ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ህዳር 16፣ 2014- የሊቢያ የቀድሞ መሪ የኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊ ልጅ ሳኢፍ አል ኢስላም ጋዳፊ ከፕሬዝዳንታዊ ምርጫው እጩነታቸው መሰረዛቸው ተሰማ

የሊቢያ የቀድሞ መሪ የኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊ ልጅ ሳኢፍ አል ኢስላም ጋዳፊ ከፕሬዝዳንታዊ ምርጫው እጩነታቸው መሰረዛቸው ተሰማ፡፡

የሊቢያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሳኢፍ አል ኢስላም ጋዳፊን የእጩነት ሰነድ ሳይቀበሉት እንደቀሩ ታስ የመረጃ ምንጭ ፅፏል፡፡

የቀድሞው መሪ ልጅ ከእጩነት የተሰረዙት በሕግ የሚያስጠይቋቸው ጉዳዮች አሉ በሚል ምክንያት መሆኑ ታውቋል፡፡

በርካታ ሌሎች ሰዎችም ከእጩነት መሰረዛቸው ተሰምቷል፡፡

ሳኢፍ አል ኢስላም እና ሌሎች በርካታ እጩዎች ከፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ተፎካካሪነት ተሰርዘዋል ቢባልም የምርጫ ኮሚሽኑ ግን ስለ ውሳኔው በይፋ የደረሰኝ ማስረጃ የለም ብሏል፡፡

ከምርጫው እጩነት ተሰርዘዋል የተባሉት ግለሰቦች ጉዳይ ከፍተኛ ውዝግብ ማስነሳቱ እንደማይቀር ተገምቷል፡፡

ቀደም ሲል ኮሚሽኑ 98 እጩዎችን መዝግቢያለሁ ብሎ ነበር፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ