ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ህዳር 16፣ 2014- የደቡብ ሱዳኗ ርዕሰ ከተማ ጁባ የአዲሱ ከንቲባ ቢሮ ዝርፊያ እንደተፈፀመበት ተሰማ

የደቡብ ሱዳኗ ርዕሰ ከተማ ጁባ የአዲሱ ከንቲባ ቢሮ ዝርፊያ እንደተፈፀመበት ተሰማ፡፡ የአዲሱ የጁባ ከተማ ከንቲባ ቢሮ ተሰብሮ ገንዘብ ፣ ኮምፒዩተር እና ሰነዶች መዘረፋቸውን ሱዳንስ ፖስት ፅፏል፡፡

የዘራፊዎቹ ማንነት ለጊዜው አልታወቀም ተብሏል፡፡

ለጁባ ከተማ አዲስ ከንቲባ የተሾመለት ቀዳሚው ከንቲባ ካሊስቶ ላዱ አወዛጋቢነት ባላጣው ሁኔታ ከኃላፊነት መባረራቸውን ተከትሎ ነው፡፡ የአዲሱ ከተማ ከንቲባ ቢሮ ዘረፋ የተፈፀመበት ቋሚ ጥበቃዎች እያሉት መሆኑ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

የማዕከላዊ ኢኳቶሪያ ግዛት አስተዳዳሪ ይሄን ወንጀል በፍጥነት አጣሩልኝ ሲሉ ማዘዛቸው ተሰምቷል፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ