በአዲስ አበባ ከ13 ሚሊዮን ካሬ ሜትር በላይ ቦታ በህገ-ወጥ ወረራ ሲያዝ እና መሬት ሳይሰጣቸውና የግንባታ ፈቃድ ሳያገኙ 332 ህንፃዎች ሲገነቡ ዝም ብሎ የተመለከተው አመራር እንዲጠየቅ ይደረጋል ተባለ፡፡
በህገ-ወጥ መንገድ የተያዙ ከ52,000 በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እንዲለቀቁ ተደርጎ እንደገና እጣ እንዲወጣባቸው መወሰኑንም ሰምተናል፡፡
በጉዳዩ ላይ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ የሰጡትን መግለጫ ትዕግስት ዘሪሁን ተከታትላዋች፡፡