ታህሳስ 21፣ 2012/ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከህግ ውጪ የተገነቡ ቤቶች ላይ እርምጃ እንደምወስድ እወቁት ብሏል
በከተማዋ ባሉ ሁሉም ወረዳዎች ህገ-ወጥ የቤት ግንባታዎችን እየለየ መሆኑንም አስተዳደሩ በፌስቡክ ገጹ ላይ ፅፎት ተመልክተናል፡፡እርምጃውን ጥር 2፣ 2012 እንደሚጀምርም በመረጃው ጠቅሷል፡፡በከተማዋ ባሉ 116 ወረዳዎች እወስደዋለሁ ባለው እርምጃ የአዲስ አበባ፣ የፌደራልና የኦሮሚያ ፖሊሶች እንዲሁም የከተማዋ አጎራባች ወረዳዎች ይሳተፋሉ ብሏል፡፡
ይህ እርምጃ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተስፋፋ ያለውን ህገ-ወጥ የመሬት ወረራ ለመከላከል እንደሚያስችለውም የከተማ አስተዳደሩ ጠቅሶታል፡፡አዲስ አበባ ውስጥ ክፍት ቦታዎች በህገ-ወጥ መንገድ እየታጠሩ ነው ያለው አስተዳደሩ ከላስቲክ ቤቶች ጀምሮ የተለያዩ ግንባታዎች እየተካሄዱ መሆናቸውን ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡
ይህ እርምጃ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተስፋፋ ያለውን ህገ-ወጥ የመሬት ወረራ ለመከላከል እንደሚያስችለውም የከተማ አስተዳደሩ ጠቅሶታል፡፡አዲስ አበባ ውስጥ ክፍት ቦታዎች በህገ-ወጥ መንገድ እየታጠሩ ነው ያለው አስተዳደሩ ከላስቲክ ቤቶች ጀምሮ የተለያዩ ግንባታዎች እየተካሄዱ መሆናቸውን ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡
- ተጨማሪ ያንብቡ about ታህሳስ 21፣ 2012/ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከህግ ውጪ የተገነቡ ቤቶች ላይ እርምጃ እንደምወስድ እወቁት ብሏል
- 1 ጊዜ የታየ