ታሪክን የኌሊት

ታሪክን የኌሊት-ነሐሴ 12፣2012/ከ180 ዓመት በፊት በዛሬዋ ቀን የተወለዱት እቴጌ ጣይቱ ብጡል

በሀገር አስተዳደር፣ ከውጭ ወራሪዎችን በመዋጋት፣ከፍ ያለ ያመራር ተሳትፎ እንዳላቸው ታሪክ የመዘገበላቸው እቴጌ ጣይቱ የተወለዱት ከ180 ዓመታት በፊት በዛሬው ቀን ነበር፡፡

እቴጌ ጣይ ብጡል በ1832 ዓ.ም. ወሎ በየጁ አካባቢ ተወለዱ፡፡ በጊዜው የነበረውንና ለሴቶች ደረጃ የሚፈቀደውን፣ የመፃፍና የማንበብ ትምህርት ተምረዋል፡፡

ወይዘሮ  ጣይቱ፣ አራተኛቸው የሆኑትን ባላቸውን ዳግማዊ አፄ ምንይልክን ካገቡ በኋላ በሃገራዊ ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ የሚታወቁ ሆነዋል፡፡

እንደርሳቸው ሁሉ ነሐሴ 12 የተወለዱትና በአራት ዓመታት የሚልቋቸው አፄ ምንሊክን ካገቡ በኋላ የእቴጌነት ማዕረግ አግኝተዋል፡፡ 

ምላሽ

ግንቦት 13-ታሪክን የኌሊት/ ኢትዮጵያን፣ ለ17 አመታት እንደፈቀዱና እንደፈለጉ ሲገዙና ሲነዱ የነበሩት ኮሎኔል መንግስቱ ሀይለማርያም፣ የተቃዋሚ የጦር ሀይል ወደ አዲስ አበባ ሲቃረብ፣ ሸሽተው ከሀገር የወጡት የዛሬ 29 ዓመት ልክ በዛሬው ቀን ነበር

ኢትዮጵያን፣ ለ17 አመታት እንደፈቀዱና እንደፈለጉ ሲገዙና ሲነዱ የነበሩት ኮሎኔል መንግስቱ ሀይለማርያም፣ የተቃዋሚ የጦር ሀይል ወደ አዲስ አበባ ሲቃረብ፣ ሸሽተው ከሀገር የወጡት የዛሬ 29 ዓመት ልክ በዛሬው ቀን ነበር፡፡ 

እለቱ ማክሰኞ ነበር፡፡ በስድስት ሰዓቱ የኢትዮጵያ ሬዲዮ የዜና እወጃ፣ በሀገሪቱ የነበረውን ደም ማፈሰስ ለማስቆም ሲባል ፕሬዚዳንት መንግስቱ ከሀገር እንዲወጡ መደረጉን ተናገረ፡፡ በማግስቱ ግን ለማንም ሳያሳውቁ ሸሸተው፣ መሄዳቸውን የመንግስት ምክር ቤት መግለጫ ሰጠ፡፡

ሌፍተናንት ጀነራል ተስፋዬ ገ/ኪዳንም የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው  የተሰየሙት በዛሬው ቀን ነበር፡፡

ሌተና ኮሎኔል መንግስቱ፣ የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ አመፅ በአዝጋሚ መፈንቅለ መንግስት እጁ ያደረገው ወታደራዊ ጁንታ (ደርግ) ሊቀመንበር ነበሩ፡፡ 

ምላሽ

ታሪክን የኋሊት/ በኢትዮጵያ የዛሬ 46 አመት በዛሬው ቀን የገጠር መሬት አዋጅ ታወጀ

በኢትዮጵያ የዛሬ 46 አመት በዛሬው ቀን የገጠር መሬት አዋጅ ታወጀ፡፡

የካቲት 25 ቀን 1967 የወጣው የመሬት አዋጅ ከዚያ በፊት ሰፍኖ የቆየውን የመሬት አጠቃቀምና ስሪት ለውጦ ከባለርስቱ ወደ አራሹ ገበሬ ያዛወረ አዋጅ ነበር፡፡

የመሬትን ባለቤትነት ላራሹ የማድረግ አስፈላጊነት ጥያቄ በጊዜው ለነበረው ንጉሳዊ መንግስት ከተለያዩ ክፍሎች ሲቀርብ ቆይቷል፡፡

ገበሬዎች በሰላማዊና በአመፅ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል፡፡

የጊዜው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችም በተደራጀ መልኩ በአመፅ ጥያቄውን ሲያነሱ ቆይተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ያለው የመሬት ስሪት ፣ በርስትነት በገባርነት የሚያዝ ሆኖ ቆይቷል፡፡

ምላሽ

ታሪክን የኋሊት/ የዛሬ 84 ዓመት፣ የካቲት 12 ለኢትዮጵያ የፅልመት ቀን ነበር

የዛሬ 84 ዓመት፣ የካቲት 12 ለኢትዮጵያ የፅልመት ቀን ነበር፡፡ 

የስቃይና የመከራ ውርጅብኝ በኢትዮጵያዊነታቸው ብቻ የተቀበሉበት ቀን ነበር፡፡ 

1929 የካቲት 12 ቀን፣ የዋለው አርብ ነበር፡፡ 

የኢጣሊያው ልዑል ልጅ በመውለዱ፣ ለልደቷ ክብር፣ ለድሆች ምፅዋት ይሰጣል፤ ተብሎ ተለፈፈ፡፡ 

በዛሬው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በዚያን ጊዜው ገነት ልዑል ቤተ-መንግሥት፤ ድሆችና ታዋቂ የከተማ ነዋሪዎች ተጠርተዋል፡፡ 

ሰዓቱ በግምት ከረፋዱ 4፡00 ይሆናል፡፡ 

ምላሽ

ታሪክን የኋሊት -ጥር 18፣ 2013

ኢጣሊያኖች፤ ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛቷ ለማድረግ ወረራ በጀመረችበት ወቅት የመጀመሪያው የመከላከል ጦርነትና ሽንፈት የገጠማት ዶጋሊ ላይ ነበር፡፡

የአሁኗ “ኤርትራ” የዚያን ጊዜዋን ባሕረ ነጋሽ  የሚያስተዳደሩት ራስ አሉላ አባ ነጋና ሰራዊታቸው የኢጣሊያን ወራሪ ኃይል ተዋግተው ድል ያደረጉት የዛሬ 134 ዓመት  በዛሬው ቀን ነበር፡፡

ምፅዋን የተቆጣጠሩት ቱርኮች ተዳክመው በነበረበት ጊዜ በእንግሊዞች ርዳታ ግብፆች እንዲተኩዋቸው ተደረገ፡፡ ይሁንና ግብጾች ፤ በሱዳኖች ወይም በድርቡሾች ተቃውሞ በጦር ሀይል ስለተመቱ አቅም አነሳቸው፡፡

በከሰላም የግብፅ ሃይል በሱዳኞቹ ተከቦ ለእልቂት በተቃረበበት ወቅት እንግሊዞች ጣልቃ ገቡ፡፡ እንግሊዞቹ ወደ ኢትዮጵያው ንጉስ ነገስት አፄ ዮሐንስ መልዕክተኛ ልከው ስምምነቱ እንዲፈረም አደረጉ፡፡

ምላሽ

ታሪክን የኋሊት- ህዳር 14፣2013/ በኢትዮጵያ ታሪክ ብዙ አሰቃቂ የግፍና የግድያ ትውስታዎች ተመዝግበዋል

በኢትዮጵያ ታሪክ ብዙ አሰቃቂ የግፍና የግድያ ትውስታዎች ተመዝግበዋል፡፡ 

ነገር ግን ከዛሬ 46 ዓመታት በፊት የወታደራዊው አስተዳደር ደርግ በንፁሃን ዜጎች ላይ የፈፀመው ግድያ በአስቃቂነቱና በነውረኛነቱ ቀዳሚ ሆኖ ይጠቀሳል፡፡ 

በ1967 ህዳር 14 ቀን ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ አምባገነኑ ወታደራዊ መንግስት 60 የሚሆኑ የቀድሞው መንግስት ባለስልጣኖችንና ወታደራዊ መኰንኖች ያለፍርድ በግፍ ገደላቸው፡፡ 

በጥቂት መኮንኖችና በአብዛኛው የበታች ሹማምንት ስብሰብ የተዋቀረው ወታደራዊ ደርግ በእጃቸው መከላከያ የሌላቸውንና በቁጥጥሩ ስር ያደረጋቸውን ባለስልጣናትና ወታደራዊ መኮንኖችን ገድሎ በቀድሞው የአዲስ አበባ ወህኒ ቤት ግቢ ውስጥ በጅምላ ቀበራቸው፡፡

ምላሽ

ታሪክን የኋሊት- መስከረም 12፣ 2013/ የጀርመን ናዚዎች የወረራቸውን ማሟሻ ያደረጉት የዛን ጊዜዋን ቼኮዝሎቫኪያ ሱዴትን ግዛት በወረራ በመያዝ ነው

የጀርመን ናዚዎች አለምን የመቆጣጠር ክፉ ሀሳብ ባደረባቸው ጊዜ የወረራቸውን ማሟሻ ያደረጉት የዛን ጊዜዋን ቼኮዝሎቫኪያ ሱዴትን ግዛት በወረራ በመያዝ ነው፡፡  

የኔነህ ከበደ ፅፎ አዘጋጅቶታል ወንድሙ ሀይሉ ያቀርበዋል፡፡

ምላሽ

ነሐሴ 14፣ 2012/ ከዛሬ 8 ዓመት በፊት፣ በዛሬው ቀን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አረፉ

ከዛሬ 8 ዓመት በፊት፣ በዛሬው ቀን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አረፉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕክምና ከሚያደርጉበት ብራስልስ ማረፋቸው በመገናኛ ብዙሃን የተነገረው ነሐሴ 14/2004 ዓ/ም ነበር፡፡

አቶ መለስ ሹመታቸው ላይ እንዳሉ የሞቱ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው፡፡

አቶ መለስ ዜናዊ በትጥቅ ትግል የመንግስትነት ስልጣን የተቆጣጠረው ኢሕአዴግ ሊቀመንበር በመሆናቸው የሃገሪቱ መሪ ለመሆን በቅተዋል፡፡

በመጀመሪያ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሆነው ቆይተው በሕገ-መንግስቱ በተሰጠው ድንጋጌ መሰረት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ለ21 ዓመታት ኢትዮጵያን መርተዋል፡፡

ምላሽ

ታሪክን የኋሊት/ ከዛሬ 131 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን አፄ ዮሐንስ በመተማው ጦርነት አረፉ

የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት አፄ ዮሐንስ 4ኛ በወረራ መተማንና አልፎም እስከ ሳር ውሃ ተቆጣጥሮ የነበረውን የሱዳን ሰራዊት ለመዋጋት ወደ መተማ ዘመቱ፡፡አፄ ዮሐንስ ወደ መተማ ሰራዊታቸውን አስከትለው የሄዱት፣ ሰሃጢ ላይ ከጣሊያኖች ጋር የነበራቸውን ፍጥጫ ትተው ነው፡፡ሰሃጢ ላይ፣ ጣሊያኖችን ከምፅዋ ምድር ለማስወጣት ዘምተው ሳለ ድርቡሾች (የሱዳን ጦር) ወሰን አልፎ መያዙን ሰሙ፡፡ወረራውን እንደሰሙ በንጉስ ተክለ ሃይማኖት የሚመራው የጐጃም ጦር የሱዳንን ወታደሮች እርምጃ እንዲቆጣጠር አዘዙ፡፡
ምላሽ
ወሬ መለያዎች
Reset filters
2021-04-20
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5,833 የላብራቶሪ ምርመራ 1,603 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡…
2021-04-20
የአንበጣ መንጋን ለመከላከል በ12 አውሮፕላኖችና በ8 ሂሊኮፕተሮች የኬሚካል እርጭት እየተደረገ ነው፡፡
2021-04-20
በመተከል ዞን ያለው የፀጥታ ችግር የቀይ መስቀልን ሰብአዊ ድጋፍ አስተጓጉሎታል ተባለ፡፡
2021-04-20
የሊቢያን ምርጫ በተመለከተ የፀጥታው ምክር ቤት ሰሞኑን ያሳለፈውን ውሳኔ የአገሪቱ ከፍተኛ መንግስታዊ ምክር ቤት በደስታ…
2021-04-20
በአጣዬና አካባቢዋ ስጋቱ እንዳለ ቢሆንም ዛሬ የተሻለ ሰላም መኖሩ ተሰማ፡፡  ለተፈናቀሉትም ከአካባቢው ማህበረሰብ የእለት…
2021-04-20
በቻድ አማፂያን ከሁለት አቅጣጫዎች ወደ ርዕሰ ከተማዋ እንጃሚና እየተቃረቡ ነው ተባለ፡፡ አማጺያኑ ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢን…