ማስታወቂያ

programs top mid size ad

መስከረም 4፣ 2014- ከሰሜናዊ ምዕራብ ናይጄርያ ለ2 ሳምንታት ገደማ በፊት ታግተው ከነበሩ ሕፃናት ተማሪዎች በአስራዎች የሚቆጠሩት መለቀቃቸው ተሰማ

ከሰሜናዊ ምዕራብ ናይጄርያ ለ2 ሳምንታት ገደማ በፊት ታግተው ከነበሩ ሕፃናት ተማሪዎች በአስራዎች የሚቆጠሩት መለቀቃቸው ተሰማ፡፡ የዛምፋራ ግዛት አስተዳደር ከዕገታ የተላቀቁትን ሴት እና ወንድ ተማሪዎች ለመገናኛ ብዙኃን እንዳሳዩ ቢቢበሲ ፅፏል፡፡

ሕፃናቱ በዕገታ ላይ በነበሩበት ወቅት ታጣቂዎች ሊገድሏቸው ሲዝቱባቸው እንደነበር ተናግረዋል፡፡ በናይጄርያ በአሁኑ ወቅት የተማሪዎች ዕገታ የዕለት ከዕለት ክስተት ያህል እየሆነ መጥቷል፡፡

ብዙውን ጊዜ ታጣቂዎች ዕገታየሚፈፅሙት የማስለቀቂያ የቤዛ ክፍያ ለመጠየቅ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በአስራዎች የሚቆጠሩትን የዛምፋራ ተማሪዎች ለማስለቀቅ የቤዛ ክፍያ ስለመክፈሉ የግዛቲቱ ሹሞች ያነሱት ነገር የለም፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ