ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ጥቅምት 17፣ 2014- በአዲስ አበባ በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን የቤት ባለቤት ያደርጋሉ የተባሉት ተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታ እየተካሄደ እንደሆነ ተነገረ

በአዲስ አበባ በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን የቤት ባለቤት ያደርጋሉ የተባሉት ተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታ እየተካሄደ እንደሆነ ተነገረ፡፡

የተገጣጣሚ ቤት ቴክኖሎጂው በከተማዋ በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን የቤት ባለቤት ለማድረግ የሚያግዙ መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።

ቴክኖሎጂው በአነስተኛ ወጪ እና ጊዜ ቤት መገንባት የሚያስችል እና አካባቢው ለልማት ቢፈለግ በቀላሉ ለመነሳት የሚችል ሆኖ የተገነባ ነው ተብሏል፡፡

በኮንስትራክሽን እና ግንባታ ዘርፍ ተመርቀው የተቀመጡ እና ፍላጎት ያላቸውን ወጣቶች በማሰልጠን የሥራ ዕድል እንዲፈጠር የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ሲሉ ከንቲባዋ ተናግረዋል።

ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች በከተማዋ በብዛት እንዲስፋፋ እና በቅርቡ ለተጀመረው የአቅመ ደካማ ነዋሪዎች ቤት እድሳት ሥራ በጥቅም ላይ እንዲውል ከከተማና መሰረተ ልማት ሚንስቴር መስሪያ ቤት ጋር እንሰራለን ብለዋል።

ቴክኖሎጂው በአዲስ አበባ እና በሌሎች ከተሞች መኖሪያ ቤት ችግርን የመቅረፍ እና ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥር በመሆኑ የክልል ከተሞች ቴክኖሎጂውን እንዲጠቀሙ ይደረጋል ብለዋል።

ተገጣጣሚ ቤቶቹ አስተማማኝ እና በአነስተኛ ወጪ በአጭር ጊዜ መጠናቀቅ የሚችሉ መሆናቸውን የቴክኖሎጂው ባለቤት ብርሃኑ ካሣ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ባለፈው ዓመት ታህሳስ ወር የተጀመረው ተገጣጣሚ ቤቶችን የመገንባት ሥራ በ10 በዓመታት ጊዜ 5 ሚሊየን ቤቶችን ለመገንባት ዕቅድ የተያዘበት ነው፡፡

ግንባታው በተጀመረበት በ2013 ዓ.ም ከ 200,000 በላይ ቤቶችን ለመገንባት የታቀደበት እንደነበር ይታወሳል፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ