ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ጥር 4፣ 2013/ በአሜሪካ የፀጥታ ጥበቃው ይበልጥ እየተጠናከረ ነው ተባለ

በአሜሪካ የፀጥታ ጥበቃው ይበልጥ እየተጠናከረ ነው ተባለ፡፡

የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች በ50ዎቹም የአሜሪካ ግዛቶች በጦር መሳሪያ ጭምር የታገዘ ተቃውሞና ሁከት ለመቀሰቀስ እንዳቀዱ የአሜሪካ ፌዴራል የምርመራ ቢሮ FBI ማስጠንቀቁን ቢቢሲ ፅፏል፡፡

የትራምፕ ደጋፊዎች በተለይም በተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በዓለ ሲመት መዳረሻ እና የእለቱ እለት በጦር መሳሪያ ጭምር የታገዘ ተቃውሞ እና ሁከት ለመቀስቀስ ማቀዳቸው ተሰምቷል፡፡ 

በዚህም የተነሳ በአሜሪካ እና በግዛቶቹ ሕግ አውጭ አካላት መሰብሰቢያዎች የብሔራዊ ዘብ ወታደሮች እና የፖሊስ ባልደረቦች በብዛት እየተሰማሩ ነው ተብሏል፡፡

ባለፈው ሳምንት የትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች የአገሪቱን ሕግ አውጭ አካላት ሕንፃዎች በመውረራቸው የተነሳ ፕሬዝዳንቱ የስራ ዘመናቸው ከማጠናቀቃቸው አስቀድሞ ከዋይት ሐውስ ለማባረር እንደራሴዎቹ ይመክራሉ መባሉ ተሰምቷል፡፡

ጆ ባይደን በመጪው ጥር 12 ቀን በሚከናወን በዓለ ሲመት 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ይሆናሉ፡፡ ባይደን በእለቱ በግላጭ ቃለ መሐላ ለመፈፀም እንደማይፈሩ ተናግረዋል፡፡

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ