ማስታወቂያ

programs top mid size ad

መጋቢት 28፣ 2013- ኬንያ ከፍተኛ የፀረ HIV መድኃኒት እጥረት አጋጥሟታል ተባለ

ኬንያ ከፍተኛ የፀረ HIV መድኃኒት እጥረት አጋጥሟታል ተባለ፡፡

ቀደም ሲል ለኬንያ የፀረ HIV መድኃኒቱ ሲቀርብላት የቆየው ዩ ኤስ ኤይድ በተሰኘው የአሜሪካ የተራድኦ ድርጅት በኩል እንደነበር ቢቢሲ አስታውሷል፡፡

አሁን የተራድኦ ድርጅቱ የመድኃኒቱን አቅርቦት ሙሉ በሙሉ ማቆሙ ተሰምቷል፡፡

ድርጅቱ የመድኃኒት አቅርቦቱን ያቆመው ኬንያ ውስጥ በመድኃኒቱ አስተዳደር ረገድ ምዝበራ እና ብልሹ አሰራር ሰፍኗል በሚል ምክንያት እንደሆነ ታውቋል፡፡

የኬንያ መንግሥታዊ የመድኃኒት አስተዳደር ባለስልጣን ግን የሚቀርብበትን ውንጀላ እያስተባበለ ነው ተብሏል፡፡

1.5 ሚሊዮን ያህል ኬንያውያን ከHIV ኤድስ ጋር እንደሚኖሩ መረጃው አስታውሷል፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ