ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ጥር 12፣2013/ የድምጻዊ ሐጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በቢሾፍቱ በተቀሰቀሰ ሁከት ላይ ሁከቱን አስተባብረዋል፣ በገንዘብም ረድተዋል በሚል በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው፣ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ከቀረበባቸው "ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት" የሚል ክስ ፍርድ ቤት ነጻ ናቸው ብሎ እንደፈረደላቸው ተሰማ

Image
Lidetu-Ayalew

የድምጻዊ ሐጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በቢሾፍቱ በተቀሰቀሰ ሁከት ላይ ሁከቱን አስተባብረዋል፣ በገንዘብም ረድተዋል በሚል በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው፣ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ከቀረበባቸው "ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት" የሚል ክስ ፍርድ ቤት ነጻ ናቸው ብሎ እንደፈረደላቸው ተሰማ፡፡

ዛሬ ዕለተ ረቡዕ ጥር 12፣2013 በነበራቸው የፍርድ ቤት ቀጠሮ የውሳኔ ሂደት፦

1ኛ መሣሪያው በሌላ ሕገ ወጥ መንገድ ያልተገኘና የመንግሥት ንብረት ስለመሆኑ በፖሊስም በአቃቤ ሕግም መረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ፤

2ተኛ ተከሳሹ መሣሪያውን የታጠቁት ያለ ፈቃድ መሳሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል መሆኑን የሚደነግገው አዲሱ አዋጅ ከመውጣቱ ከብዙ ዓመታት በፊት እና የፓርላማ አባል በነበሩበት ወቅት መሆኑ ስለተረጋገጠ፣ ክሱ ውድቅ ተደርጎ ፍርድ ቤቱ በነፃ እንዳሰናበታቸው ተሰምቷል፡፡

አቶ ልደቱ ስለሽግግር መንግሥት ምሥረታ አስፈላጊነት ያወራል ከተባለ ጽሑፍ ጋር በተያያዘ በቀረበባቸው ሌላ ክስ ገና ብይን እንዳልተሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል።

አቶ ልደቱ አያሌው የመሠረቱትና የምክር ቤት አባል የሆኑበት የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) በቅርቡ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መሰረዙ ይታወሳል፡፡

ፓርቲው የተሰረዘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ በአዲሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የስነ ምግባር አዋጅ መሠረት ባካሄደው የመሥራቾችን ፊርማ የማጣራት ሂደት፣ ፓርቲው ካቀረባቸው መሥራች ፈራሚዎች መካከል ከ35 በመቶ በላይ የተረጋገጠ ፊርማ ማግኘት አልቻልኩም ብሎ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ