ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ታህሳስ 14፣ 2012 የሸገር ስፖርት ወሬዎች

የ14ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የመዝጊያ ስነ ስርዓት በኢንተር ኮንቲነንታል አዲስ ሆቴል ተካሂዷል። የመዝግያ ስነ ስርዓቱ ዋና አካል የነበረው የሽልማት መርሃ ግብርም ተከናውኗል።
  • የቅዱስ ጊዮርጊሱ ሳላዲን ሰኢድ ለሽልማት በታጨባቸው ሁለት ዘርፎች አሸንፏል።
  • የተሸለመባቸው ዘርፎች በውድድሩ ባስቆጠራቸው 4 ጎሎች በኮከብ ግብ አስቆጣሪነት እንዲሁም ወልቂጤ ከተማ ላይ ባስቆጠራት ጎል በምርጥ ጎል አስቆጣሪነቱ ዘርፍ ነው።
  • የኢትዮጵያ ቡናው ፈቱዲን ጀማል የውድድር ኮከብ ተጨዋች ተብሏል።
  • የኮከብ አሰልጣኝነትን ክብርን ደግሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ሰርዳን ዝቪችሆቪሰች አሸንፈዋል።
አለን ፓርዲው ወደ አሰልጣኝነት መንበር ዳግም ተመልሰዋል።
  • የቀድሞው የኒውካስትል ዩናይትድና ዌስትሃም አለቃ እንግሊዛዊው የ58 ዓመት ጎልማሳ አለን ፓርዲው በደች ዋናው ሊግ ወይም ኤሪዲቪዜ ላይ የሚወዳደረው አዶ ደን ሀግ አሰልጣኝ ተደርገው መሾማቸውን ቢቢሲ ስፖርት ተናግሯል።
  • የፓርዲው ኋላፊነት እስከ ውድድር ዘመኑ ማብቂያ ድረስ የሚዘልቅ መኾኑም ተሰምቷል።
  • ክሪስ ፖዌል ደግሞ የፓርዲው ምክትል ይሆናሉ ተብሏል።
  • አዶ ደን ሀግ በኤሪዲቪዜው የደረጃ ሰንጠረዥ ከወራጅ ቀጠናው በሁለት ነጥቦች ከፍ ብሎ 17ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ዐቢይ ሐብታሙ

ምስል ምንጭ፦ አዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን
ቁልፍ ቃላት
ምላሽ