የቦይንግ ኩባንያ ሁሉም 777 አውሮፕላኖች ለጊዜው ከበረራ ውጭ ቢሆኑ የተሻለ ይሆናል አለ፡፡
አንድ የዚህ ስሪት አውሮፕላን የቀኝ ሞተር በእሳት መያያዙን ተከትሎ ዩናይትድ አየር መንገድ 24 የዚህ ዓይነት አውሮፕላኖቹን ከአገልግሎት ውጭ አድርጓቸዋል፡፡
ጃፓንም የዚህ ስሪት አውሮፕላኖች ለጊዜው ከበረራ ውጭ እንዲሆኑ መምከሩ ታውቋል፡፡ ቀደም ሲል ቦይንግ 737 ማክስ 8 በአለም ዙሪያ ለ2 ዓመታት ያህል ከበረራ ውጭ ሆኖ መቆየቱን መረጃው አስታውሷል፡፡
የአሁኑ የቦይንግ 777 ጉዳይ ደግሞ ለኩባንያው በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖበታል፡፡
በ
- 1 ጊዜ የታየ
ቁልፍ ቃላት