ19 ሺህ በላይ ሰዎች ለቀው መውጣታቸው ተጠቅሷል፡፡ በስፔን ወቅታዊ የሰደድ እሳት ምክንያት በአገሪቱ ብሔራዊ የአደጋ ጊዜ መታወጁ ታውቋል፡፡ ፈረንሳይም በሰደድ እሳት መዛመት እየተፈተነች ነው፡፡ የሰደድ እሳቱ በሁለቱም አገሮች ከ220 ሺህ በላይ ሰዎችን የመኖሪያቸው አፈናቅሏል ተብሏል፡፡ በአውሮፓ የሰደድ እሳቱ ለመባባሱ ወቅታዊው የሙቀት ማዕበል በዋና ምክንያትነት እየቀረበ ነው፡፡ #አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቻይና እና ሩሲያ ለኢራን የጦር መሳሪያ እንዳይሰጡም ሆነ እንዳይሸጡ በብርቱ ማ
Jul 251 min read
የሐምሌ 17 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#ብሪታንያ የብሪታንያ መንግስት በኬንያ ላካሂድ የነበረውን አመታዊ የጦር ልምምድን ትቼዋለሁ አለ፡፡ የብሪታንያ ሰራዊት አመታዊ የኬንያ የጦር ልምምዱን የተወው ከምስራቅ አፍሪካዊቱ አገር መንግስት ፈቃድ ባለማግኘቱ ነው መባሉን አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡ የብሪታንያ ጦር ከዚህ ቀደም በኬንያ በየአመቱ በመደበኛነት የጦር ልምምዱን ሲያደርግ መቆየቱን መረጃው አስታውሷል፡፡ የኬንያ መንግስት ለብሪታንያ አመታዊ የጦር ልምምድ ፈቃድ የነሳበት ምክንያት አልተጠቀሰም፡፡ የሚመለከታቸው ሹሞችም ከAFP ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል ተብሏል፡፡ የብሪታንያ ጦር ይሄንኑ አመታዊ ወታደራዊ ልምምዱን በሌላ አፍሪካ አገር ያካሂዳል ተብሏል፡፡ የልምምዱ አስተናጋጅ የአፍሪካ አገር ማን እንደሆነች በስም አልተጠቀሰችም፡፡ #አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ
Jul 242 min read


የኢራን ሹሞች አሜሪካን በሚሳየሎቻችን አትምጪብን አሏት፡፡
ሰኔ 12/2018 - #ዓለም_አቀፍ_ወሬዎች #ኢራን የኢራን ሹሞች አሜሪካን በሚሳየሎቻችን አትምጪብን አሏት፡፡ የኢራን የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ኢስማየል ባጋይ የኢራን የሚሳየል መርሐ ግብር አሜሪካ እና ኢራን በደረሱት የጦርነት ማቆሚያ የመግባቢያ ስምምነት አንድም ስፍራ አልተጠቀሰም ማለታቸውን ሬውተርስ ፅፏል፡፡ ቃል አቀባዩ ሚሳየላችን ለተኩስ እንጂ ለድርድር አይቀርብም ሲሉ መሳለቃቸውም ተሰምቷል፡፡ ከአሜሪካ ሹሞች በኩል የኢራን የሚሳየል መርሐ ግብር የወደፊቱ ድርድር አካል ነው የሚለው አስተያየት እየተደጋገመ ነው ተብሏል፡፡ የኢራን ሹሞች ደግሞ ምንም ቢፈጠር ሚሳየሎቻችን ለድርድር አይቀርቡም የሚል አቋም ይዘዋል፡፡ በመግባቢያ ስምምነቱ ዝርዝር ጉዳዮች ኢራን እና አሜሪካ በ60 ቀናት ውስጥ ድርድር እንደሚያደርጉ በሰነዱ ላይ መስፈሩን መረጃው አስታውሷል፡፡
Jun 192 min read


የአለማችን የሙቀት መጠን በእጅጉ እየጨመረ እንደሚመጣ የሳይንስ ሊቃውንት አስጠነቀቁ፡፡
ግንቦት 26/2018 - ዓለም አቀፍ ወሬዎች #ኤልኒኖ የአለማችን የሙቀት መጠን በእጅጉ እየጨመረ እንደሚመጣ የሳይንስ ሊቃውንት አስጠነቀቁ፡፡ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በብዙ የአለማችን ክፍሎች እንደሚመዘገብ አለም አቀፉ የአየር ሁኔታ ተከታታይ መስሪያ ቤት ማስጠንቀቁን ቢቢሲ ፅፏል፡፡ ኤል ኒኖ የተሰኘው የአየር ለውጥ ክስተት የከፍተኛ ሙቀት ጭማሪው ምክንያት መሆኑ ታውቋል፡፡ ከወዲሁም የሙቀት መጠን ጭማሪው መከሰቱን መረጃው አስታውሷል፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ደግሞ የሙቀት መጠን ጭማሪው እየተጠናከረ ይመጣል ተብላል፡፡ የሙቀት መጠን ጭማሪው ደረጃ ሊቃውንቱን ከወዲሁ በእጅጉ እያሳሰበ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ የአየር ለውጡን ተፅዕኖ ለመገደብ ሲወተወት ቢቆይም ችግሩ ከእርምጃው እየገዘፈ መምጣቱ ይነገራል፡፡ #አሜሪካ የአሜሪካ ጦር በኢራን ኬሽም ደሴት ላይ ያነጣጠረ
Jun 32 min read


ግንቦት 20/2018 - ዓለም አቀፍ ወሬዎች
#ፍልስጤም የፍልስጤማውያኑ ታጣቂ ቡድን (ሐማስ) የወታደራዊ ክንፉ የበላይ ሞሐመድ አውዳ በእስራኤል ጥቃት መገደሉ እውነት ነው አለ፡፡ ሞሐመድ አውዳ የተገደለው እስራኤል በጋዛ ከተማ በፈፀመችው የአየር ጥቃት እንደሆነ TRT ዎርልድ ጽፏል፡፡ ከሐማሱ የወታደራዊ ክንፍ አዛዥ ጋር በጥቃቱ ባለቤቱ እና ሁለት ልጆቹ መገደላቸው ታውቋል፡፡ አውዳ ከሐማስ መስራቾች አንዱ እንደነበር በቡድኑ መግለጫ ተጠቅሷል፡፡ ሞሐመድ አውዳ በሐማስ ወታደራዊ ክንፍ የበላይነት የተሰየመው በቅርቡ እንደነበር መረጃው አስታውሷል፡፡ እስራኤል የጋዛ የጦር ዘመቻዋን ከጀመረች ወዲህ በርካታ ስመ ጥር የሐማስ ወታደራዊ አዛዦችን መግደሏን መረጃው አስታውሷል፡፡ #ጋና ምዕራብ አፍሪካዊቱ ጋና ከደቡብ አፍሪካ ዜጎቿን ማስወጣት ጀመረች፡፡ በደቡብ አፍሪካ በውጭ ተወላጅ አፍሪካውያን ላይ ያነጣጠረው
May 282 min read


አሜሪካ የሆርሙዝን የባህር መተላለፊያ ወሽመጥ እና የኢራንን ወደቦች መዝጋቷን ቻይና በጥብቅ ተቃወመችው፡፡
ሚያዝያ 7/2018 - ዓለም አቀፍ ወሬዎች #አሜሪካ አሜሪካ የሆርሙዝን የባህር መተላለፊያ ወሽመጥ እና የኢራንን ወደቦች መዝጋቷን ቻይና በጥብቅ ተቃወመችው፡፡ እስያዊቱ አገር የአሜሪካን እርምጃ አደገኛ ነው እንዳለችው አናዶሉ ፅፏል፡፡ ሀላፊነት የጎደለውም ስትል ጠርታዋለች፡፡ የቻይና የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአሜሪካ የባህር ወሽመጡን መዝጋት ውጥረቱን ይበልጥ የሚያባብስ ነው የሚል መግለጫ አውጥቷል፡፡ የቻይናው የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ለችግሩ መቃለል ዘላቂ እና አጠቃላይ የተኩስ አቁም የሚደረግበት መላ ቢፈለግ የተሻለ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የሆርሙዝ ሰርጥ ጉዳይ በአለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ አቅርቦቱን ችግር እያባባሰው መምጣቱ ይነገራል፡፡ አሜሪካ የባህር መተላለፊያ ወሽመጡን ከሰኞ ቀን 8 ሰዓት አንስቶ ዘግቼዋለሁ ማለቷን መረጃው አስታውሷል፡፡ #ናይጀር
Apr 151 min read


መጋቢት 28/2018 - ዓለም አቀፍ ወሬዎች
#ፍልስጤም የፍልስጤማውያኑ የጦር እና የፖለቲካ ድርጅት (ሐማስ) የእስራኤል ጦር በጋዛ የሚፈፀመውን ጥቃት አቁሞ ጠቅልሎ ካልወጣ በስተቀር በጭራሽ ትጥቅ አልፈታም አለ፡፡ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለጋዛ ሰርጥ የወደፊት ሰላም ቀደም ሲል ያቀረቡት ባለ 20 ነጥቦች የሰላም እቅድ ሐማስ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ እንዲፈታ የሚጠይቅ መሆኑን ሬውተርስ አስታውሷል፡፡ የሐማስ የበላዮች በዚህ ጉዳይ ትናንት ከአደራዳሪዎቹ ጋር መመካከራቸው ተሰምቷል፡፡ ይሄን ተከትሎም የሀማስ ወታደራዊ ክንፍ ቃል አቀባይ አቡ ኦባይዳ የእስራኤል ጦር ከመንፈቅ በፊት በተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት የጋዛ ሰርጥን ለቅቆ ካልወጣ በስተቀር በጭራሽ ትጥቅ አንፈታም ብለዋል፡፡ በጋዛ የወደፊት ዘላቂ ስለማለቱ የሐማስ ትጥቅ መፍታት ነገር በጣሙን አስቸጋሪው ጉዳይ እንደሆነ ይነገራል
Apr 62 min read


መጋቢት 22/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ጀርመን በጀርመን ከሚኖሩ ስደተኞች 80 በመቶዎቹ ወደ አገራቸው እንደሚሸኙ መራሄ መንግስት ፍሬድሪክ ሜርዝ ተናገሩ፡፡ ሶሪያውያኑ ስደተኞች በመጪዎቹ 3 አመታት ከጀርመን ወደ አገራቸው ይሸኛሉ መባሉን ቢቢሲ ፅፏል፡፡ መራሄ መንግስት ሜርዝ 80 በመቶዎቹ ሶሪያውያን ስደተኞች በ3 አመታት ጊዜ ወደ አገራቸው እንደሚሸኙ እወቁልን ያሉት ከሶሪያው ጊዜያዊ ርዕሰ ብሔር አህመድ አልሻራ ጋር በበርሊን ከተነጋገሩ በኋላ ነው ተብሏል፡፡ ብዙዎቹ ሶሪያውያን ስደተኞች ጀርመን የገቡት በአገራቸው ተቀስቅሶ የነበረው ውስብስብ የእርስ በርስ ጦርነት በተፋፋመበት ወቅት ነበር፡፡ አሁን ስደተኞቹን ከጀርመን መመለስ ይጀመራል ቢባልም ዝርዝሩ ገና አልታወቀም፡፡ ሶሪያ በአሁኑ ወቅት ከ10 ዓመት በፊት ከነበረው በእጅጉ የተሻለ ፀጥታ እንደሚስተዋልባት መረጃው አስታውሷል፡፡ #አሜሪካ አ
Mar 312 min read


የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአገራቸው ጦር የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ዘይት መናኸሪያ የሆነውን የካርግ ደሴት ሊይዝ እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ፡፡
መጋቢት 21/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአገራቸው ጦር የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ዘይት መናኸሪያ የሆነውን የካርግ ደሴት ሊይዝ እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ፡፡ የካርግ ደሴት የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ዘይት ማምረቻ እና ለውጭ ገበያ ከታለመው ነዳጅ 90 በመቶው የሚላከው ከዚሁ ደሴት እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ ከወር በላይ ባስቆጠረው የኢራን ጦርነት ምክንያት በአለም ዙሪያ የነዳጅ ዘይት ዋጋ በጣሙን እያሻቀበ ነው ተብሏል፡፡ ኢራን በኢስፍሐን ዩኒቨርስቲ ላይ ለተፈፀመባት ጥቃት በእስራኤል እና በባሕረ ሰላጤው አገሮች በሚገኙ የአሜሪካ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ የአፀፋ ጥቃት እንደምታደርስ ዝታለች፡፡ ኢራን በእስራኤል ደቡባዊ ክፍል የኢንዱስትሪዎች መገኛ ላይ በፈፀመችው የሚሳየል ድብደባ ከባድ ቃጠሎ መድረሱ ታውቋል፡፡
Mar 302 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page
_edited.jpg)
