ቢዝነስ ወሬ

ህዳር 24፣ 2014- አሁን በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ መያዝ ባለበት ጊዜ በከተማው ግን ከ1.5 እስከ 20 ሚሊየን ብር የሚሸጡ መኪናዎች ደረታቸውን ገልብጠው የሚዛቸውን ኢትዮጵያዊ ይጠብቃሉ

አሁን በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ መያዝ ባለበት ጊዜ በከተማው ግን ከ1.5 እስከ 20 ሚሊየን ብር የሚሸጡ መኪናዎች ደረታቸውን ገልብጠው የሚዛቸውን ኢትዮጵያዊ ይጠብቃሉ፡፡ 

ሻፓኙም፣ ውስኪውም እንደ ልብ ይጨለጣል፡፡ 

ይህ ምን ይነግረናል? 

ምላሽ

መስከረም 20፣ 2014- በዛሬው የገበያ ቅኝት መሰናዶዓችን በአዲስ አበባ ከተማ በስፋት እየተለመደ የመጣውን የእሁድ ገበያ እንቃኛለን

በዛሬው የገበያ ቅኝት መሰናዶዓችን በአዲስ አበባ ከተማ በስፋት እየተለመደ የመጣውን የእሁድ ገበያ እንቃኛለን፡፡ 

በቀደሙት ዓመታት በአብዛኛው አልባሳት ብቻ ይሸጡባቸው የነበሩት የእሁድ ገበያዎች አሁን አሁን ለገበያ የሚቀርቡት ሸቀጦች በዓይነትም እየሰፉ መኾኑን ሸገር ተመልክቷል፡፡ 

ምላሽ

ታህሳስ 20፣ 2014- አባይ ባንክ የዲያስፖራውን ወደ ሀገር ቤት መምጣት መነሻ አድርጎ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል የድጋፍ መርኃ ግብር አዘጋጅቻለሁ አለ

አባይ ባንክ የዲያስፖራውን ወደ ሀገር ቤት መምጣት መነሻ አድርጎ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል የድጋፍ መርኃ ግብር አዘጋጅቻለሁ አለ፡፡

መርኃ ግብሩ “አንድ ብር ለአንድ ዶላር፡፡ ይመንዝሩ! ይደግፉ!” በሚል የሚካሄድ መኾኑን ባንኩ ለሸገር ነግሯል፡፡ 

የመርኃ ግብር ዓላማ ከውጭ የሚገቡ የሀገር ልጆች በእጃቸው የያዙትን የውጭ ምንዛሪ በባንኩ ሲመነዝሩ፣ ከእያንዳንዱ ዶላር ወይም የውጭ ምንዛሪ አንድ ብር በጦርነቱ ሰበብ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ማድረግ ነው ተብሏል፡፡

አባይ ባንክ በዚሁ መርኃ ግብር የሚገኘው የውጭ ምንዛሪ ለሀገር ይበጃል፣ ከእያንዳንዱ ብር ምንዛሪ ደግሞ ለተፈናቀሉ የሀገር ልጆች ለመደገፍ ያግዛል ብሏል፡፡

ምላሽ

ታህሳስ 13፣ 2014- ከሳምንታት በፊት መንግሥት በዛ ያሉ አልባሳትና የግል መጠቀሚያዎችን በሻንጣ ይዘው ለሚገቡ መንገደኞች ሰጥቶት የነበረውን የቀረጥ ነጻ ፈቃድ ማንሳቱ ይታወሳል፡

ከሳምንታት በፊት መንግሥት በዛ ያሉ አልባሳትና የግል መጠቀሚያዎችን በሻንጣ ይዘው ለሚገቡ መንገደኞች ሰጥቶት የነበረውን የቀረጥ ነጻ ፈቃድ ማንሳቱ ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎ በአልባሳት ገበያ ላይ የተፈጠረ አዲስ ነገር ይኖር ይኾን?

ማህሌት ኤርሲዶ ወደ መርካቶ ጎራ ብላ የአልባሳት ነጋዴዎችን አነጋግራለች፡፡

ምላሽ
2022-01-28
በኢትዮጵያ የቡና ግብይት ውስጥ የደላሎች ሰንሰለት በመሰበሩ ከቡና የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ ገቢ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ ተሰማ…
2022-01-28
ሙሉ ገቢው ለተፈናቃይ ወገኖች የሚውል የሙዚቃ ቪዲዮ ዛሬ ይመረቃል፡፡ አዘጋጁ ፒያኒስት ግርማ ይፍራሸዋ ነው፡፡
2022-01-28
የውሃ ልማት ፈንድ ለንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እና ለጤና አጠባበቅ አገልግሎት ማሻሻያ ብድር ያቀረብኩላቸው ከተሞች ብድሩን…
2022-01-28
የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጌአለሁ ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ…