የአገር ውስጥ ወሬ

ህዳር 24፣ 2014- ኢትዮጵያ በህግ አውጪ አካሏ ሽብርተኛ ብላ የፈረጀችውን ሕወሃት መዋጋት ከጀመረች 1 ዓመት አልፏታል

ኢትዮጵያ በህግ አውጪ አካሏ ሽብርተኛ ብላ የፈረጀችውን ሕወሃት መዋጋት ከጀመረች 1 ዓመት አልፏታል፡፡

ጦርነቱ፣ ውጊያው የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ቀልብ ሊባል በሚችል መልኩ ቀልብ ወጥሮ የያዘ ነው፤ የታዳጊዎችንም ጭምር፡፡

ታዳጊዎች የጦር ሜዳ ውሎዎችን ሲመለከቱ፤ ምን ይሰማቸዋል? 

ሲሰሙ አስተሳሰባቸው ላይስ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ይኖረው ይሆን? 
 

ምላሽ

ህዳር 24፣ 2014- ኢትዮጵያ በህግ አውጪ አካሏ ሽብርተኛ ብላ የፈረጀችውን ሕወሃት መዋጋት ከጀመረች 1 ዓመት አልፏታል

ኢትዮጵያ በህግ አውጪ አካሏ ሽብርተኛ ብላ የፈረጀችውን ሕወሃት መዋጋት ከጀመረች 1 ዓመት አልፏታል፡፡

ጦርነቱ፣ ውጊያው የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ቀልብ ሊባል በሚችል መልኩ ቀልብ ወጥሮ የያዘ ነው፤ የታዳጊዎችንም ጭምር፡፡

ታዳጊዎች የጦር ሜዳ ውሎዎችን ሲመለከቱ፤ ምን ይሰማቸዋል? 

ሲሰሙ አስተሳሰባቸው ላይስ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ይኖረው ይሆን? 
 

ምላሽ

ህዳር 24፣ 2014-ትልቁ የፋይናንስ ተቋም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ “አይዞን ኢትዮጵያ” በተባለ መላ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ3 ሚሊየን ዶላር በላይ ሰበሰብኩ አለ

ትልቁ የፋይናንስ ተቋም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ “አይዞን ኢትዮጵያ” በተባለ መላ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ3 ሚሊየን ዶላር በላይ ሰበሰብኩ አለ፡፡

የተገኘው የውጭ ምንዛሬው ባስፈላጊው ጊዜ የተገኘ ነው ተብሏል፡፡

የውጭ ምንዛሬው በጥቂት ሳምንታት ውስጥም የተገኘ ነው ተብሏል፡፡

ለኢትዮጵያ ያሰቡ የኢትዮጵያ ወዳጆች አገራቸውን አይዞሽ በማለት የላኩት የአገር ልጆች 13 ሺህ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡

ከአሜሪካ 87 በመቶ ከቀረው አለም ደግሞ 23 በመቶ የመጣ መሆኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ ነግረውናል፡፡

ምላሽ

ህዳር 23፣ 2014- ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ በምስራቅና በምዕራብ የተገኘው የኢትዮጵያ የሰራዊት ድል በመሃል ሃገርም እንደሚደገም ተናገሩ

ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ በምስራቅና በምዕራብ የተገኘው የኢትዮጵያ የሰራዊት ድል በመሃል ሃገርም እንደሚደገም ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጦር ግንባ በብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣብያው ባስተላለፉት መልዕክት ነው ይሄንን ያሉት፡፡

ምላሽ

ህዳር 23፣ 2014- የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዲስ አበባ የጠቅላይ ሚኒስትሩን በታህሳስ አጋማሽ በጥር መጀመሪያ አዲስ አበባ እንገናኝ የሚለውን ጥሪ በተመለከተ ወደ አገር ቤት ለሚመጡ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ቅናሽ ያለበት መስተንግዶ እንደሚሰጥ ሲል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተናገረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዲስ አበባ የጠቅላይ ሚኒስትሩን በታህሳስ አጋማሽ በጥር መጀመሪያ አዲስ አበባ እንገናኝ የሚለውን ጥሪ በተመለከተ ወደ አገር ቤት ለሚመጡ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ቅናሽ ያለበት መስተንግዶ እንደሚሰጥ ተናገረ፡፡

አየር መንገዱ ከአውሮፓ ፣ ከሰሜን አሜሪካ እና ኬሎችም ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገር ቤት እንዲገቡ በእኔ በኩል ከሚመለከታቸው ጋር የሚፈለገውን ሁሉ እያደረኩ ነው ብሏል፡፡ 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየር ትኬት ቅናሽና ተጨማሪ የሻንጣ የኪሎ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሰምተናል፡፡

አየር መንገዱ የማይበርበትም ሥፍራ ቢኖር፣ ገበያውን ለማምጣት እንደሚሰራ ከአየር መንገዱ ምንጫችን ሰምተናል።

ምላሽ

ህዳር 22፣2014-ሰበር ወሬ/ የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና ፋኖ ታሪካዊቷን የላስታ ላሊበላ ከተማ እና የላሊበላ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን መቆጣጠራቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ተናገረ

ሰበር ወሬ 

የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና ፋኖ ታሪካዊቷን የላስታ ላሊበላ ከተማ እና የላሊበላ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን መቆጣጠራቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ተናገረ።

አገልግሎቱ ማምሻውን ይፋ ባደረገው ሰበር ዜና፣ "በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙባትን የላሊበላ ከተማንና ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያውን ለመቆጣጠር የተቻለው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መሪነት በየግንባሩ የተጀመረው ማጥቃት ውጤት ማስመዝገብ በመቻሉ ነው" ብሏል።

አገልግሎቱ አክሎም፣ "ጀግኖቹ የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ የላስታ ላሊበላን አካባቢ በማጽዳት የሰቆጣ ከተማን ለመቆጣጠር ወደፊት እየገሠገሡ ነው" ብሏል።

ምላሽ

ህዳር 22፣ 2014- ሰበር ወሬ/በጋሸና፣ በመዘዞና በወራኢሉ የጦር ግንባሮች በአሸባሪው በሕወሓት ቁጥጥር የነበሩ ከተሞች ነፃ መውጣታቸው ተሰማ

ሰበር ወሬ

በጋሸና፣ በመዘዞና በወራኢሉ የጦር ግንባሮች በአሸባሪው በሕወሓት ቁጥጥር የነበሩ ከተሞች ነፃ መውጣታቸው ተሰማ፡፡

ድሉ የተመዘገበው የመከላከያ፣ የልዩ ኃይል፣ የሚሊሺያና የፋኖ አባሎች ባደረጉት የጥምረት ዘመቻ መሆኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ተናግረዋል፡፡

የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር አቶ ለገሠ ቱሉ ያስተላለፉትን መልዕክት ሙሉ ቃል ቀጥሎ እናቀርባለን፡፡
 

ምላሽ

ህዳር 20፣ 2014- ዶ/ር እሌኒ ገመድህን ከገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪዎች ምክር ቤት አባልነታቸው መነሳታቸው ተሰማ

ዶ/ር እሌኒ ገ/መድህን ከገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪዎች ምክር ቤት አባልነታቸው መነሳታቸው ተሰማ፡፡ 

የፕላንና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር የዶ/ር እሌኒ ገ/መድህንን ከገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪዎች ም/ቤት አባልነት መነሳትን አስመልክቶ ትላንትና መግለጫ ሰጥቷል፡፡ 

 

ምላሽ
ወሬ መለያዎች
Reset filters
2021-12-04
መሠረታዊ የሚባሉና ዜጎችን የሚጠቅሙ የጤና መረጃዎች በነፃ የሚቀርቡበት ማዕከል ዛሬ ሥራ መጀመሩ ተነገረ፡፡  በማዕከሉ…
2021-12-04
መሠረታዊ የሚባሉና ዜጎችን የሚጠቅሙ የጤና መረጃዎች በነፃ የሚቀርቡበት ማዕከል ዛሬ ሥራ መጀመሩ ተነገረ፡፡  በማዕከሉ…
2021-12-04
ሕወሃት በአፋር ክልል የተፈፀመው ወረራ ባደረሰው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ሳቢያ በክልሉ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ የሚሆን…
2021-12-04
በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና በእስራኤል እና በኢራን መካከል ያለው ግንኙነት ፍፁም የጠላትነት ነው፡፡ በኢራን የኒኩሊየር መርሃ…
2021-12-04
ኢትዮጵያ በህግ አውጪ አካሏ ሽብርተኛ ብላ የፈረጀችውን ሕወሃት መዋጋት ከጀመረች 1 ዓመት አልፏታል፡፡ ጦርነቱ፣ ውጊያው…
2021-12-04
ኢትዮጵያ በህግ አውጪ አካሏ ሽብርተኛ ብላ የፈረጀችውን ሕወሃት መዋጋት ከጀመረች 1 ዓመት አልፏታል፡፡ ጦርነቱ፣ ውጊያው…