ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ህዳር 17፣2014 - የመከላከያ ሠራዊት ቡርቃንና በባቲ ከተማ ዙሪያ ያሉ ተራሮችን መቆጠጠሩን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ተናገረ

Image
FDRE-GCS

የመከላከያ ሠራዊት ቡርቃንና በባቲ ከተማ ዙሪያ ያሉ ተራሮችን መቆጠጠሩን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ተናገረ።

የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ምሽቱን ይፋ ባደረገው መግለጫ፣ "በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁርጠኝነት የተነቃቃው ጀግናው ሠራዊታችን በባቲ ካሳጊታ ግንባር ሲደረግ በነበረው ውጊያ ካሳጊታን አስቀድሞ ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ ያወጣ ሲሆን፣ ወደፊት በመገስገስ ቡርቃን እና በባቲ ከተማ ዙሪያ ያሉ ተራሮችን ተቆጣጥሮ ወደ ባቲ ኮምቦልቻ እየገሠገሠ ነው" ብሏል።

በተጨማሪም ሰራዊቱ "በአፋር ክልል፣ በጭፍራ ግንባር ጪፍቱን፣ የጭፍራ ከተማን እና አካባቢውን ከወራሪው ነጻ አውጥቶ ወደፊት በመገስገስ ላይ ነው" ብሏል። 

የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት በዚሁ መግለጫው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መላውን የፀጥታ ኃይል ራሳቸው በመምራት የኅልውና ዘመቻውን ከዳር ለማድረስ ቃል በገቡት መሠረት በግንባር ተገኝተው ቃላቸውን ተግባራዊ እያደረጉ ይገኛሉ ብሏል።
 

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ