ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ጥቅምት 17፣ 2014- የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ በአጎአ ዙሪያ ከአሜሪካ ኤምባሲ የሥራ ኃላፊ ጋር መምከራቸው ተነገረ

የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ በአጎአ ዙሪያ ከአሜሪካ ኤምባሲ የሥራ ኃላፊ ጋር መምከራቸው ተነገረ፡፡

ኮሚሽነሯ ሌሊሴ ነሜ ከአሜሪካ ኤምባሲ ከፍተኛ የንግድ ባለሙያ ያሱኢ ፓይ ጋር አሜሪካ ለአፍሪካ ሀገራት በሰጠችው ከቀረጥ ነፃ የንግድ እድል ዙሪያ መክረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በዚሁ የንግድ እድል ብዙ እየተጠቀመች እየደሆነ በማብራራት በአባልነቷ እንድትዘልቅ ኤምባሲው እገዛ እንዲያደርግ ተጠይቋል፡፡

አጎአ አሜሪካ ከሰሀራ በስተደቡብ ላሉ 34 የአፍሪካ ሀገራት ያለ ቀረጥና ኮታ ምርታቸውን ወደ አሜሪካ ገበያ እንዲያስገቡ የሰጠችው የንግድ እድል መሆኑ ይታወቃል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህም አሜሪካ ኢኮኖሚያዊ ጫናና ለማሳደር በሚል ከዚሁ ፕሮግራም ኢትዮጵያን ልታስወጣት ትችላለች የሚለው መረጃ ተደጋግሞ እየተሰማ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የዛሬው ምክክርም ይህ እንዳይሆን በኢትዮጵያ ያለው የአሜሪካ ኤምባሲ እገዛ እንዲያደርግ የተጠየቀበት ነው ተብሏል፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ