ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ጥር 18፣ 2013 / በአዲስ አበባ ከተማ 323 ባለቤት አልባ ሕንፃዎች በጥናት መለየታቸውን የከተማ አስተዳደሩ ተናገረ

Image
Addis-Abeba-city

በአዲስ አበባ ከተማ 323 ባለቤት አልባ ሕንፃዎች በጥናት መለየታቸውን የከተማ አስተዳደሩ ተናገረ፡፡

የሕንፃዎቹ ባለቤት እኔነኝ ብሎ የቀረበ የለም ያሉት የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ናቸው፡፡ በተደረገ ጥናት በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ከተገነቡት ከእነዚህ ህንፃዎች መካከል 58ቱ ተጠናቀው እየተከራዩ ያሉም ይገኙበታል ተብሏል፡፡

264 ሕንፃዎች ግን ግንባታቸው ተጀምሮ በተለይ ከለውጡ በኋላ ሳይጠናቀቁ ግንባታቸው የቆሙ እንደሆኑ ምክትል ከንቲባዋ ተናግረዋል፡፡ ሕንፃዎቹ ሲገነቡ ምንም ዓይነት የግንባታ ፈቃድ ያልወሰዱ ናቸው የተባለ ሲሆን እያንዳንዱ ሕንፃ ከ500 ካሬ ሜትር በላይ ቦታ የያዘ መሆኑን ሰምተናል፡፡

በአጠቃላይ ባለቤት አልባ ሕንፃዎች የያዙት የቦታ ስፋት 229,556 ካሬ ሜትር ነው፡፡

ምክትል ከንቲባዋ በሕገ-ወጥ የመሬት ወረራ በጋራ መኖሪያ ቤቶችና በቀበሌ ቤቶች ዙሪያ ዛሬ ከጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል፡፡


 

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ